ሰኔ ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሚኒስትር ዴኤታው ይህን ያሉት ትናንት በጽህፈት ቤታቸው በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ነው። አቶ ሽመልስ በትናንቱ መግለጫቸው ትኩረት ያደረጉባቸው ሁለት ነጥቦች፦ በኦሞ ወንዝ አካባቢ እየተሰራ ያለውን የስኳር ፕሮጀክት አስመልክቶ ከሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እየተሰማ ያለውን ተቃውሞ እና መንግስት በ”ስካይፒ “፣ በ”ጎግል ቶክ” እና በ”ያሁ መሴንጄር” አማካይነት የሚደረጉ ጥሪዎችን ...
Read More »የጸጥታ ሀይሎች በሱዳን መንግስት ተቃዋሚዎች ላይ እርምጃ እየወሰዱ ነው
ሰኔ ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የጸጥታ ሀይሎቹ እርምጃውን የወሰዱት የአልበሽር መንግስት የመንግስትን ወጪን ለመቀነስ የወሰደውን እርምጃ ለመቃወም በወጡ ሰልፈኞች ላይ ነው። ትናንት ከጁመአ ጸሎት በሁዋላ ተቃዋሚዎቹ ህዝቡ መንግስት እንዲለወጥ ይፈልጋል የሚል መፈክሮችን አሰምተዋል። ተመሳሳይ ተቃውሞ በባህሪ አካባቢ ተነስቶ ፖሊሶች ተቆጣጥረውታል። የሱዳን የዩኒቨርሰቲ ተማሪዎች ያነሱት ተቃውሞ በአገሪቱ የሚታየውን የኢኮኖሚ ችግር ይበልጥ ያባብሰዋል ተብሎ ተሰግቷል። ደቡብ ሱዳን ራሱን ከሰሜኑ ...
Read More »በሲዳማ ዞን እየተነሳ ባለው ተቃውሞ የመንግስት እጅ አለበት ተባለ
ሰኔ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአዋሳ ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጡት ለዘመናት ተቻችለው የኖሩ ህዝቦች እንዲጋጩ ለማድረግ የመንግስት ባለስልጣናት ሆን ብለው እየሰሩ ነው። ህዝቡ በኑሮ ውድነቱ፣ በመብት አፈናው እና በተለያዩ አስተዳደራዊ ችግሮች እየተማረረ፣ ከዛሬ ነገ ለውጥ ይመጣል እያለ በሚናፍቅበት በዚህ አስቸጋሪና አስፈሪ ወቅት፣ መንግስት የዋሳ ከተማን አስተዳደር እንደገና የህዝብ አጀንዳ አድርጎ በማቅረብ ግጭት እንዲነሳ መጣሩ ነዋሪዎችን አስቆጥቷል። የዞኑ ባለስልጣናት ...
Read More »ሸብርተኝነትን ይዋጋል የተባለ መታወቂያ በብሔራዊ ደረጃ ሊዘጋጅ ነው
ሰኔ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሸብርና ወንጀልን ለመከላከል ይረዳል የተባለ በአገር አቀፍ ደረጃ ብሔራዊ የመታወቂያ ካርድ ለመስጠት የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ ትናንት ለፓርላማ ቀረበ፡፡ በፍትህ ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ በሚኒስትሮች ም/ቤት ጸድቆ ለፓርላማ የቀረበው ረቂቅ ሕግ በአገር አቀፍ ደረጃ አንድ ወጥ የሆነ፣የራሱ ሚሲጢራዊ ኮድ ያለው መታወቂያ በብሔራዊ ደረጃ ማዘጋጀት ያስፈለገው ሸብርና ወንጀልን ለመከላከልና ለምርመራ ተግባራት፣ለብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ለግብር አከፋፈል፣ለፋይናንስ ...
Read More »የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የጋዜጠኛና መምህርት ርእዮት አለሙን አቤቱታ አደመጠ
ሰኔ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዛሬ ረፋዱ ላይ የመሀል ዳኛው አቶ ዳኘ መላኩ፣ የቀኝ ዳኛው በላቸው አንሺሾና ስማቸው ያልተገለጠው ግራ ዳኛው በመሩት ችሎት ላይ የርእዮት ጠበቃ የሆኑት አቶ ሞላ ዘገየ እና አቃቢ ህጉ አቶ ብርሀኑ ወንድማገኝ ተከራክረዋል። የርእዮት አባት የሆኑት አቶ አለሙ ገበቦ በረዳት ጠበቃነት ተሳትፈዋል። ጠበቃ ሞላ ዘገየ ደንበኛቸው ርእዮት አለሙ በህገመንግስቱ አንቀጽ 29 በተሰጣት መብት ...
Read More »ለእስር ቤቶች ግንባታ የሚመደበው በጀት በየዓመቱ ከፍተኛ ጭማሪ እያሳየ ነው
ሰኔ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ መንግስት ለእስር ቤቶች ግንባታ በየዓመቱ የሚመድበው ባጀት በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መምጣቱን መረጃዎች ጠቆሙ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ከ2003 እስከ 2005 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት መንግስት ለፌዴራል እስር ቤቶች ግንባታ ብቻ በድምሩ 415 ሚሊየን 153 ሺ100 ብር መድቧል፡፡ በ2003 በጀት ዓመት 13 ሚሊየን ለግንባታ( ካፒታል ወጪ) የመደበ ሲሆን ይህ ቁጥር በ2004 ዓ.ም ወደ 193 ...
Read More »የፖለቲካ ግብ ያለውን ማስታወቂያ የሚከለክለው ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ
ሰኔ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፖለቲካ ፓርቲዎች ( ድርጅቶች ) የፖለቲካ ግብ ያለው ማስታወቂያ እንዳያሰራጩ የሚከለክለው ረቂቅ አዋጅ በብሮድካስት ባለሥልጣን አርቃቂነት በሚኒስትሮች ም/ቤት ጸድቆ ትናንት ለፓርላማ ቀረበ፡፡ ረቂቅ አዋጁ የፖለቲካ ድርጅቶች የሚያደርጉትን የአድራሻ ለውጥ፣የስብሰባ ጥሪ እና መሰል ማስታወቂያ እንደተጠበቀ ሆኖ የፖለቲካ ግብ ያለው ማስታወቂያን በመገናኛ ብዙሃን እንዳይተላለፍ ይከለክላል፡፡ አዲሱ ህግ የፖለቲካ ድርጅቶችና የሃይማኖት ተቋማት የመገናኛ ብዙሃንን ማስታወቂያዎች ...
Read More »ዶ/ር ኢሌኒ ገብረመድህን ከሀላፊነታቸው መልቀቃቸውን አስታወቁ
ሰኔ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዶ/ር ኢሌኒ ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እርሳቸውና አብረዋቸው ሢሰሩ የነበሩት የሥራ ባልደረቦቻቸው በፈቃዳቸው ሀላፊነታቸውን እንደለቀቁ አስታውቀዋል። ሀላፊነታቸውን የለቀቁትም፤ ቦታውን በዘርፉ ልምድ ላካበቱ ሙያተኞች ለመልቀቅ በመፈለጋቸው እንደሆነ ተናግረዋል። ዶ/ር ኢሌኒ ሥራ መልቀቃቸውን ፦”የመተካካት ሂደት ነው” ቢሉትም፤ ሁኔታው በገዥዎቹ መንደር ሳይቀር ድንጋጤ መፍጠሩን ጋዜጣዊ መግለጫውን የተከታተሉ ጋዜጠኞች ጠቁመዋል። እንደ ምንጮች መረጃ ፤ሁኔታው ለብዙዎች እንቆቅልሽ ...
Read More »በሲዳማ ዞን ከፍተኛ የሆነ የዘር ግጭት ሊነሳ ይችላል በማለት የአካባቢው ሰው በስጋት ወድቋል
ሰኔ አስራ አራት ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የአዋሳ ዘጋቢዎች እንደገለጡት ትናንት በአለታ ጩኮ የተነሳውን ተቃውሞ ተክትሎ በዛሬው እለትም ከአዋሳ በ 10 ኪሜ ርቅት ላይ በምትገኘው ቱላ ከተማ ውስጥ ተማሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጋቸውንና መኪኖችን አግተው ለመስክ ስራ የሄዱ ሰራተኞች ስራ ሳይሰሩ እንዲመለሱ ማድረጋቸው ታወቋል። ተማሪዎች በየመኪኖች ውስጥ እየገቡ የወላይታ ተወላጆችን እንዲወርዱ ሲጠይቁ እንደነበር የገለጠው ዘጋቢያችን ትናንት ማታ 2 የወላይታ ተወላጆች ...
Read More »የእነ አቶ አንዱአለም አራጌ የፍርድ ውሳኔ ተራዘመ
ሰኔ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በእነ አቶ አንዱአለም አራጌ የክስ መዝገብ በአሸባሪነት ወንጀል ከ10 ወራት በፊት ከተከሰሱት 24 የተቃዋሚ ፓርቲ የአመራር አባላት ፣ ጋዜጠኞችና የሲቪክ ማህበረሰብ አባላት 8 ተከሳሾች ዛሬ የመጨረሻውን ውሳኔ ለመስማት በፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ቢቀርቡም በድጋሜ ቀጥሮ ወደ እስር ቤት እንዲመለሱ ተደርጓል። ዛሬ ከጠዋቱ 3 ሰአት ከ35 ደቂቃ ላይ በችሎቱ ...
Read More »