በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ ያልተጠበቀ አደጋ ሊደርስ እንደሚችል ሰራተኞች አስጠነቀቁ

ሚያዚያ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም   ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለፉት ሳምንታት ሸኚዎች ወደ ውስጥ ገብተው ዘመዶቻቸውን እንዳይሸኙ ክልከላ መጣሉን በተደጋጋሚ ስንዘግብ ቆይተናል። የአየር  መንገድ ሰራተኞች እንደሚሉት መንግስት እግዱን የጣለው የሽብር ጥቃት እንደሚፈጸም መረጃው ስለደረሰው ነው። ይሁን እንጅ አንዳንድ ወገኖች መንግስት ወደ ሳውዳ አረብያ  የሚጎርፉትን ወጣት ሴቶች ህዝቡ እንዳያያቸው የተጠቀመበት ስልት ነው ሲሉ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ወጣት ሴቶች ...

Read More »

በደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ባስነሱት ተቃውሞ በርካቶች ታስረዋል

ሚያዚያ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም   ኢሳት ዜና:-ተቃውሞው ምግብን ሰበብ አድርጎ እንደተፈጠረ ቢነገርም፣ የተማሪዎች ግን ከዚህ የዘለለ ነው ተብሎአል። ትናንት ከሰአት በሁዋላ የተነሳው ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን ተቃውሞው ከዞኑ ፖሊስ አቅም በላይ በመሆኑ የፌደራል ፖሊስ ጣልቃ ገብቷል። ተማሪዎች በፖሊሶች ላይ የሚያወርዱት ድንጋይ  መምህራኑ ከግቢያቸው እንዳይወጡ አድርጓቸው እንደነበር የደረሰን መረጃ ያመለክታል። የፌደራል ፖሊስ ግቢውን ለመቆጣጠር መሳሪያዎችን መተኮሱን አድማ ...

Read More »

አንድነት ፓርቲ በትናንትናው እለት በአርባ ምንጭ የተሳካ ስብሰባ አካሄደ

ሚያዚያ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም   ኢሳት ዜና:-አንድነት ለዲሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ ባለፈው ቅዳሜ በወላይታ ሶዶ የተሳካ ስብሰባ ከካሄደ በሁዋላ በማግስቱ ደግሞ በአርባ ምንጭ  በርካታ ህዝብ በተገኘበት የተሳካ ስብሰባ አካሂዷል። የከተማው መስተዳደር ለፓርቲው ስብሰባ ማካሄጃ ሲቀላ በሚባለው አካባቢ በሚገኝ የፖሊስ አዳራሽ ቢፈቅድም፣ አዳራሹ ለተሰብሳቢው በማይመች መልኩ ማዘጋጀቱን ለማወቅ ተችሎአል። በስብሰባው ላይ በርካታ ህዝብ እንደሚገኝ እየታወቀ ሲመጣ፣ የወረዳው ባለስልጣናት ...

Read More »

ሁለት የመካከለኛው ምሥራቅ ዜጎች በ24 ሰዓት ውስጥ ከአገር እንዲወጡ መወሰኑ ውሸት ነው ተባለ

ሚያዚያ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም   ኢሳት ዜና:-በታላቁ የአንዋር መስጊድ  ለፀሎት በተሰበሰቡ ምዕመናን መካከል በመግባት ህገ-ወጥ  ቅስቀሳ ሲያደርጉ እና  በህገ -ወጥ መንገድ ወረቀት ሲበትኑ የተገኙ ሁለት የመካከለኛው ምሥራቅ ዜጎች በ 24  ሰ ዓት ውስጥ ከ አገር እንዲወጡ ተወሰነ በማለት የ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ትናንት ያስተላለፈውን ዘገባ የ አዲስ አበባ ነዋሪዎች ፦”የተለመደ ነጭ ውሸት” ሲሉ አጣጣሉት። በጉዳዩ ዙሪያ የ ኢሳት ...

Read More »

ሰማያዊ ፓርቲ በምርጫ ቦርድ እየተጉላላ ነው

ሚያዚያ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም   ኢሳት ዜና:-በወጣቶች እና በምሁራን  የተቋቋመው እና በአጭር ጊዜ ውስጥ እጅግ በርካታ አባላትን ምፍራቱ የሚነገርለት ሰማያዊ ፓርቲ ፤ከምርጫ ቦርድ ህጋዊ ፈቃድ ማግኘት እንዳልቻለ ገለጸ። ሰማያዊ ፓርቲ  የተቋቋመው የዛሬ አምስት ወር አካባቢ ቢሆንም፤ አባላት ከማፍራት ጀምሮ በ አጭር ጊዜ ውስጥ እያደረጋቸው ያሉት እንቅስቃሴዎች  በመንግስት ዘንድ  ስጋት ማሳደር ሳይጀምሩ እንዳልቀሩ አንድ የፓርቲው ከፍተኛ አመራር ጠቁመዋል። ...

Read More »

በወላይታ ሶዶ አንድነት ፓርቲ በወከባ ውስጥ ሆኖ ስብሰባውን አካሄደ

ሚያዚያ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም   ኢሳት ዜና:-አንድነት ፓርቲ ዛሬ ሚያዚያ 26፣ 2004 ዓም በወላይታ ሶዶ ከተማ ህዝባዊ ስብሰባ መጥራቱን ተከትሎ  የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች በሰብሳቢዎቹና በተሰብሳቢዎቹ ላይ ከፍተኛ ወከባ አድርሰዋል። በስብሰባው ላይ ለመገኘት ከአዲስ አበባ ወደ ወላይታ ያመሩት ኢ/ር ዘለቀ ረዲ፣ ዶ/ር ሀይሉ አርአያና አቶ ዳንኤል ሺበሺ ወደ ከተማዋ ሲገቡ መኪናቸው ጉዳት እንደደረሰባት፣ እንዲሁም ደጋፊዎቻቸውና የከተማዋ ነዋሪዎች ወደ ...

Read More »

በደሴ ከተማ ከጁምአ ጸሎት በሁዋላ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ

ሚያዚያ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም   ኢሳት ዜና:-በደሴ ከተማ  በፉርቃን መስጊድ ለአምስተኛ ጊዜ የተካሄደው ይህ የተቃውሞ ሰልፍ  በድምቀቱም ሆነ  በህዝብ ብዛት  ባለፉት አራት ሳምንታት ከተካሄዱት ሰልፎች የበለጠ  ሆኖ ታይቷል። የሰልፉ አስተባባሪዎች መንግስት  በብዙሀን ሙስሊሞች ላይ ያነጣጠረ የማስጠንቀቂያ መልዕክት ባስተላለፈበት ጊዜ  የተካሄደው ሰልፍ  ይበልጥ ጠንካራ እና ደማቅ የሆነው፤ ህዝበ-ሙስሊሙ  መንግስት  የቀረበለትን የመብት ጥያቄ  በሀይል ለመፍታት በያዘው መንገድ   ላይ  ይበልጥ ...

Read More »

የአፍሪካ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን በኢትዮጵያ የሚፈጸመውን የሰብአዊ መብት ጥሰት አወገዘ

ሚያዚያ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም   ኢሳት ዜና:-ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም ባልታየ ሁኔታ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈጸሙትን የሰብአዊ መብት ጥሰቶች አንድ በአንድ በመዘርዝር፣ የመለስ መንግስት አፋጣኝ የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቋል። የአፍሪካ የሰብአዊ እና የህዝቦች መብቶች ኮሚሽን በጋምቢያ ዋና ከተማ በባንጁል ከኤፕሪል 18 እስከ ሜይ 2 ባደረገው ስብሰባ ላይ ባወጣው የአቋም መግለጫ በኢትዮጵያ ውስጥ እስረኞች ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ በማእከላዊ እስር ቤት ...

Read More »

በኢትዮጵያ የውጭ ጋዜጠኞች ማህበር በአመቱ ውስጥ የተሻለ ስራ የሰሩ ጋዜጠኞችን ሸለመ

  ሚያዚያ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም   ኢሳት ዜና:-ማህበሩ ሚያዚያ 23 በአልያንስ ፍራንሴስ ባካሄደው የሽልማት ስነስርአት ላይ የብሉምበርጉ ጋዜጠኛ ዊሊያም ዳቪድ ሰን የኢትዮጵያ ሚዲያ ብዙ ጊዜ የሚተች ቢሆንም፣ የሚቀርቡ አንዳንድ ዘገባዎች፣ መዝናኛዎችና መረጃዎች ፣ ተስፋ የሚሰጡ ናቸው ሲሉ በስነስርአቱ ላይ ተናግረዋል። በእንግሊዝኛ የፎርቹኗ ማህሌት መስፍን አሸናፊ ስትሆን ማህሌት በሰሜን ወሎ  የተገኘን ማእድን ተከትሎ የተፈጠረውን ውዝግብ ሚዛናዊ በሆነ መንገድ ...

Read More »

በአቶ መለስ መንግስትና በኢትዮጵያ ሙስሊሞች መካከል የተፈጠረው ውጥረት አደገኛ ደረጃ ላይ ደርሷል

ሚያዚያ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም   ኢሳት ዜና:-የብዙሀኑ ሙስሊም አስተባባሪ ኮሚቴ፤ “በሀሰት ፕሮፓገጋንዳ የመብት ጥያቄዎቻችን አይዳፈኑም”  በሚል ርዕስ ባለ 15 ገጽ መግለጫ በበተነበት በትናንትናው ዕለት፤ መንግስት  በፊናው የማስጠንቀቂያ እና የማስፈራሪያ መግለጫ አውጥቷል።  የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ባወጣው በዚሁ ረዥም መግለጫ፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ   በአብዛኛው የሙስሊም ህብረተሰብ ዘንድ እየተነሳ ያለውን ጥያቄና ተቃውሞ፤ በምርጫ 97 ወቅት ተከስቶ ከነበረው ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር ...

Read More »