የአፍሪካ ቢሊየነሮች ቁጥር ቀነሰ

 (ኢሳት ዲሲ–ጥር 7/2011)በአፍሪካ የቢሊየነሮች ቁጥር ከ23 ወደ 20 መውረዱን ፎርብስ ዘገበ። የባለጸጎቹን የሃብት መጠን በተመለከተ በየዓመቱ ደረጃ የሚያወጣው ፎርብስ በሳምንቱ መጨረሻ በለቀቀው ሪፖርት ናይጄሪያዊው አሊኮ ዳንጉቴ በ10.3 ቢሊየን ዶላር አሁንም የአፍሪካ ግንባር ቀደም ሃብታም ቢሆኑም ሃብታቸው ከቀደመው ዓመት ወደ 2 ቢሊዮን ዶላር ቀንሶ ተገኝቷል። አሊኮ ዳንጎቴ በኢትዮጵያ የሚገኘው ዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ባለቤት መሆናቸውም ይታወቃል። ከዓመት በፊት የዚሁ ፋብሪካ ስራ አስኪያጅና ...

Read More »

በአለም በከባድ ድህነት ውስጥ ያሉ ዜጎች በአምስት ሃገራት ይኖራሉ ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 7/2011)በአለም እጅግ ከፍተኛ በሚል ድህነት ውስጥ ካሉ ዜጎች ግማሽ የሚሆኑት የሚኖሩት ኢትዮጵያን ጨምሮ በአምስት ሃገራት መሆኑ ተገለጸ። እንደጥናቱ ቢሊየን ከሚበልጠው የዓለም ህዝብ 736 ሚሊየኑ በተጎሳቆለ ድህነት ውስጥ የሚኖሩ መሆኑ ታውቋል። ከነዚህ ውስጥ ደግሞ ግማሹ ማለትም 368 ሚሊየኑ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአምስት የአፍሪካ ሃገራት የሚገኙ ናቸው። የአለም ባንክ ባላፈው ቅዳሜ ይፋ ባደረገውና እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2015 በተደረገው ጥናት መሰረት በዓለማችን ...

Read More »

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በኢንዶኔዢያ ተገዶ እንዲያርፍ ተደረገ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 7/2011)የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን የኢንዶኔዢያን የአየር ክልል ያለፈቃድ ጥሷል በሚል በተዋጊ ጀቶች ተገዶ እንዲያርፍ መደረጉ ተገቢ ርምጃ እንዳልሆነ የኢትዮጵያ አየር መንገድ  ገለጸ። በዓለም አቀፍ የሲቪል አቪየሽን ድርጅት የቺካጎ ኮንቬንሽን መሰረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሕገ-ወጥ ተግባር አለመፈጸሙን ገልጿል። ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነው የበረራ ቁጥር ET 32728 የሆነው የዕቃ ማጓጓዣ አውሮፕላን ትናንት የኢንዶኔዥያን የአየር ክልል ያለፈቃድ ጥሶ ገብቷል ...

Read More »

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከነገ ጀምሮ እንደሚሰበሰብ ታወቀ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 7/2011)የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከነገ ጀምሮ በአዲስ አበባ እንደሚሰበሰብ አስታወቀ። በአባል ድርጅቶቹ በተለይም በሕወሃትና በሌሎች መካከል ያለው ግንኙነት ከጊዜ ወደ ግዜ እየሻከረ በመጣበት ወቅት የተጠራው ይህ ስብሰባ በፌደራል መንግስት በከባድ ወንጀል የሚፈለጉትን አቶ ጌታቸው አሰፋን ጨምሮ ሌሎች ተጠርጣሪዎችን የትግራይ ክልል መንግስት የደበቀበትን ጉዳይ ጨምሮ በርካታ የልዩነት ነጥቦች ይነሱበታል ተብሎ ይጠበቃል። የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ስልጣናቸውን መልቀቃቸውን ...

Read More »

የኪርጊስታን ወታደራዊ አውሮፕላን በደረሰበት ቃጠሎ 15 ሰዎች ሞቱ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 6/2011) ንብረትነቱ የኪርጊስታን መንግስት የሆነ የዕቃ ማጓጓዣ ወታደራዊ አውሮፕላን በደረሰበት ቃጠሎ 15 ሰዎች መሞታቸው ተዘገበ። ቦይንግ 707 የሆነው ወታደራዊ አውሮፕላን አሳፍሯቸው ከነበሩት 16 ሰዎች በህይወት የተረፈው አንድ ሰው ብቻ ሲሆን እሱም ሆስፒታል መወሰዱ ተመልክቷል። በመጥፎ አየር ጸባይ ሳቢያ ዛሬ በአራን ርዕሰ መዲና ቴህራን አቅራቢያ ፍታህ አውሮፕላን ማረፊያ ለማረፍ ሲሞክር መንደርደሪያውን በመሳቱ ቃጠሎ የደረሰበት ይህ ቦይንግ 707 ወታደራዊ አውሮፕላን ...

Read More »

በቄሌም ወለጋ ባንኮች ተዘረፉ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 6/2011)በቄሌም ወለጋ የኦነግ ታጣቂዎች ባንኮችን ዘረፉ። የመንግስት መስሪያ ቤቶችን ማቃጠላቸውም ተሰምቷል። የቄሌም ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ ለኢሳት እንደገለጹት ባለፉት ሁለት ቀናት በኦነግ ታጣቂዎች ስድስት ባንኮች ተዘርፈዋል። ሁለት የወረዳ የመንግስት መስሪያቤቶች ተቃጥለዋል። በመንግስትና በግል ባንኮች ላይ በተፈጸመው ዝርፊያ ምን ያህል ገንዘብ መወሰዱን ማወቅ አልተቻለም። ኦነግ በዞኑ ግድያን ጨምሮ የተለያዩ የሽብር ተግባራትን መፈጸሙን የሚያመለክቱ መረጃዎች በመውጣት ላይ ናቸው። በሌላ በኩል አየር ...

Read More »

በቅማንትና በአማራ ህዝብ መካከል በተፈጠረ ግጭት በርካታ ሰዎች ተገደሉ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 6/2011) በቅማንትና በአማራ ህዝብ መካከል በተፈጠረ ግጭት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን የአማራ ክልል መንግስት አስታወቀ። ባለፉት ሁለት ቀናት ሽንፋ በተባለ የመተማ ወረዳ አካባቢ ሁለቱ ወገኖች ከፍተኛ ሰብዓዊ ጥፋት ካደረሰ ግጭት ውስጥ መግባታቸውን የክልሉ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሃላፊ ለኢሳት ገልጸዋል። ሃላፊው አቶ አሰማህኝ አስረስ የሁለቱ ወገኖች ግጭት በሶስተኛ ወገን የተጠነሰሰና እንዲባባስ የሚደረግ ነው ብለዋል። ይህን በስም ያልጠቀሱትን ሶስተኛ ወገን እጁን ክልሉን ...

Read More »

ከከምባታ ጠምባሮ ወደ ከፋ ዞን በገቡ ነዋሪዎች ላይ ጥቃት ተፈጸመ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 6/2011)ከከምባታ ጠምባሮ ወደ ከፋ ዞን ከ15ዓመታት በፊት በሰፈራ የገቡ ነዋሪዎች ላይ ጥቃት ተፈጸመ። ከመስከረም ወር ጀምሮ በተለያዩ ጊዜያት ሲፈጸም የነበረው ጥቃት ተጠናክሮ ባለፈው ሳምንት በርካታ ሰዎች መገደላቸው ታውቋል። የከምባታ ጠምባሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶክተር ታከለ ነጫ ለኢሳት እንደገለጹት በጥቃቱ 37 ሰዎች ተገድለዋል። ከ30ሺህ በላይ ዜጎች ተፈናቅለዋል። ለመንግስት ጥሪ ብናደርግም ቶሎ ባለመድረሱ አደጋው ሊከፋ ችሏል ሲሉ ዋና አስተዳዳሪው ገልጸዋል። ...

Read More »

የዚምባቡዌው ሮበርት ሙጋቤ 150 ሺህ ዶላር ተሰረቁ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 11/2011)ከቀድሞ የዚምባቡዌ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ ሻንጣ 150 ሺህ የአሜሪካን ዶላር የሰረቁ ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ። ተጠርጣሪዎቹ ገንዘቡን እንደሰረቁና በገንዘቡም ተሽከርካሪ ቤትና ከብቶች እንደገዙበት አቃቤህግ አስታውቋል። ከሌቦቹ ውስጥ የሮበርት ሙጋቤ የቅርብ ዘመድ እንደሚገኙበትም ታውቋል። ዚምባቡዌን ለ37 ዓመታት ያህል የገዙትና በወታደሮች አስገዳጅነት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2017 ስልጣናቸውን የለቀቁት የ94 ዓመቱ አዛውንት ሮበርት ሙጋቤ 150 ሺህ ዶላር የተሰረቀው ከገጠር መኖሪያቸው ነው። ...

Read More »

አቶ ሰለሞን በቀለ አረፉ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 3/2011)በኢትዮጵያ በተካሄዱ የለውጥ እንቅስቃሴዎች ውስጥ በገንዘባቸውና በሃሳባቸው ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ የሚታወቁት አቶ ሰለሞን በቀለ አረፉ። የቀብራቸው ስነስርአትም ነገ በአሜሪካ ቨርጂኒያ ግዛት ፌርፋክስ  ይፈጸማል። በኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ ለማምጣት በሃገር ቤት የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶችን በማገዝ፣ተባብረው እንዲሰሩም ድጋፍ በማድረግ ስማቸው የሚጠቀሰው አቶ ሰለሞን በቀለ፣ቅንጅት በተፈጠረበት ወቅትም ከፍተኛ ድጋፍ ካደረጉ ባለሃብቶች ውስጥም ይጠቀሳሉ። ከ52 አመታት በፊት ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ የተጓዙት አቶ ሰለሞን ...

Read More »