የካቲት 3 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለፈው ሳምንት አንድነት ፓርቲ በጠራው ውይይት ላይ የተገኘው ህዝብ ከአዳራሹ አቅም በላይ መሆን፣ የነገውን የመድረክ ስብሰባ የአዘጋጁትን ወገኖች አሳስቦዋቸዋል። አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የመድረክ አባል ለኢሳት እንደተናገሩት በቀድሞው ቀበሌ 42 በአሁኑ ወረዳ 5 የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከቀኑ 7 ሰአት ጀምሮ በሚካሄደው ስብሰባ ላይ በርካታ ህዝብ እንደሚገኝ የሚጠበቅ ቢሆንም፣ ገዢው ፓርቲ የራሱን ሰዎች አብዛኛውን ቦታ እንዲይዙት ...
Read More »በአወልያ የሚገኙ ሙስሊሞች ተቋውሞአችንን በመላው መስጊዶች ማሸጋገር እንችላለን ሲሉ አስጠነቀቁ
የካቲት 3 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአወልያ የሚገኙ ሙስሊሞች ለሰላም ስንል እንጅ፣ ተቃውሞዋችንን በአንዋር መስጊድ እና በመላው አገሪቱ በሚገኙ መስጊዶች ማሸጋገር እንችላለን ሲሉ አስጠነቀቁ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች የአርብ ስግደትን ለማካሄድ በአወልያ በተገኙበት ሰአት እንደተናገሩት መንግስት ለጥያቄቸው መልስ የማይሰጥ ከሆነ ተቃውሞውን በመላ አገሪቱ በሚገኙ መሲኪዶች ሁሉ እንደሚያሸጋግሩት አስጠንቅቀዋል። ችግሩን ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር ተደራድረው መፍትሄ እንዲፈልጉ ከተወከሉት መካከል አንዱ የሆኑት አቡበክር ...
Read More »የኢትዮጵያ መንግስት በሳውዲ አረቢያ ለታሰሩ ወገኖቻቸው በቂ ትኩረት አልሰጠም ተባለ
የካቲት 3 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢንተርናሽናል ክርስቲያን ኮንሰርን ባወጣው ዘገባ እንዳመለከተው፣ በእስር ላይ የሚገኙት 35 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት አስፈላጊውን እገዛ እንዲያደርጉላቸው ቢጠይቁም፣ የኢምባሲው ሰራተኞች ግን ለጉዳያቸው ትኩረት ሊሰጡ አልፈለጉም። እስረኞቹ እንደሚሉት አንድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማት በጎበኛቸው ወቅት በአራት ቀናት ውስጥ ተመልሶ እንደሚመጣ ቃል ቢገባላቸውም ፣ እስከ ዛሬ ዘወር ብሎ እንዳላያቸው ተናግረዋል። በጂዳ ኢምባሲ ጽህፈት ቤት ሰራተኛ የሆኑት መርዋን ...
Read More »በሶሪያ አንድ የመንግስት ደጋፊ የሆኑ ጄኔራል ተገደሉ
የካቲት 3 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የሶሪያ የመከላከያ ሆስፒታል አዛዥ የሆኑት ብርጋዴር ጄኔራል ዶ/ር ኢሳ አል ኮሊ የተገደሉት በታጠቁ አሸባሪዎች ነው ሲሉ የመንግስቱ የመገናኛ ኤጀንሲ ዘግቧል። በሶሪያ ህዝባዊ አመጽ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ አንድ ከፍተኛ የወታደራዊ አዛዥ ሲገደሉ ብርጋዴር ጄኔራል ዶ/ር ኢሳ አል ኮሊ የመጀመሪያ ናቸው። የሶሪያ መንግስት ወታደሮች ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በሆምስ በከፈቱት ጥቃት ከ400 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የመገናኛ ብዙሀን ...
Read More »ሰሞኑን በጦርነት ወሬ ሲታመሱ የቆዩት ደቡብና ሰሜን ሱዳን አንዱ በሌላው ላይ ጦርነት ላለመጫር ተስማሙ
የካቲት 3 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሁለቱ አገሮች ስምምነቱን የፈረሙት በቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት በታቦ ምቤኬ አደራዳሪነት በአዲስ አበባ ነው። ሁለቱ አገሮች አንዱ የሌላውን ሉአላዊነት ለማክበር ተስማምተዋል፤ አላስፈላጊ ከሆነ ፕሮፓጋንዳም ራሳቸውን እንደሚያቅቡ ፈርመዋል ሲሉ ታቦ ምቤኪ ተናግረዋል። በቅርቡ ከነዳጅ ዘይት ጋር በተያያዘ የተነሳው አለመግባባት ለድርድር አለመቅረቡም ተመልክቷል። ደቡብ ሱዳን በኢትዮጵያ በኩል አልፎ ጅቡቲ የሚደርስ የነዳጅ ቧንቧ ለመዘርጋት ስምምነት መፈረሙዋ ይታወሳል።
Read More »በሆሳዕና በተፈጠረው የውሀ እጥረት ነዋሪዎቹ አደጋ ላይ መውደቃቸውን ገለጡ
የካቲት 2 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጡት በከተማው በተከሰተው የውሀ እጥረት የተነሳ የአካባቢው ህዝብ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ወድቋል። ውሀ ከጠፋ ወራት ማስቆጠራቸውን የሚናገሩት ነዋሪዎች በተለይ ባለፈው ሳምንት መብራት እና ውሀ በአንድ ላይ በመጥፋቱ የህዝቡን ችግር አባብሶታል። ህዝቡ የወንዝ ውሀ ለማግኘት 8 ኪሎሜትር ድረስ መጓዝ ግድ እንደሆነበት ነዋሪዎች ይናገራሉ። 20 ሊትር የወንዝ ውሀ በ10 ብር ለመግዛት መገደዳቸውንም ያክላሉ ...
Read More »በታሪካዊነቱ የሚታወቀው ዋልድባ ገዳም ከመንግስት ጋር ውዝግብ ውስጥ ገባ
የካቲት 2 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር ዞን በአድርቃይ ወረዳ የሚገኘው የዋልድባ ገዳም አካባቢ ለሸንኮራ አገዳ ምርት ይፈለጋል በሚል ምክንያት መታጠሩ መነኮሳቱን ጨምሮ የአካባቢውን ህዝብ አስቆጥቷል። በታሪካዊነቱ የሚታወቀው የዋልድባ ገዳም ከጥንት ጀምሮ በይዞታነት የያዘው መሬቱ በግድ እንዲታጠር መደረጉ ያበሳጫቸው መነኮሳትና ህዝቡ ከጠቅላይ ሚኒሰትሩ ጀምሮ ላሉ ባለስልጣናት አቤት ቢልም የሚሰማው አላገኘም። ሰሞኑን ውዝግቡ እየተካረረ መምጣቱን፣ መንግስት ውሳኔውን ካላስተካካለ ...
Read More »ደቡብ ሱዳን የነዳጅ ቧንቧ መስመር ለመዘርጋት ከኢትዮጵያ ጋር ስምምነት ተፈራረመች
የካቲት 2 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በጅቡቲ ወደብ በኩል ነዳጅ ለዉጭ ገበያ ማቅረብ የሚያስችላትን የቧንቧ መስመር በኢትዮጵያ ለመዘርጋት ደቡብ ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር የመግባቢያ ስምምነት መፈራረሟ ተዘግቧል። የደቡብ ሱዳን የማስታወቂያ ሚኒስትር ለአሶስየትድ ፕሬስ የዜና አገልግሎት እንደገለፁት የቧንቧ መስመሩ ባለቤት ደቡብ ሱዳን እንደምትሆንና መስመሩ በኢትዮጵያ በኩል ወደ ጅቡቲ የሚተላለፍበት ተጨማሪ እንደሚሆን ተናግረዋል። የሁለቱ መንግስታት ባለስልጣኖች በወሩ መጀመሪያ ላይ በአዲስ አበባ ላይ የመግባቢያ ...
Read More »አልሸባብ አልቃይዳን በይፋ መቀላቀሉ ተገለፀ
የካቲት 2 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአልቃይዳዉ መሪ በእስልምና ተከታዮች ፎረም ላይ ባስተላለፉት የቪዲዮ መልእክት በሶማሊያ የሚንቀሳቀሰዉ አልሸባብ በፀረ ፅዮናዊነት የሚደረገዉን የጅሃድ ዘመቻ በመቀላቀል የአልቃይዳ አባል መሆኑ እሳቸዉንና እምነት ያላቸዉን እንደሚያስደስት፤ በተቃራኒዉ እምነት የሌላቸዉን ሊያስደነግጥ እንደሚችል ተናግረዋል። የአልቃይዳዉ መሪ በተጨማሪ በሶማሊያ የሚገኙ የእስልምና ተከታዮች ዉሸትን የሚሰብኩትንና ንፁህ በሆነዉ የእስላም ምድር ላይ ይህን መአት ያመጡትን ደካማ የሶማሊያ መሪዎች እንዳይቀበሏቸዉ ጥሪ አድርገዋል። ...
Read More »የአፍሪቃ ቀንድ አሁንም ለረሃብና ለምግብ እጥረት የተጋለጠ እንደሆነ ጥናቶች አረጋገጡ
የካቲት 2 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአፍሪቃ ቀንድ ቁጥሩ 13 ሚሊዮን የሚሆን ህዝብ የምግብ እጥረት እንዳለበትና በመቶ ሺዎች የሚገመቱ ለረሃብ ይጋለጣሉ የሚል ስጋት እንዳለ ኦክስፋምና የእንግሊዝ ህፃናት አድን ድርጅት ያወጡት ሪፖርት ገልጿል። ከ50 እስከ 100 ሺህ ሰዎች እንደሞቱበት በሚነገረዉ በአፍሪቃ ቀንድ ተከስቶ የነበረዉ የረሃብ አደጋ በክፍለ ዘመኑ ከታዩት ሁሉ በአይነቱ ልዩ የሆነ የአስቸኳይ ጊዜ ክስተት እንደነበር ሪፖርቱ ጠቅሷል። ድርቅ ባሰከተለዉ ...
Read More »