የመለስ ዜናዊ መንግስት በንጹህ ዜጎች ላይ የሚፈጽመውን ግድያን ቀጥሎበታል ሲል ግንቦት7 አስታወቀ

 

ሚያዚያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም  

ኢሳት ዜና:-ግንቦት7 ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው የመለስ ዜናዊ መንግስት ለረጅም ጊዜ ይዞት የቆየውን የትግራይን የበላይነትን የማስጠበቅ አላማውን ከግብ ለማድረስ አማራዎችን ከደቡብ ከማፈናቀል ጀምሮ በጋምቤላ ፣ በአፋር እና በአርሲ አካባቢዎች በንጹህ ዜጎች ላይ ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ ወስዷል።

 ኢትዮጵያ  የአለም ታላላቅ ሀይማኖቶች የሆኑት እስልምናና ክርስትና ለዘመናት ተቻችለው የኖሩባት አገር ብትሆንም፣ በቅርቡ እየታዩ ያሉት ምልክቶች ይህ እውነታ በፍጥነት እየተለወጠ መሆኑንና አምባገነኑ መለስም ሁኔታውን ወደ አደገኛ የሀይማኖት ግጭት እየመራው እንደሚገኝ ገልጧል።

ንቅናቄው እንደሚለው ሙስሊሙ ማህበረሰብ ሀይማኖታዊ መብቱ እንዲከበርለት ቢጠይቅም አገዛዙ ግን ምላሹ ጭቆና፣ ማስፈራሪያ፣ ግድያና እስር ሆኗል።

 በአፋር ክልል የመለስ ዜናዊ ወታደሮች በሴቶች እና ህጻናት ላይ ሳይቀር ግፍ መፈጸማቸውን፣ የወሳው ግንቦት7 ፣ የአለማቀፉ ማህበረሰብ የእነዚህን ሴቶችና ህጻናት ድምጽ እንዲሰማ ጠይቋል።

ንቅናቄው በመጨረሻም የአፋር ህዝብ መብቱን ለማስከበር በሚያደርገው ትግል መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከጎኑ እንዲቆሙ ጥሪ አቅርቧል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide