ህዳር 19 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ታዋቂው የዜና ማሰራጫ በአገር ቤት የሚገኙ ጋዜጠኞችን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ ጋዜጠኞች በአሁኑ ጊዜ “የትኛው በሽብርተኝነት ያስከስሳል፣ የትኛው አያስከስስም” በማለት እየተጨነቁ ነው። የሲፒጄ የአፍሪካ ተወካይ ሙሀመድ ኬታ እንዳለው ከሆነ ደግሞ ኢትዮጵያ በጋዜጠኞች ስደት አለምን በመምራት ላይ ናት። ሂውማን ራይትስ ወችን ጨምሮ በርካታ አለማቀፍ ድርጅቶች የኢትዮጵያን የጸረ ሽብር ህግ በአገር ውስጥ የሚካሄዱትን የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ለመግታት ታስቦ የተረቀቀ ...
Read More »በሞያሌ ከተማ በተነሳው ግጭት 7 ሰዎች ተገደሉ
ህዳር 18 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሞያሌ ከተማ የኦሮሞ ተወላጅ በሆኑት ቦረናዎችና የሶማሊ ተወላጅ በሆኑት ገሪዎች መካከል በተነሳ ግጭት ሰባት ሰዎች ተገድለዋል፣ ከሟቾች መካከል ሁለት ሴቶች ይገኙበታል። ህዳር 10 ቀን የተነሳው ግጭት ገሪዎች ወይም ሶማሊዎች በከተማው የሚገኘውን አንድ ትምህርት ቤት ለእኛ መሆን አለበት የሚል ጥያቄ ማቅረባቸውን ተከትሎ ሲሆን፣ ቦረናዎች ደግሞ በእኛ መሬት ላይ ያለን ትምህርት ቤት ሶማሊዎች ሊወስዱት አይገባም ማለታቸውን ...
Read More »በአዲስ አበባ እሁድ እለት በተካሄደው 11ኛው ታላቁ ሩጫ ማህበረሰቡ ገዢውን ፓርቲ ሲያወግዝና ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ብሶቶችን ሲያስተጋባ ዋለ
ህዳር 18 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ዘጋቢያችን እንደገለጠው መንግስት መድረኩ የብሶት ማሰሚያ መድረክ እንዳይሆን በመስጋት ከፍተኛ ጥረት አድርጎ ነበር። ከዚህ ቀደም ህዝቡ መስቀል አደባባይ ሲደርስ ” መለስ ሌባ፣ መለስ ይውረድ” የሚል ጩኸት በማሰማቱ፣ የመሮጫው አቅጣጫ ከአምና ጀመሮ እንዲቀዬር ተድረጎአል። የዘንድሮው የመሮጫ አቅጣጫ ለገጽታ ግንባታ በሚል የጎተራን የማሳለጫ መንገድ እንዲያካትት ተድረጎአል። ይህም ሁሉ ጥረት ተደርጎ ህዝቡ ገዢውን ፓርቲ ከማውገዝና ብሶቱን ...
Read More »የአቶ መለስ ዜናዊ መንግሥት በእነ ኤሊያስ ክፍሌ የክስ መዝገብ በ”ሽብርተኝነት ወንጀል‘ የከሰሳቸውን ተከላከሉ ሲል ውሳኔ አስተላለፈ
ህዳር 18 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአቶ መለስ ዜናዊ መንግሥት በእነ ኤሊያስ ክፍሌ የክስ መዝገብ በ”ሽብርተኝነት ወንጀል‘ የከሰሳቸውን የፖለቲካ ፓርቲ የአመራር አባላትና እና ጋዜጠኞች ተከላከሉ ሲል በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሦስተኛ ወንጀል ችሎት በኩል ውሳኔ አስተላለፈ፡፡ የፌዴራል ፍርድ ቤት ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ለዛሬ ጠዋት ይዞት የነበረውን የችሎት ጊዜ ቀጠሮ ወደ ከሰዓት በኋላ ያስተላለፈ ሲሆን ለዚህም በሰዓቱ ለተገኙት ተከሳሾች፣ የተከሳሽ ቤተሰቦችና ...
Read More »አስደንጋጭ ዜና የደረሰው ኢህአዴግ የከተማውን ህዝብ በመከፋፈል ኮንፈረንስ ሊጠራ መሆኑ ታወቀ
ህዳር 16 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-“የአዲስ አበባ ህዝብ በአስተዳደር በደል ምክንያት ከስርአቱ ጋር ሆድና ጀርባ ሆኗል” የሚል አስደንጋጭ ዜና የደረሰው ኢህአዴግ የከተማውን ህዝብ በመከፋፈል ኮንፈረንስ ሊጠራ መሆኑ ታወቀ የብሄር ብሄረሰቦችን ቀን ምክንያት በማድረግ ገዢው ፓርቲ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በከተማዋና በመላ አገሪቱ ተፈጥረዋል ባለቸው ችግሮች ዙሪያ ውይይት እንደሚያደርግ የደረሰን ዜና አመልክቷል። በዚህም መሰረት ህዳር 17 ከንግዱ ማህበረሰብ አባላት ጋር፣ ...
Read More »በእስር ላይ ይገኝ የነበረ አንድ የቀድሞው የቅንጅት አባል በማረሚያ ቦት ውስጥ ህይወቱ ማለፉ ታወቀ
ህዳር 16 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ምንጮች እንዳሉት መስፍን አድማሱ የተባለው የቀድሞው ቅንጅት ተማራጭ በሙስና ወንጀል ተከሶ ለ 3 አመት ከስድት ወር በእስር ሲማቅቅ ነበር። ግለሰቡ በሶስት አመት የእስርቤት ቆይታው አንድም ቀን ፍድር ቤት ቀርቦ እንደማያውቅ የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ስለግለሰቡ አሟሟት ምክንያት ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። ይሁን እንጅ ግለሰቡ ማረፉን ከቤተሰቦቹ የተገኘው መረጃ አረጋግጧል። በርካታ ዜጎች በሚደርስባቸው ...
Read More »ኢትዮጵያ ጦሯ ወደ ሶማሊያ ግዛት ዘልቆ መግባቱን አመነች
ህዳር 16 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ አንድ የ ኢትዮጵያ ባለስልጣን ለሮይተርስ እንደገለጹት፤በጣም አነስተኛ ቁጥር ያለው የኢትዮጵያ ጦር ወደ ሶማሊያ ግዛት ገብቷል። የደቡባዊ ሶማሊያን አብዛኛውን ክፍል ከተቆጣጠሩት የአልሸባብ ሚሊሻዎች ጋር እየተዋጉ የሚገኙትን የኬንያንና የሶማሊያን የሽግግር መንግስት ሰራዊት ለማገዝ ኢትዮጵያ ተጨማሪ ጦር እንደምትልክም፤ እኚሁ ባለስልጣን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ቀደም ሲል ጦሯ ወደ ሶማሊያ ግዛት እንዳልገባ ስታስተባብል መቆየቷ ይታወሳል። እኚሁ የኢትዮጵያ ...
Read More »የመንግስት ጭቆና ልንሸከመው ከምንችለው በላይ ደርሶአል ሲል አንድነት ፓርቲ ገለጠ
ህዳር 15 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አንድነት ፓርቲ ህዳር 14 ቀን 2004 ዓ/ም ባወጣው መግለጫ የኢህአዴግ አገዛዝ ብሶት የወለደው ህዝብ እየፈጠረ መሆኑን ጠቅሶ፣ ብሶት የወለደው ህዝብም አምባገነኖችን ማስወገዱ አይቀሬ ነው ብሎአል። ፓርቲው የኢትዮጵያ አምባገነኖች ከቱኒዚያው ቤን አሊ፣ ከሊቢያው ጋዳፊ፣ ከግብጹ ሙባረክ ሊመማር አለመቻላቸውን ከጳጉሜ 3 2003 ዓም ጀምሮ የሰለማዊና ህጋዊ ፖለቲካ አራማጆችንና ነጻ ጋዜጠኞችን በሽብርተኝነት ከሶ ወደ ወህኒ ማውረዱን በመጥቀስ ...
Read More »በስደት እጃቸውን ለኔዘርላንድ መንግስት ከሰጡ በሁዋላ፣ ተመልሰው ከመንግስት ጋር ግንኙነት የሚያደርጉት ለማጋለጥ እየሰራን ነው ሲሉ በሆላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውን ገለጡ
ህዳር 15 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ መንግስት የሚያደርሰውን ጥቃት መቋቋም አንችልም በማለት ከአገራቸው ተሰደው በመምጣት እጃቸውን ለኔዘርላንድ መንግስት ከሰጡ በሁዋላ፣ ተመልሰው ከመንግስት ጋር ግንኙነት የሚያደርጉት ኢትዮጵያውያንን ለማጋለጥ እየሰራን ነው ሲሉ በሆላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውን ገለጡ። ለስራቸው እንቅፋት ይፈጥራል በሚል ምክንያት ስማቸውን መግለጥ ያልፈለጉት ኢትዮጵያውያኑ እንዳሉት ፣ ገዢው ፓርቲ በሚጠራቸው ስብሰባዎች ላይ የሚገኙትን ሁሉ በፎቶ እና በሌሎች ማስረጃዎች በማስደገፍ አይ ኤን ...
Read More »የኢትዮጵያ መንግስት ወረራ በረሃብ የተጎዳዉ የሶማሊያ ህዝብ ያለበትን ስቃይ እንደሚያባብሰዉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገለፀ
ህዳር 15 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሰብኣዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩረዉ አለርት ኔት ከናይሮቢ እንደገለፀዉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባወጣዉ የሰብኣዊ ሁኔታ ዘገባዉ የኢትዮጵያ መንግስት ወረራ ፣ በረሃብ የተጎዳዉ የሶማሊያ ህዝብ ከመኖሪያዉ እንዲፈናቀልና ህይወት አድን የሆነዉን እርዳታ ትቶ እንዲሸሽ በማድረግ ያለበትን ስቃይ እንደሚያባብሰዉ ገልጿል። በሶማሊያ 4 ሚሊዮን ህዝብ የምግብ ርዳታ የሚያስፈልገዉ ሲሆን 250 ሺህ ሰዎች ድርቅና የርስ በርስ ግጭት ባስከተሉት ረሃብ የተጎዳ ...
Read More »