በመንግስት እና በኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጭ ግንባር መካከል ድርድር ቢጀመርም፡ ጦርነቱም እንደ ቀጠለ ነው

መስከረም ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በመንግስት እና በኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጭ ግንባር መካከል  ድርድር ቢጀመርም፡ ጦርነቱም እንደ ቀጠለ ነው ሲሉ የግንባሩ ቃል አቀባይ ገለጡ የኦብነግ ቃል አቀባይ  አቶ ሀሰን አብዱላሂ  በኬንያ አደራዳሪነት ተከታታይ የሆኑ ድርድሮችን ለማካሄድ ስምምነት ላይ ቢደረስም ፣ ጦርነቱ ግን አሁንም እንደቀጠለ መሆኑን ተናግረዋል። “እናንተ ከመንግስት ጋር ድርድር ውስጥ የገባችሁት ሀይላችሁ እየተዳከመ በመምጣቱ ነውን?” በሚል ...

Read More »

በደቡብ ክልል የተለያዩ ከተሞች ነዋሪዎች ሲሉ ተናገሩ

መስከረም ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ከደቡብ ክልል ከወላይታ ብሄረሰብ የተገኙ መሆናቸው በክልሉ ነዋሪዎች ዘንድ ምን ስሜት ፈጠረ የሚለውን ለማወቅ ኢሳት ከተለያዩ የክልሉ ነዋሪዎች ጋር  ቃለምልልስ አድርጓል። አንዳንድ ነዋሪዎች የእርሳቸው መመረጥ ደስታ የፈጠረላቸው መሆኑን ቢናገሩም፤ አብዛኞቹ ግን ሹመቱ የይስሙላ በመሆኑ ምንም ስሜት እንዳልሰጣቸው ይናገራሉ። አቶ ኦታራ ኦሼ የጋሞጎፋ ዞን ተወላጅ ናቸው። የአቶ ሀይለማርያም ሹመት ” ...

Read More »

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ኢሳት ወደ ኢትዮጵያ የሙከራ ስርጭት ጀመረ

መስከረም ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በገዢው ፓርቲ አፈና ከአንድ አመት በላይ ለሚሆን ጊዜ ታፍኖ ቆየው ኢሳት ወደ ኢትዮጵያ የሚያስተላልፈውን የሙከራ ስርጭት  ጀምሯል። ከኒው ሆርን ቴሌቪዥን የአየር ስርጭት በመግዛት በሚቀጥሉት ቀናት ሙሉ ስርጭቱን የሚጀምረው ኢሳት፣ በቅርቡ ተጨማሪ የራሱ ሙሉ የስርጭት ጊዜ ይኖረዋል። አዲሱ ስርጭት በኤ ቢ 7 በ7 ዲግሪ ዌስት ላይ በ 10815 ሜጋ ሀርዝ፣ በ27 ሺ 500 ...

Read More »

የደመራ በአል በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ ተከበረ

መስከረም ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከምታከብራቸው ታላላቅ ሀይማኖታዊ በአላት መካከል አንዱ የሆነው የደመራ በአል በዛሬው እለት በመላ አገሪቱ ተከብሮአል። የደመራ በአል  ንግስት ኢሌኒ እየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበትን መስቀል ለመፈለግ የተጠቀመችበትን ደመራ እና የእጣን ጭስ ለመዘከር የሚደረግ ሀይማኖታዊ በአል ነው። የቤተክርስቲያኑዋ መጽሀፍት እንደሚያመለክቱት ግማደ መስቀሉ በአጼ ዳዊትና በልጃቸው ባአጼ ዘርአያቆብ በአስራ አምስተኛም ምእተ አመት መግቢያ ላይ ...

Read More »

በደቡብ ክልል ” መለስ ዜናዊ እንኳን ሞተ” ብለው ተናግረዋል የተባሉ 80 ሰዎች ታሰሩ

መስከረም ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በደቡብ ኦሞ ዞን በደቡብ አሪ ወረዳ የሚገኙ አርሶአደሮች፣ ” መለስ ዜናዊ እንኳንም ሞተ፣ አናዝንም” በማለት ሲናገሩ ተሰምተዋል በሚል ነው የወረዳው አቃቢ ህግ ክስ ያቀረበባቸው። የክስ መዝገቡ እንደሚያመለክተው አርሶ አደሮቹ በኢፌዲሪ ወንጀል ህግ አንቀጽ 4 /86 ሀ ላይ የተደነገገውን ተላልፈዋ ል። በመዝገብ ቁጥር 4103/30/2004 ፣ በ ቀን ጻጉሜ 1፣ 2004 በተጻፈው የክስ ቻርጅ ...

Read More »

የኦሮሚያ ቴሌቪዥን በኢቲቪ ምክንያት ከዓረብ ሳተላይት ተባረረ

መስከረም ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኦሮምኛ ቋንቋ የሚተላለፉ ፕሮግራሞችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማሰራጨት ውል ገብቶ ሥራ የጀመረው በኦሮሚያ ክልል መንግስት የሚተዳደረው የኦሮሚያ ቴሌቪዥን የኢትዮጽያ ቴሌቪዥንን(ኢቲቪ) ፕሮግራሞች በአማርኛ ቋንቋ ማስተላለፍ ከመጀመሩ ጋር ተያይዞ ከውል ውጪ ተንቀሳቅሰሃል በሚል ከዓረብ ሳት መባረሩ ተጠቆመ፡፡ ቀደም ብሎ ከዓረብ ሳት ጋር ውል የገቡ ጣቢያዎችን ጃም በማድረግ ወይም በማፈን ክስ ቀርቦበት ከዓረብ ሳት የተባረረው ...

Read More »

የኦህዴድ ካድሬዎች የአቶ ሀይለማርያምን ሹመት በመቃወማቸው በኦነግነት እየተከሰሱ ነው

መስከረም ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለኢሳት የደረሱት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የኦሮሞ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ካድሬዎች፣ ኦህዴድ ተገቢውን የስልጣን ቦታ አለገኘም በማለት ተቃውሞ ማሰማታቸውን መቀጠላቸውን ተከትሎ በርካታ ካድሬዎች በኦነግነት እየተወነጀሉ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል። በከፍተኛ ስልጣን ላይ የሚገኙት የኦህዴድ መሪዎች ሹመቱን ከመቀበል ውጭ ሌላ አማራጭ የለም በማለት አቋማቸውን ግልጽ በማድረግ ካድሬዎቻቸውን ለማሳመን ጥረት ቢያደርጉም፣ በመካከለኛ ደረጃ የሚገኙ እና ተራ አባላቱ ...

Read More »

የኢትዮጵያ መንግስት ከቻይና ባንክ ጋር የ500 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ፈረመ

መስከረም ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን በቻይ መንግስት ከተያዘው የቻይና የልማት ባንክ የ500 ሚሊዮን ዶላር ወይም የ8 ቢሊዮን ብር ብድር ማግኘቱ ታውቋል። ገንዘቡ የሚውለው ሁለት የስኳር ፋብሪካዎችን ለመገንባት መሆኑ ታውቋል። ለተመሳሳይ ፕሮጀክት መንግስት 394 ሚሊዮን ዶላር የሚሆን ብድር ከህንድ መንግስት ማግኘቱ ይታወሳል። ቻይና ለኢትዮጵያ መንግስት የሚሰጠው ብድር የወለድ መጠን አልታወቀም። ይሁን እንጅ ከቻይና የሚገኘው እርዳታ ...

Read More »

አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የታዛዥነት እንጅ የአዛዥነት ስብእና የላቸውም ተባለ

መስከረም ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢትዮጵያን ለ 21 ዓመታት የገዙዋት አቶ መለስ ዜናዊ በህመም ምክንያት ከዚህ አለም በሞት ሲለዩ እርሳቸውን የተኩዋቸው አዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ፣  ትሁት፣ ቅንና ደግ ቢሆኑም፣ የህወሀት ባለስልጣናትን ተጋፍተው ለውጥ የሚያመጡ ሰው አለመሆናቸውን እርሳቸውን በቅርብ የሚያውቁና አብረዋቸው የሰሩ ሰው ለኢሳት ተናግረዋል። አቶ ሀይለማርያም ተሿሚዎቻቸውን እንደፈለጉ ለማሽከርከር ለሚፈልጉ የኢህአዴግ ባለስልጣናት የተመቸ ጠባይ ...

Read More »

ደቡብ ጎንደር እስቴ መካነ ኢየሱስ ውስጥ ህዝብ በጅምላ በፖሊስ እየተደበደበ መሆኑን በስፍራው የሚገኘው የኢሳት ወኪል ዘገበ

መስከረም ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የችግሩ መንስዔ በከተማዋ የሚያልፈው የመንገድ ፕሮጀክት በሌላ በኩል በማለፉ ምክንያት ህዝቡ በሰላማዊ ሰልፍ ተቃወሞውን ለማሰማት በመውጣቱ ነው። ለህዝቡ የታውሞ ሰልፍ የመንግስት ተወካዮች ምላሽ እንሰጣለን  ባሉት መሰረት የአካባቢው ነዋሪ  ቀና ምላሽ እየጠበቀ ባለበት ሁኔታ < ምላሽ እንሰጣለን >ያለው መንግስት ያሰማራው ልዩ ሃይል በትናንትናው ዕለት ሰልፈኛውን ህዝብ በጅምላ በቆመጥ ሲደበድብ ውሏል። የፖሊስ አባላቱ መውሰድ ...

Read More »