በአርሲ ዞን በተነሳ ተቃውሞ ሰዎች መገደላቸው ተሰማ

ሚያዚያ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም  

ኢሳት ዜና:-ትናንት በአርሲ ዞን በአሳሳ ከተማ  ትልቁ መስጊድ ውስጥ የተቃውሞ ሰልፍ ባደረጉ ሙስሊሞች ላይ የፌዴራል ፖሊስ አባላት በከፈቱት ተኩስ የ 6 ዓመት ታዳጊ ህፃንን ጨምሮ ሰባት ሰዎች መገደላቸውና በርካቶች መቁሰላቸው ተዘግቧል።

ቢላል ራዲዮ ግጭቱ በተከሰተ ጊዜ ከስፍራው ባስተላለፈው ዘገባ በሰልፈኞቹ ላይ ከየአቅጣጫው በተከፈተው የተኩስ እሩምታ ሰባት ሰዎች  ወዲያውኑ  ሲሞቱ   በርካታዎች  ከባድና ቀላል የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል።

ሌሎች የዜና ምንጮች ደግሞ፤ከባድ የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ብዙዎች ከመሆናቸው አኳያ፤ የሟቾች ቁጥር ከተጠቀሰው በላይ ሊያሻቅብ እንደሚችል  እያመለከቱ ነው።

በአዲስ አበባ  እየተካሄደ ያለው የሙስሊሞች መብት የማስከበር   አገር አቀፍ እንቅስቃሴ አንድ አካል እንደሆነ  በተነገረው በአሰሳው  ሰልፍ ሲንጸባረቁ ከነበሩት መፈክሮች መካከል ዋነኞቹ፦”የአህባሽን አስተምህሮ አንቀበልም! መጂሊስ ስለማይወክለን ይውረድልን! መንግስት ጥያቄያችንን ማድበስበሱን ያቁም!” የሚሉት ነበሩ።

የግጭቱ መንስኤም አንድ የአህባሽ አስተምህሮን አምርሮ እየተቃወመ የነበረን ሰልፈኛ ፖሊሶች ክፉኛ በመደብደባቸው እንደሆነ፤ቢላል ከሰልፉ ስፍራ ያነጋገራቸው አንድ አስተባባሪ ተናግረዋል።

ሰውዬው ላይ እየተፈፀመበት ባለው አሰቃቂ ድብደባ ክፉኛ የተቆጡት ሰልፈኞች ፖሊሶቹ ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ በጩኸት መጠየቃቸውን ተከትሎ ውጥረቱ እየተባባሰ በመምጣቱ  ሰልፉን ከተለያዬ አቅጣጫ በዓይነ ቁራኛ ሲከታተሉ የነበሩ ፌዴራል ፖሊስ አባላት ድንገት በሰልፈኛው ላይ የተኩስ እሩምታ መልቀቃቸው ተገልጿል።

ባለፈው ሳምንት በ አንዋር መስጊድ በተካሄደው ተመሣሳይ ሰልፍ ላይ ፓሊሶች ወረቀት ሲበትን የነበረን ወጣት በመኪና ጭነው ለመውሰድ ያደረጉት ሙከራ በሰልፈኛው ህዝብ ትብብር እንደከሸፈ መዘገቡ ይታወሳል።

አሰሳው ሰልፍ ላይ የተመደቡት ፖሊሶች ግን ፦ጭካኔ በተሞላበት መንገድ ሲደበድቡት የነበረውን ግለሰብ እንዲተውት ከህዝብ ለተሰነዘረባቸው ጩኸት የሰጡት ምላሽ ጥይት መሆኑ ብዙዎችን አሳዝኗል።

ከሰልፉ ስፍራ ቃለ-ምልልስ የሰጡት ግለሰብ እንደጠቆሙት ፤ ፖሊሶቹ ከብዛታቸውና ከትጥቃቸው በተጨማሪ  ከመጀመሪያ ጀምሮ  ሲያደርጉት የነበረው እንቅስቃሴ ሁሉ፤ ሆነ ብለው እርምጃ ለመውሰድ ታዘውና ተዘጋጅተውበት የመጡ ይመስሉ ነበር ።

ቢላል እንዳለው፤ፖሊሶች  የወሰዱት ጭካኔ የተሞላበት  እርምጃ፤ በአሰሳ ከተማ ነዋሪዎች ላይ ጥልቅ የሀዘን ስሜት ፈጥሯል።

በግጭቱ የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ወገኖች ወደ አሶሳ ህክምና ማዕከል መወሰዳቸው ታውቋል።

በትናንትናው ዕለት በ አንዋር መስጊድና በ አወሊያ፣ በስልጤ ዞንና በሌሎች የክልል ከተሞች በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ከጁምአ ሶላት በሁዋላ ተመሣሳይ የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል።

በተለይ በትልቁ አንዋር መስጊድ በተካሄደው ሰልፍ ላይ  የተገኙ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች  ፦”ድምፃችን ይሰማ!” በማለት አምርረው ሲጮኹ እና በስፍራዎቹ ተሰቅለው ይታዩ የነበሩ የመጂሊስ አመራሮችን ፎቶግራፎች በጥርሳቸው ጭምር እየበጫጨቁ በመጣልና በመረጋገጥ ቁጣቸውን ሲገልጹ ታይተዋል።

በዋነኝነት፦“ባልመረጥነውና በማይወክለን መጂሊስ አንመራም! መንግስት የ አህባሽን አስተምህሮ በሀይል ለመጫን ከሚያደርገው ሙከራ ይታቀበ!” የሚሉ ጥያቄዎችን በማንገብ የ ኢትዮጵያ ሙስሊሞች የተቃውሞ ሰልፎችን ማድረግ ከጀመሩ ወራቶች ቢቆጠሩም፤ መንግስት ለጥያቄያቸው ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ተቃውሞው እየተባባሰ አስፈሪ ደረጃ ላይ ደርሷል።

ውጥረቱ እንዴት ይፈታ ይሆን ? የሚለው ጥያቄ የኢትዮጵያውያን  ዋነኛ መነጋገሪያ ከመሆኑም ባሻገር የዓለማቀፍ ብዙሀን መገናኛን ትኩረትም ስቧል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በአዲስ አበባም ሆነ በሌሎች አካባቢዎች ሙስሊሞች ተቃውሞ እያሰሙ እንደሆነ ተደርጎ በተለያዩ መገናኛ ብዙሀን መዘገቡ ትክክል አይደለም፣ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ተደርገዋል በማለት መረጃዎችን እያዛቡ የሚያቀርቡት መንግስትን በሀይል ለመገልበጥ የወሰኑ ጥቂት አክራሪ ሰለፊያዎች ናቸው ብሎአል። ሚኒስቴሩ አያይዞም፣ መንግስት ከህዝቡ ጋር በጋራ በመሆን ሽብርተኝነትን ለመዋጋት የጀመረውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ ይቀጥልበታል፣ በአገሪቱ ውስጥ ሰላም እና መረጋጋት እንዲፈጠርም አስፈላጊውን ሁሉ እርምጃ ይወስዳል ብሎአል። ይህ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር መግለጫ መንግስት ሙስሊሙ ያነሳውን ተቃውሞ በሀይል ለመጨፍለቅ መወሰኑን የሚያሳይ ብቻ ሳይሆን መጪዎቹ ጊዜያት የደም ጊዜያት ሊሆኑ እንደሚችሉ አመላካች ነው።

አቶ መለስ ሰሞኑን በአርሲ አካባቢ የአልቃይዳ ኔትወርክ ተገኝቷል ብለው መናገራቸው ይታወሳል። በርካታ ሙስሊሞች ግን

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide