አቶ ጁኔይዲን ሳዶ የለውጥ ሠራዊት ግንባታ በሚፈለገው ደረጃና ፍጥነት እየተከናወነ አለመሆኑን ገለጡ

ሰኔ ፲፱ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሚኒስትሩ ዛሬ የመ/ቤታቸውን የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለፓርላማው ባቀረቡበት መድረክ ላይ ከም/ቤቱ አባላት ለተነሱት ጥያቄዎች በሰጡት ምላሸ በአመለካከት እና በክህሎት ችግሮች ምክንያት ዕቅዱ በሚፈለገው ደረጃ እየተፈጸመ አለመሆኑን አምነዋል፡፡ ሚኒስትሩ በሪፖርታቸው ግልጽና ተጠያቂነት እንዲሁም መልካም አስተዳደርን በየደረጃው የሰፈነበት ሲቪል ሰርቪስ ለመፍጠር በየተቋማቱ የለውጥ ሠራዊት መገንባት እንደመሳሪያ በመውሰድ እንቅስቃሴ ተደርጓል፡፡ በእስካሁኑም እንቅስቃሴ በየመድረኩ የተፈጠሩ ብዥታዎችን ...

Read More »

የዶክተር ነጋሶን ጤንነት ለመታደግ 8 ሺህ ዩሮ ያስፈልጋል ተባለ

ሰኔ ፲፱ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የቀድሞው  የአገሪቱ ፕሬዝዳንት እና የአሁኑ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ  እግራቸው ላይ በተከሰተ የደም ዝውውር ችግር በአደገኛ የጤና ችግር ላይ እንደሚገኙ ተገለፀ። የዶክተሮችን የምርምር ውጤት በመጥቀስ ፍኖተ-ነፃነት እንደዘገበው፤ ዶክተር ነጋሶ በአስቸኳይ ኦፕራሲዮን ካልተደረጉ እግራቸው ሊቆረጥ ይችላል። በመሆኑም የ ኢትዮጵያ ህዝብ የዶክተር ነጋሶን ጤንነት ይታደግ ዘንድ አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ህዝባዊ ጥሪ ...

Read More »

በኢትዮጵያ፤ የአይ.ኤም.ኤፍ ዌብሳይት ታገደ

ሰኔ ፲፱ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ የአይ.ኤም.ኤፍ እና የኢኮኖሚስት ዌብ ሳይቶች መታገዳቸውን የኢሳት ምንጮች ገለጡ። ምንጮቻችን እንደጠቆሙት ካለፉት ሁለት  ቀናት ወዲህ የገንዘብ ተቋሙን እና የ ኢኮኖሚስት  ድረ-ገፆችን ለማየት አልቻሉም። ዓለማቀፉ የገንዘብ ተቋም( አይ.ኤም.ኤፍ) ሰሞኑን ኢት ዮጵያን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤ የመንግስት ባለስልጣናት ኢኮኖሚው 11 በመቶ እንዳደገ የሚሰጡት መግለጫ ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው ነው ከማለቱም ባሻገር በተያዘው ዓመት የ ኢት ...

Read More »

በአዋሳ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ጉብኝታቸውን ትተው ተመለሱ

ሰኔ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለፈው ሳምንት ከአዋሳ እና ከሲዳማ ዞን ጋር በተያያዘ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ በካናዳ ትምህርታዊ ጉብኝት ሲያደርጉ የነበሩት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ጉብኝታቸውን ትተው በመመለስ ትናንት መግለጫ ሰጥተዋል። አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በአዋሳ ጉዳይ ለተነሳው ተቃውሞና ለጠፋው የሰው ህይወት ችግሩን የቀሰቀሱትን ለፍርድ እንደሚያቀርቡ ለክልሉ ራዲዮ ተናግረዋል። አቶ ሽፈራው የአዋሳ ጉዳይ በሀሳብ ደረጃ ተነሳ እንጅ ውሳኔ ያልተሰጠበት ...

Read More »

አቶ በረከት ስምኦን መንግስታቸው ስካይፒንና የኢንተርኔት አገልግሎቶችን ለመዘጋት መወሰኑን አመኑ

ሰኔ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የመንግስት ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ሽመልስ ከማል መንግስት ስካይፕንና የኢንተርኔት አገልግሎትን ለመዝጋት ወስኗል በማለት የሚገልጡት የምእራባዊያን ጋዜጠኞች ናቸው በማለት መግለጫ በሰጡ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አቶ በረከት ስምኦን ኢንተርኔት ለቴሌኮም አገልግሎት የመጠቀም ተግባር አገሪቱን ከፍተኛ ገቢ እያሳጣት በመምጣቱ ስካይፒን ጨምሮ ሌሎች የኢንተርኔት የቴሌኮም አገልግሎቶችን መንግስት ለመዝጋት ወስኗል ብለዋል። የመንግሥት የኮምኒኬሸን ሚኒስትር የሆኑት ...

Read More »

መንግስት፤ የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅን ከአልሸባብ ጋር በማገናኘት ለመወንጀል የሸረበው ድራማ ተጋለጠ

ሰኔ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአቶ መለስ መንግስት ባለሟሎች  ማንንም ሊያሳምን በማይችል ደረጃ ፍትህ ጋዜጣን ከአልሸባብ ጋር ግንኙነት እንዳለው በማስመሰል የፈበረኩትን አስቂኝ ድራማ ያጋለጠው፤  የጋዜጣው ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ነው። “ፍትህን እና አልሸባብን  ምን አገናኛቸው?” በሚል ርዕስ ጋዜጠኛ ተመስገን ባስነበበው ጽሁፍ፤ አዲስ ዘመንና በተመሳሳይ መስመር የተሰለፉት እነ አይጋ ፎረም፣ዋልታ እና ዛሚ፤ በፍትህ ጋዜጣ ላይ “አርማጌዶን” ወይም ...

Read More »

የሕወሃት መንግስት በእርዳታ ያገኘውን ምግብ ኤክስፖርት ማድረግ ሊጀምር ነው

ሰኔ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የሕወሃት አስተዳደር ከበጎ አድራጊ ድርጅቶችና መንግስታት በረሃብ ለተጎዳው ወገናችን የሚላከውን የእርዳታ እሕል፤ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ድርጅት በተሰኘው ተቋም በኩል በአለም ዓቀፍ ገበያ አውጥቶ ለመሸጥ እንዳቀደ ሬውተር የተሰኘው የዜና ወኪል ዘገበ። በቅርቡ ሃላፊነቴን ለሌላ ሰው አስረክባለሁ ያሉት የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር እሌኒ ገብረ መድሕን፤ በዚሁ ጉዳይ ዙሪያ ላነጋገራቸው ለሬውተር ...

Read More »

በአዋሳ ከተማ ያለው ውጥረት እንደቀጠለ ነው

ሰኔ ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአዋሳ ከተማን እጣ ፋንታ እና የሲዳማ ዞንን የክልል ጥያቄ ተከትሎ በሲዳማ ዞን ተወላጅ የምክር ቤት አባላት በአንድ ጎን እና የፌደራሉና የሌሎች የምክር ቤት አባላት በሌላ ጎን ሆነው  የጀመሩት ውዝግብ እየተካረረ መምጣቱን ተከትሎ በአዋሳ የሚታየው ከፍተኛ ውጥረት አለመቀነሱን ዘጋቢያችን ገልጧል። በዛሬው እለት ወጣቶች ሰላማዊ ሰልፍ ያደርጋሉ በሚል ስጋት የፌደራል ልዩ ሀይል አድማ በታኝ ...

Read More »

ወደ ዓረብ አገራት የሚሄዱ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር ከሶስት እጥፍ በላይ አሻቀበ

ሰኔ ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በመጠናቀቅ ላይ በሚገኘው በ2004 በጀት  አመት 10 ወራት ውስጥ ብቻ 140 ሺ ዜጎች ሥራ ፍለጋ ወደ ተለያዩ የአረብ ሀገራት መጓዛቸውን  ይህ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር  በ329 በመቶ ማሻቀቡን አንድ ጥናት አመለከተ፡፡ በትላንትናው ዕለት በጠ/ሚኒስትሩ ቢሮ ይፋ የሆነው ይህው ጥናት እንደሚያመለክተው  በህገወጥ መንገድ ከአገር የሚወጡት ዜጎች ቁጥር በአስደንጋጭ መልኩ ማሻቀቡን የጠቆመ ...

Read More »

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሠራተኛው ላይ የ 7 አመት ከ 8 ወራት እስራት ተበየነ

ሰኔ ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፍርድ ቤቱ አብዱራሂም ሺሁ ሀሰን በተሰኘው የመንግስታቱ ድርጅት የሴኩሪቲ ኦፊሰር ላይ ይህን ውሳኔ ያሳለፈው፦ “ለኦጋዴ ብሄራዊ ነፃነት ግንባር መረጃዎችን  አስተላልፏል” በማለት በ ፌዴራል አቃቤ ህግ  በተመሰረተበት ክስ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ እንደሆነ ገልጿል። አብዱራሂም  የሽብርተኝነት ክስ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ፤  ዓለማቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማት፦  የኢትዮጵያ መንግስት  ተዓማኒነት የሌለውን ክሱን ውድቅ በማድረግ የመንግስታቱ ድርጅት የደህንነት ...

Read More »