ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በፋይናንስ ዘርፍ እንዲሳተፉየሚፈቅድ ረቂቅ ሕግ ተዘጋጀ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 14 /2011) በፋይናንስ ዘርፍ ውስጥ እንዳይሳተፉ በሕግ ተከልክለው የቆዩ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን በዘርፉ ተሳታፊ እንዲሆኑ የሚፈቅድ ረቂቅ ሕግ መዘጋጀቱን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዢ አስታወቁ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶር ይናገር ደሴ በሰጡት መግለጫ፣ በፋይናንስ ዘርፉ ውስጥ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንዳይሳተፉ የሚያግደውን ሕግ በማሻሻል ተሳታፊ የሚሆኑበት መንገድ መመቻቸቱን አስታወቀዋል፡፡

ይሕ በእንዲህ እንዳለም የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በተለይ ለግብርና የሰጠው ከ6 ቢሊየን ብር በላይ ብድር ሊመለስ የማይችልበት ደረጃ መድረሱን  የባንኩ ገዥ ይፋ አድርገዋል፡፡

በኢትዮጵያ ሕግ መሠረት የፋይናንስ ዘርፉ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ላላቸው ብቻ የተፈቀደ ነው።

በዚሁህግ መሰረትም  የውጭ ዜግነት ያላቸው ዳያስፖራዎች በዘርፉ ተሳታፊ እንዳይሆኑ ተገድበው ቆይተዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶር ይናገር ደሴ በሰጡት መግለጫ በፋይናንስ ዘርፍ ውስጥ እንዳይሳተፉ በሕግ ተከልክለው የቆዩ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን በዘርፉ ተሳታፊ እንዲሆኑ የሚፈቅድ ረቂቅ ሕግ ተዘጋጅቷል።

አዲሱ ረቂቅ ዝርዝር ጉዳዩ ባይገለጽም፣ ማሻሻያው ዳያስፖራው በዘርፉ እንዲሰማራ ያስችላል ነው የተባለው፡፡

‹‹በእኛ በኩል በተለይ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በፋይናንስ ዘርፉ መሳተፍ የሚቻልበትን ዕድል እንዲኖር ጥናቶችን አጥንተናል፤›› ሲሉ ዶር ይናገር አስታወቀዋል።

እናም ከሚመለከታቸው ጋር ውይይት ተደርጎበት ከፀደቀ አንድ ትልቅ የለውጥ አካል ይሆናል ብለዋል።

ረቂቅ ሕጉ ከጸደቀ ዲያስፖራዎች ባብንክና ኢንሹራንስ ኢንቨስትመንት እንዲሰማሩ ያስችላቸዋል።

ይሕ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በተለይ ለግብርና የሰጠው ከ 6 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር ሊመለስ የማይችልበት ደረጃ መድረሱን  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶር ይናገር ደሴ አስታውቀዋል፡፡

ባንኩ ለግብርና ከሰጠው ብድር ውስጥ 6.3 ቢሊዮን ብር የሚሆነው ሊመለስ የማይችል መሆኑን ነው የገለጹት፡፡ ይህም የሆነው በተደራጀና በተቀነባበረ መንገድ ብድሩ በመሰጠቱ ነው ብለዋል፡፡

ይሕ በመሆኑም  የባንኩን የተበላሸ የብድር መጠን ከፍ ያደርገዋል የሚል ሥጋት አሳድሯል፡፡ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ባለፈው ዓመት የተበላሸ የብድር መጠኑ 40 በመቶ መድረሱ ይታወሳል፡፡ ‹

‹የልማት ባንክ ከፍተኛ ችግር አለበት፡፡ ያልተመለሰ ብድር ምጣኔው በከፍተኛ መጠን ጨምሯል፡፡ በተለይ ደግሞ ለእርሻ ያበደረው ብድርን መመለስ አልተቻለም፤›› ብለዋል፡፡

ሪፖርተር ጋዜጣ ዶር ይናገር ደሴን ጠቅሶ እንደዘገበው   በግብርና ስራ ስም ክርልማት ባንክ የተበደሩ ሰዎች ወደ ሕግ የሚቀርቡበት ሁኔታ እንዲጀመር ብሔራዊ ባንክ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡