በስደት እጃቸውን ለኔዘርላንድ መንግስት ከሰጡ በሁዋላ፣ ተመልሰው ከመንግስት ጋር ግንኙነት የሚያደርጉት ለማጋለጥ እየሰራን ነው ሲሉ በሆላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውን ገለጡ

ህዳር 15 ቀን 2004 /

ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ መንግስት የሚያደርሰውን ጥቃት መቋቋም አንችልም በማለት ከአገራቸው ተሰደው በመምጣት እጃቸውን ለኔዘርላንድ መንግስት ከሰጡ በሁዋላ፣ ተመልሰው ከመንግስት ጋር ግንኙነት የሚያደርጉት ኢትዮጵያውያንን ለማጋለጥ እየሰራን ነው ሲሉ በሆላንድ የሚኖሩ  ኢትዮጵያውን ገለጡ።
ለስራቸው እንቅፋት ይፈጥራል በሚል ምክንያት ስማቸውን መግለጥ ያልፈለጉት ኢትዮጵያውያኑ እንዳሉት ፣ ገዢው ፓርቲ በሚጠራቸው ስብሰባዎች ላይ የሚገኙትን ሁሉ በፎቶ እና በሌሎች ማስረጃዎች በማስደገፍ አይ ኤን ዲ እየተባለ ለሚጠራው መንግስታዊ ድርጅት ለማስረከብ እየሰሩ ነው።

በነገው እለት የኢትዮጵያ ኢምባሲ በሮተርዳም ከተማ የጠራውን ስብሰባ በማስመልከት ኢትዮጵያኑ እንደገለጡት፣ ከመንግስት ጋር እየሰሩ መንግስት እንዳሰደዳቸው እድርገው ወረቀታቸውን ያገኙ ሁሉ፣ ችግር ላይ ይወድቃሉ ሲሉ አስጠንቅቀዋል።