የሲ.ፒ.ጄ የ2010- ሀሳብን የመግለጽ ነፃነት ሽልማት አሸናፊ የሆነው የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ አገሩን ጥሎ ተሰደደ

ህዳር 11 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የ 1997 ምርጫን ተከትሎ ከቅንጅት መሪዎችና ከሌሎች ጋዜጠኞች ጋር ታስሮ የነበረውና ዕድሜ ልክ ከተፈረደበት በሁዋላ በይቅርታ የተፈታው ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ፣   ሰሞኑን ለስደት የተዳረገው መንግስት፤  የሰጠውን “ይቅርታ” በማንሳት ዳግም ወደ እስር ቤት ሊያስገባው መወሰኑን በመስማቱ መሆኑን ከኢሳት ጋር ባደረገው አጭር ቃለምልልስ ገልጧል ጋዜጠኛ ዳዊት ፣እነ ውብሸት ታዬ፣ እስክንድ ነጋና ርእዮት አለሙ በሽብረተኝነት ተከሰው ከታሰሩበት ጊዜ ...

Read More »

በመላው አለም የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ የፌስ ቡክ ተጠቃሚ ኢትዮጵያውያን፣ መምህር የኔሰው ገብሬን ፎቶግራፍ በመጠቀም ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሎአል

ህዳር 11 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በመላው አለም የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ የፌስ ቡክ ተጠቃሚ ኢትዮጵያውያን፣ በቅርቡ የመንግስትን ዘረኛና አምባገነን አገዛዝ በመቃወም እራሱን አቃጥሎ የተሰዋውን መምህር የኔሰው ገብሬን ፎቶግራፍ በመጠቀም ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሎአል። ሁኔታውን በቅርበት የተከታተሉ የፌስቡክ ተጠቃሚ ኢትዮጵያውያን እንደገለጹት ከሆነ፣ ፌስ ቡክ በመባል የሚታወቀው የኢንተርኔት መገናኛ መድረክ በአለም ዙሪያ ከ8 መቶ ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች ሲኖሩት በቅርቡም የተጠቃሚዎቹ ቁጥር አንድ ...

Read More »

አዲስ አበባ የሚገኙ የውጪ አገር ኤምባሲዎች በስልክ፣ በኢንተርኔትና በተያያዥ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎቶች መማረራቸው ተዘገበ

ህዳር 11 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኤምባሲዎቹ ምሬታቸውን የገለጹት፤ ኢትዮ ቴሌኮም ዋነኛ ከሚላቸው የኮርፖሬት ደንበኞቹ ጋር ባሳለፍነው ሳምንት ረቡዕ በሒልተን ሆቴል ባካሄደው የሐሳብ ልውውጥ መድረክ ነው። ከኤምባሲዎቹ በተጨማሪ መንግስታዊ መስሪያ ቤቶች ጭምር ምሬታቸውን የገለጹ ሲሆን፤ ቴሌን ካማረሩት አስተዳደራዊ መስሪያ ቤቶች መካከል የአዲስ አበባ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ይገኝበታል። የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት፤የአፍሪካ መዲና የሆነችው ኢትዮጵያ በስልክና በ ኢንተርኔት አገልግሎት ፤ከመንግስት አልባዋ ሶማሊያ ...

Read More »

የመምህር የኔሰው ገብሬ አሟሟት በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የግፍ አገዛዝ የደረሰበትን ደረጃ ያሳያል ሲሉ ኢትዮጵያውያን ገለጡ

ህዳር 9 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፍትህ፣ ዲሞክራሲና ነጻነት በሌለበት አገር አልኖርም በማለት እራሱን በእሳት አቃጥሎ የገደለው መምህር የኔሰው ገብሬ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የግፍ አገዛዝ የደረሰበትን ደረጃ ያሳያል ሲሉ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች እና የሲቪክ ማህበረሰብ አባላት ገለጡ የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ፌደራሊስት ( ኦፌዴን) ሊቀመንበር የሆኑት አቶ በቀለ ነገአ ለኢሳት እንደተናገሩት ፤ የየኔሰው ሞት አስደንጋጭ ዜና ቢሆንባቸውም፤ የእኛ ...

Read More »

የኢትዮጵያ መንግስት የአገሪቱን መሬት ለባለሃብቶች ማቀራመቱ በምንም ዓይነት ተቀባይነት የሌለዉ ፍፁም ጎጂ ተግባር እንደሆነ ተገለፀ

ህዳር 9 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የዎርልድ ፕሬስ ጋዜጠኛ የመሬት ቅርምትና የአለም ባንክ በሚል ርዕስ ባቀረቡት ጥናታዊ ፅሁፍ በኢትዮጵያ የዉጭ ኢንቬስትሜንትን ለማዳበር ከነበረዉ ፍላጎት አንፃር የአገሪቱን ለም መሬቶች ለዉጭ ባለሃብቶች ለመስጠት የተወሰደዉ እርምጃ ማህበራዊ፤ አካባቢያዊና የህዝቡን የምግብ ፍላጎት ለመጠበቅ በሚያስችል ሁኔታ አለመፈፀሙን ገልፀዋል። የኢትዮጵያ መንግሰት በመሬት ቅርምቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ገበሬዎች እንደሌሉ ቢገልፅም በጋምቤላና በቤንሻንጉል ክልል 45 ሺህና 90 ሺህ ሰዎች ...

Read More »

መንግስት የየኔሰው ገብሬን ሞት ለመሸፋፋን ከፍተኛ ሩጫ እያደረገ ነው፣ ማንም ሰው ከዬኔሰው ቤተሰቦች ጋር እንዳይገናኙ መከልከሉ ታወቀ

ህዳር 8 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዲሞክራሲና ፈትህ በሌለበት አገር አልኖርም በማለት በዋካ እራሱን በእሳት በማቃጠል የገደለውን የየኔሰው ገብሬን ሞት ለመሸፋፋን ከፍተኛ ሩጫ በማድረግ ላይ የሚገኘው መንግስት፣ የአካባቢው ወጣቶችን ጨምሮ ማንም ሰው ከዬኔሰው ቤተሰቦች ጋር እንዳይገናኙ መከልከሉ ታወቀ የበርካታ ልጆች አስተዳዳሪ የሆነችው  ታደለች በቀለ፣ ከማንኛው ሰው ጋር እንዳትገናኝ ለማድረግ ሰፈሩዋ በሙሉ በፖሊስና በደህንነት ሀይሎች 24 ሰአት ሙሉ እየተጠበቀ መሆኑን የገለጡት ...

Read More »

ኢትዮጵያ ጦሩዋን መልሳ ወደ ሶማሊያ ለማስገባት ከፍተኛ ፍላጎት ማሳየቱዋን የአፍሪካ ህብረት ባለስልጣናት ገለጡ

ህዳር 8 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኒውዮርክ ታይምሱ ጄፍሪ ጀንትልማን እንደዘገበው የኢትዮጵያ ጦር በአልሸባብ ሰራዊት ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ይችል ዘንድ የኢትዮጵያን ሰራዊት መልሶ  ለማስገባት እያሰበ ነው። አንድ የሶማሊያ  ባለስልጣን ግን የኢትዮጵያ ጦር የሸክ ሸሪፍ አህመድን መንግስት ለመደገፍ በሚል ሰበብ ወደ ድንበሩ ዘልቆ መግባቱን ተናግረዋል። የምእራብና የአፍሪካ ህብረት  ባለስልጣናት የኢትዮጵያ ውሳኔ በሶማሊያ ውስጥ የስልጣን ሽሚያ ስለሚፈጥርና ኢትዮጵያም የራሱዋን መንግስት የማቋቋም ፍላጎት ...

Read More »

በሽብር ተግባር ተሰማርታችኋል” በሚል የፈጠራ ክስ ከነ አቶ አንዱዋለም ጋር ታስረዉ የነበሩት አቶ ዘመኑ ሞላ እና አቶ አሳምነዉ ብርሀኑ ተፈቱ

ህዳር 7 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አቶ መለስ ፦” የታሰሩት ሰዎች በሙሉ ሽብርተኛ ለመሆናቸው ከበቂ በላይ ማረጋገጫ አለን” ሲሉ ቢደመጡም ፤የ ኢትዮጵያ ህዝብ ግን የታሠሩት በሙሉ የሰላምና የነፃነት ታጋዮች እንጂ አሸባሪዎች እንዳልሆኑ  በተደጋጋሚ ሲናገር መቆየቱ ይታወቃል። ከእስረኞቹ ቤተሰቦች አንዱ ለ ኢሳት በሰጡት አስተያዬት፦” የታሰሩት ወንድምና እህቶቻችን አሸባሪዎች እንዳልሆኑ ራሳቸው እነ አቶ መለስ  ያውቁታል።የሚያደርጉት የትግል እንቅስቃሴ ስልጣናቸውን እንዳያሳጣቸው በማሰብ ነው ያሰሯቸው። ...

Read More »

ስሎቫኪያ ፦”ኢትዮጵያ ለፈጸመችው ስህተት በይፋ ይቅርታ ልትጠይቅ ይገባል” ስትል አሣሰበች

ህዳር 7 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ስሎቫኪያ በኢትዮጵያ ታስረው የነበሩትን አምባሳደሯን አስመልክቶ  በኢትዮጵያ መንግስት  የተሰጣት ማብራሪያ በቂ ስላልሆነ ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጣት አጥብቃ ጠይቃለች። “ ዘ ስሎቫክ ስፔክታተር”  የተባለው የስሎቫኪያ ጋዜጣ  እንደዘገበው፤ በኢትዮጵያ ፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ውለው ለሁለት ቀናት ከታሰሩ በኋላ የተለቀቁት በኢትዮጵያ የስሎቫኪያ አምባሳደር፣ በጉዳዩ ዙርያ ከስሎቫክ ባለሥልጣናት ጋር ለመመካከር ወደ አገራቸው ተመልሰዋል ፡፡ አምባሳደር ሚላን ዱብቼክ ከመኖሪያቸው ወጥተው የእግር ጉዞ ...

Read More »

በዋካ ከተማ የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ መርተዋል የተባሉት አባት ከሀላፊነት እንዲነሱ ተደረገ፣ ህዝቡ ግን ተቃውሞውን እያሰማ ነው

ህዳር 6 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአካባቢው ያለውን ጭቆና፣ የመልካም አስተዳዳርና የፍትህ መታጣት በመቃወም እራሱን በእሳት በማጋየት ተቃውሞን የገለጠው የመምህር የኔሰው ገብሬ አስደንጋጭ ዜና የህዝቡ የመነጋገሪያ አጀንዳ በሆነበት ማግስት፣ የአካባቢው የሀይማኖት ባለስልጣናት፣ “ተቃውሞውን የሚያስተባብሩት በከተማው የሚገኘው የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ካህን ናቸው”  በሚል ሰበብ  ፣ የቤተክርስቲያኑዋን አስተዳዳሪ የሆኑትን በኩረ ትጉሀን ይልማ መኮንንን ከሃላፊነት አንስተዋል። የእገዳውን  ደብዳቤ የጻፉት የዞኑ የአገረስብከት ሀላፊ የሆኑት መምህር ...

Read More »