ሚያዚያ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዮሐንስ ሲሳይ የተባለው የ40 አመት ጎልማሳ ኢህአዴግ አገሪቱን ከተቆጣጠረ በሁዋላ በአጭር ጊዜ ቢሊየነር ለመሆን የበቃ የዘመኑ ባለሀብት ነው። የሱ እና ሸበል የሚባሉ ኩባንያዎችን የመሰረተው ዮሐንስ ፣ ኢህአዴግ ለምርጫ በሚወዳደርበት ጊዜ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ለፓርቲው ለግሷል። የትኛውም የአገር ውስጥ ባለሀብት ባላደረገው መልኩም፧ ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ በማውጣት ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ቦንድ ገዝቷል። ...
Read More »ከ70 በላይ የፓኪስታን ዜጎች ጋምቤላን ለቀው ወጡ
ሚያዚያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለፈው ቅዳሜ በጋምቤላ በፓኪስታንና በኢትዮጵያውያን ላይ በተፈጸመው ጥቃት አራት ኢትዮጵያውያን እና አንድ ፓኪስታናዊ መገደላቸውን እንዲሁም አራት ፓኪስታናውያንና 5 ኢትዮጵያውያን መቁሰላቸውን ተከትሎ፣ በሼክ ሙሀመድ ሁሴን አል አሙዲን ሳውዲ ስታር ኩባንያ ውስጥ በከፍተኛ አመራርነት ይሰሩ የነበሩ ከ70 በላይ የፓኪስታን ዜጎች አካባቢውን ለቀው ዛሬ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘዋል። ፓኪስታናውያኑ አካባቢውን የለቀቁት የፓኪስታን ኢምባሲ ባለስልጣናት ...
Read More »መንግስት ድምጻችን ይሰማ የሚሉ ወጣቶችን ማሰር ጀመረ
ሚያዚያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከወራት በፊት በአወልያ የተነሳው የእምነት ነጻነት ይከበር ጥያቄ እየተስፋፋ ሄዶ መላው አገሪቱን እያዳረሰ ባለበት ሰአት መንግስት በአንዳንድ አካባቢዎች የሀይል እርምጃ መውሰድ ጀምሮአል። በምእራብ አርሲ ዞን አሳሳ ወረዳ 4 የእስልምና እምነት ተከታዮች በፌደራል ፖሊስ አባላት ከተገደሉ በሁዋላ ፣ ጥያቄውን አነሱ ሙስሊሞችን ማዋከብና ማሰሩ ቀጥሎአል። በአወልያ በተነሳው ተቃውሞ ወቅት የተመረጡ የሙስሊሙ አመራሮች፣ ከአቶ ...
Read More »ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ተቀጣ
ሚያዚያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በእነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ በፌዴራል አቃቤ- ሕግ አቤቱታ የቀረበበት የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የሁለት ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት ትናንት ከሰዓት በኋላ በከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ተፈረደበት፡፡ ፍርድ ቤቱ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የሚገኘውን 5ተኛ ተከሳሽ ክንፈሚካኤል ደበበ (አበበ ቀስቶ) ከማረሚያ ቤት ...
Read More »የመለስ ዜናዊ መንግስት በንጹህ ዜጎች ላይ የሚፈጽመውን ግድያን ቀጥሎበታል ሲል ግንቦት7 አስታወቀ
ሚያዚያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ግንቦት7 ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው የመለስ ዜናዊ መንግስት ለረጅም ጊዜ ይዞት የቆየውን የትግራይን የበላይነትን የማስጠበቅ አላማውን ከግብ ለማድረስ አማራዎችን ከደቡብ ከማፈናቀል ጀምሮ በጋምቤላ ፣ በአፋር እና በአርሲ አካባቢዎች በንጹህ ዜጎች ላይ ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ ወስዷል። ኢትዮጵያ የአለም ታላላቅ ሀይማኖቶች የሆኑት እስልምናና ክርስትና ለዘመናት ተቻችለው የኖሩባት አገር ብትሆንም፣ በቅርቡ እየታዩ ያሉት ምልክቶች ...
Read More »በጋምቤላው በደረሰው ጥቃት የሞቱት የሳውዲ ስታር ሰራተኞች ተሸኙ
ሚያዚያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከጋምቤላ በምስል ተደግፎ ለኢሳት የተላከው ዘገባ እንዳመለከተው ባለፈው ቅዳሜ በአበቦ ወረዳ በሳውዲ ስታርና በሳውዲ ስታር ሰብ ኮንትራክተር በሆነው CRBC ኩባንያ ሰራተኞች ላይ ቅዳሜ እለት በተፈጸመው ጥቃት የሞቱት ዛሬ በአንድ የመከላከያ ሰራዊት ሄሊኮፕተር እና በአንድ አውሮፕላን ተጭነው ወደ አዲስ አበባ ተሸኝተዋል። ድርጊቱ የተፈጸመው ሰራተኞቹ ከአሌሮ ግድብ የሚወጣውን ውሀ ለሩዝ እርሻው ለማቅረብ የቧንቧ ...
Read More »በሺዎች የሚቆጠሩ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ወደ ዋልድባ ተመሙ፣ ሁለት ነጮች ተገድለዋል ሌሎች ሰራተኞች አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል
ሚያዚያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሺዎች የሚቆጠሩ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ወደ ዋልድባ ተመሙ፣ ሁለት ነጮች ተገድለዋል ሌሎች ሰራተኞች አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል የገዳሙ አባቶች ለሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ባቀረቡት ጥሪ መሰረት እስከ 200 ኪሎሜትር ርቀት የሚገኙ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ወደ አካባቢው መትመማቸውን ተከትሎ ሁለት ነጮች መሞታቸውን፣ ሌሎች ሰራተኞች ደግሞ እኛ ከህዝብ ጋር አንጣላም በማለት አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል። የሟቾቹ ...
Read More »የህወሀት ታጣቂዎች፤ በመተማ መንደር ማቃጠላቸው ተገለጸ
ሚያዚያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአካባቢው ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል ተብሎአል።“ጅንግራ”ተብላ የምትጠራውና የመተማ አካል የሆነችው የኮንትሮባንድ መናኸሪያ ሰፈር ፤ በአቶ መለስ መንግስት ታጣቂዎች ሙሉ በሙሉ በእሳት መውደሟ ተገለጸ። መንደሯ በውስጧ ያቀፈቻቸው ከ 50 የሚበልጡ መኖሪያ ቤቶች፤ ከነንብረቶቻቸው ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን ከስፍራው የወጡ ዜናዎች አመልክተዋል። የዜናው ምንጮች ከስፍራው ያስተላለፉት መረጃ እንደሚያመለክተው፤ የኢትዮጵያ መንግስት ጅንግራን ፦’ለልማት እንደሚፈልገው በመግለጽ ...
Read More »ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል የባለቤቷን ሽልማት ልትቀበል ነው
ሚያዚያ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የ2012 የፔን ባርባራ ጎልድ ስሚዝ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት አሸናፊ በሆነው በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ሽልማት ሥነ-ስርዓት ላይ ባለቤቱ ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል እንደምትገኝ ምንጮቹን በመጥቀስ የዘገበው አዲስ ቪው ነው። ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ሀሳቡን በነፃነት በመግለጹ ሳቢያ በፈጠራ የሽብርተኝነት ተከሶ ጉዳዩን በፍርድ ቤት እየተከታተለ ባለበት በአሁኑ ወቅት “ፔን ፍሪደም አዋርድ” የተባለውንና ለጀግና ጋዜጠኞች የሚሰጠውን ...
Read More »በአርሲ ዞን በተነሳ ተቃውሞ ሰዎች መገደላቸው ተሰማ
ሚያዚያ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ትናንት በአርሲ ዞን በአሳሳ ከተማ ትልቁ መስጊድ ውስጥ የተቃውሞ ሰልፍ ባደረጉ ሙስሊሞች ላይ የፌዴራል ፖሊስ አባላት በከፈቱት ተኩስ የ 6 ዓመት ታዳጊ ህፃንን ጨምሮ ሰባት ሰዎች መገደላቸውና በርካቶች መቁሰላቸው ተዘግቧል። ቢላል ራዲዮ ግጭቱ በተከሰተ ጊዜ ከስፍራው ባስተላለፈው ዘገባ በሰልፈኞቹ ላይ ከየአቅጣጫው በተከፈተው የተኩስ እሩምታ ሰባት ሰዎች ወዲያውኑ ሲሞቱ በርካታዎች ከባድና ቀላል የመቁሰል ...
Read More »