በእስር ላይ ይገኝ የነበረ አንድ የቀድሞው የቅንጅት አባል በማረሚያ ቦት ውስጥ ህይወቱ ማለፉ ታወቀ

ህዳር 16 ቀን 2004 /

ኢሳት ዜና:-የኢሳት ምንጮች እንዳሉት መስፍን አድማሱ የተባለው የቀድሞው ቅንጅት ተማራጭ በሙስና ወንጀል ተከሶ ለ 3 አመት ከስድት ወር በእስር ሲማቅቅ ነበር።

ግለሰቡ በሶስት አመት የእስርቤት ቆይታው አንድም ቀን ፍድር ቤት ቀርቦ እንደማያውቅ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

ስለግለሰቡ አሟሟት ምክንያት ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። ይሁን እንጅ ግለሰቡ ማረፉን ከቤተሰቦቹ የተገኘው መረጃ አረጋግጧል።

በርካታ ዜጎች በሚደርስባቸው አሰቃቂ ድብደባ በእስር ቤት ውስጥ እንደሚሞቱ ይታወቃል።

መንግስት የአቶ መስፍን አድማሱን ሞት በተመለከተ የሰጠው መግለጫ የለም