(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 15/2011)አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሳ ለ3ኛ ጊዜ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ። በጥረት ኮርፖሬት ተፈፅሟል በተባለ የሀብት ምዝበራ የተጠረጠሩት አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሳ ለሶስተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ ተጨማሪ የ14 ቀን ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል። ፍርድ ቤቱ በጥያቀው ላይ ወሳኔ ለመስጠት ለ ሰኞ ቀጠሮ ሰጥቷል። የአማራ ክልል ፀረ ሙስና ኮሚሽን አቃቢ ህግ ተጨማሪ ምርመራዎችን ለማድርግ የ14 ቀናት ጊዜ ...
Read More »የኦነግ አባላት ከነበሩባቸው ቦታዎች እየተመለሱ ነው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 15/2011) 2011በመንግሥትና በኦነግ መካከል በአባገዳዎችና በሽማግሌዎች አማካይነት የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ የግንባሩ አባላት ከነበሩባቸው ቦታዎች በሰላም እየተመለሱ መሆናቸው ተነገረ። በምዕራብ ኦሮሚያ የሚንቀሳቀሰው የኦነግ ኃይል አዛዥ ኩምሳ ድሪባ ወይም በትግል ስሙ መሮ በመባል የሚታወቀው ግን ይህንን ለመፈፀም ዝግጁ አይደለም ተብሏል። በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ተሰማርተው የሚገኙ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ጦር አባላት የአባገዳዎችን ጥሪ ተከትለው ትጥቅ ፈትተው ወደ ጦር ካምፖች ከመግባታቸው በፊት ...
Read More »በለገጣፎ አንድም የተፈናቀለ ዜጋ የለም ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 15/2011) በለገጣፎ ተፈናቅሎ ሜዳ ላይ የተጣለ አንድም ዜጋ የለም ሲሉ የለገጣፎ ከተማ ከንቲባ ገለጹ። እስካሁንም ህገ ወጥ በሚል የፈረሰ ቤት የለም፣ የፈረሱትም በመንግስት ቦታ ላይ የተገነቡ ቤቶች ናቸው ብለዋል። የኦሮሚያ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ አድማሱ ዳምጠው ግን ክልሉ ለከተሞች ልማት ከሰጠው ትኩረት ጋር በተያያዘ በህገወጥ የተገነቡ ቤቶች እየፈረሱ መሆኑን ገልጸዋል። ሕጋዊ ከሆኑ ደግሞ መራጃ እንዲያቀርቡ አስቀድሞ ተጠይቀዋል ብለዋል። ...
Read More »የሲዳማ ዞን ክልል የመሆን ጉዳይን የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 14 /2011)የሲዳማ ዞን ክልል የመሆን ጥያቄን በህገ መንግስቱ መሰረት ተግባራዊ እንዲሆን የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ በሀዋሳ ከተማ ተካሄደ። በሲዳማ ዞን በሚገኙ 36 ወረዳዎችና ከተማ አስተዳድሮች የተውጣጡ ነዋሪዎች የተሳተፉበት ሰላማዊ ሰልፍ ሕገምንግስቱ ይከበር የሚል ጥያቄ አቅርበዋል። የደቡብ ክልል ምክር ቤት በጥቅምት ወር ባካሄደው መደበኛ ጉባኤ የሲዳማ ዞን ክልል የመሆን ጥያቄ ህገ መንግስታዊ ሂደቱን ተከትሎ እንዲፈጸም ባለፈው ጥቅምት ወር ባካሄደው ጉባኤ ...
Read More »ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በፋይናንስ ዘርፍ እንዲሳተፉየሚፈቅድ ረቂቅ ሕግ ተዘጋጀ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 14 /2011) በፋይናንስ ዘርፍ ውስጥ እንዳይሳተፉ በሕግ ተከልክለው የቆዩ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን በዘርፉ ተሳታፊ እንዲሆኑ የሚፈቅድ ረቂቅ ሕግ መዘጋጀቱን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዢ አስታወቁ፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶር ይናገር ደሴ በሰጡት መግለጫ፣ በፋይናንስ ዘርፉ ውስጥ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንዳይሳተፉ የሚያግደውን ሕግ በማሻሻል ተሳታፊ የሚሆኑበት መንገድ መመቻቸቱን አስታወቀዋል፡፡ ይሕ በእንዲህ እንዳለም የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በተለይ ለግብርና የሰጠው ከ6 ቢሊየን ብር ...
Read More »በለገጣፎ የተጀመረው ቤትን የማፍረስ ዘመቻ ህግን መሰረት ያደረገ ነው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 14 /2011)በለገጣፎ የተጀመረው ቤትን የማፍረስ ዘመቻ ህግን መሰረት ያደረገ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ሚልኬሳ ሚደግሳ ተናገሩ። በጉዳዩ ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የቢሮ ሃላፊው በለገጣፎ እየተወሰደ ያለው እርምጃ የሊዝ አዋጅ 721ን መሰረት ያደረገ መሆኑን ቢሮ ሃላፊው ገልጸዋል። የኦሮሚያ ክልል መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ሚልኬሳ ሚደግሳ እንደገለጹት እርምጃው ከተሞች ስርዓት ባለውና ዓለም አቀፍ ...
Read More »አቶ ዳንኤል በቀለ መንግሥት ያቀረበላቸውን ጥያቄ ተቀበሉ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 14 /2011)በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አቶ ዳንኤል በቀለ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር እንዲሆኑ መንግሥት ያቀረበላቸውን ጥያቄ መቀበላቸው ተሰማ። ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንዳረጋገጡት አሜሪካን የሚገኙት የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አቶ ዳንኤል፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽንን በኮሚሽነርነት እንዲመሩ መንግሥት ላቀረበላቸው ጥያቄ ፈቃደኛ ሆነዋል። ለሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና ለሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ኮሚሽነሮች የሚሾሙት፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚያቋቁመው ...
Read More »በቀድሞ መርማሪዎች ላይ ክስ ቀረበ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት/2011) አስር የቀድሞ መርማሪዎች አሰቃቂ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈፅመዋል የሚል ክስ ቀረበባቸው። ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስሩ የቀድሞ መርማሪዎች በአጠቃላይ 78 ክሶች እንደተመሰረተባቸው አስታውቋል። ከክሶቹ መካከል እስረኞችን እጃቸውን በካቴና በማሰር፣ በጣት እንዲቆሙ በማድረግ፣ በኤሌትሪክ ገመድ በመግረፍና በግንባር ግድግዳ በማስገፋት እና በኤሌክትሪክ በማስነዘር ይርገኝበታል። በብልታቸው ላይ 2 እስከ 4 ሊትር ሃይላንድ ውኃ በማንጠልጠል ከ2 ሰዓት እስከ 3 ሰዓት እንዲቆዩ በማስደረግ፣ ፣ ...
Read More »የማረሚያ ቤት የፖሊስ አባላት ላይ ክስ ተመሰረተ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 13/2011)ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ላይ በደረሰው ቃጠሎ በተነሳው ረብሻ የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈፅመዋል በሚል የተጠረጠሩ የማረሚያ ቤት የፖሊስ አባላት ላይ ክስ ተመሰረተ። ተከሳሾች በፌደራል ማረሚያ ቤቶች የቂሊንጦ፣ የዝዋይ እና የሸዋ ሮቢት ማረሚያ ቤት በተለያየ የሃላፊነት ደረጃ ሲሰሩ የነበሩ መሆናቸውም ተገልጿል። የክሱ ዝርዝር እንደሚያስረዳው ነሃሴ 28 ቀን 2008 ዓ.ም ጠዋት በፌደራል ማረሚያ ቤቶች ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ላይ በደረሰው ቃጠሎ በተነሳው ...
Read More »የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን እርዳታ መላክ ጀመረ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት/2011)የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በማዕከላዊና ምዕራብ ጎንደር ዞኖች ለተፈናቀሉ ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታ መላክ ጀመረ። ኮሚሽኑ በማዕከላዊና ምዕራብ ጎንደር ዞኖች ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ለተፈናቀሉ ዜጎች የተለያዩ ሰብዓዊ ድጋፎች መላክ መጀመሩን አስታወቋል። በአማራ ክልል ከተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ከ90 ሺህ ባላይ ዜጎች በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች ይገኛሉ። ከእነዚህ ተፈናቃይ ዜጎች ውስጥም አብዛኛዎቹ በማዕከላዊና ምዕራብ ጎንደር ተፈጥሮ በነበረው የፀጥታ ...
Read More »