በኢትዮጵያ ውስጥ ጋዜጠኞችን በሽብር እያሳበቡ መክሰስ መጀመሩን ተከትሎ ፣ ከፍተኛ ፍርሀት መንገሱን ረዩተር ዘገበ

ህዳር 19 ቀን 2004 /

ኢሳት ዜና:-ታዋቂው የዜና ማሰራጫ በአገር ቤት የሚገኙ ጋዜጠኞችን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ ጋዜጠኞች በአሁኑ ጊዜ “የትኛው በሽብርተኝነት ያስከስሳል፣ የትኛው አያስከስስም” በማለት  እየተጨነቁ ነው።

የሲፒጄ የአፍሪካ ተወካይ ሙሀመድ ኬታ እንዳለው ከሆነ ደግሞ ኢትዮጵያ በጋዜጠኞች ስደት አለምን በመምራት ላይ ናት።

ሂውማን ራይትስ ወችን ጨምሮ በርካታ አለማቀፍ ድርጅቶች የኢትዮጵያን የጸረ ሽብር ህግ በአገር ውስጥ የሚካሄዱትን የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ለመግታት ታስቦ የተረቀቀ መሆኑን ጽፈዋል።