የጸጥታ ሀይሎች በሱዳን መንግስት ተቃዋሚዎች ላይ እርምጃ እየወሰዱ ነው

ሰኔ ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የጸጥታ ሀይሎቹ እርምጃውን የወሰዱት የአልበሽር መንግስት የመንግስትን ወጪን ለመቀነስ የወሰደውን እርምጃ ለመቃወም በወጡ ሰልፈኞች ላይ ነው።

ትናንት ከጁመአ ጸሎት በሁዋላ ተቃዋሚዎቹ ህዝቡ መንግስት እንዲለወጥ ይፈልጋል የሚል መፈክሮችን አሰምተዋል። ተመሳሳይ ተቃውሞ በባህሪ አካባቢ ተነስቶ ፖሊሶች ተቆጣጥረውታል።

የሱዳን የዩኒቨርሰቲ ተማሪዎች ያነሱት ተቃውሞ በአገሪቱ የሚታየውን የኢኮኖሚ ችግር ይበልጥ ያባብሰዋል ተብሎ ተሰግቷል። ደቡብ ሱዳን ራሱን ከሰሜኑ ሱዳን ከለየ በሁዋላ በሰሜን ሱዳን የሚታየው የኢኮኖሚ ችግር እየከፋ መጥቷል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide