አቶ መለስ ዜናዊ ሞተውም በከፍተኛ እጀባ እተጠበቁ ነው

መስከረም ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አራት ኪሎ በሚገኘው ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ለተቀበሩት ለሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ለአቶ መለስ ዜናዊ  ልዩ ጥበቃ እየተደረገላቸው መሆኑን ፍኖተ-ነፃነት ዘገበ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይታተም ቢከለከልም  “ኦን ላይን” ጋዜጣ በመሆን  በኢንተርኔት ስርጭቱን የቀጠለው ፍኖተ-ነፃነት እንደዘገበው፤ አቶ መለስ ከተቀበሩ በኋላ ባልተለመደ ሁኔታ የቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን በሮች የተቆለፉ ሲሆን፤ መቃብራቸው በተለየ ኃይል ልዩ ጥበቃ እየተደረገለት ነው፡፡ ከቀብሩ ...

Read More »

የብአዴን አባልነትን ያልተቀበሉ ሠራተኛ “ከተማዋን ለቀህ ጥፋ” ተባሉ

መስከረም ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአማራ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ጐንደር ዞን ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ የአብርሃጅራ ከተማ ውስጥ የብሔረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ አባልነትን ያልተቀበሉ ሠራተኛ ከከተማዋ ለቀው እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው። ነዋሪዎቹ እንደሚሉት፤ የከተማወወ አስተዳደርና የፀጥታ ቢሮ ኃላፊዎች በዜጎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የመብት ጥሰት እየፈፀሙ ነው። የአካባቢው ሹመኞችና የቢሮ ሀላፊዎች ራሳቸውን የተለዩ አድርገው ስለሚቆጥሩ የሠራተኞችንና የነዋሪዎችን  መብቶች በማናለብኝነት እየጣሱ ...

Read More »

እድገት የመብጥ ጥሰት መሸፈኛ ሊሆን አይገባም ተባለ

በሰብአዊ መብት፤ የሲቪልና ፖለቲካ መብቶች ኪሳራ የሚመጣ የምጣኔ ሀብትና የቁጥር እድገት ለህዝብ ጎጂ ነው፤ ሲሉ የሂውመን ራይትስ ወች የአፍሪካ ክፍል ሀላፊ አቶ ዳንኤል በቀለ ተናገሩ። ምርጫ 97ን ተከትሎ ከፖለቲካ መሪዎችና ከፖለቲከኞች ጋር ለሁለት አመታት ታስረው የነበሩት አቶ ዳንኤል በቀለ በኒው ዮርክ ታይምስ ላይ በጻፉት ጽሁፍ፤ ለጋሽ አገሮች ገንዘባቸውን መሪዎች የፖለቲካ ስልጣን እንዲያጋብሱበት ካደረጉ፤ መርዳት የፈለጉትን ህዝብ ይጎዳል ሲሉ ተናግረዋል። የሩዋንዳ፤ ...

Read More »

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቃውሞ በአንዋር መስጊድ ቀጥሎ ዋለ

ለአራት ሳምንታት ተቋርጦ የነበረው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቃውሞ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ቀጥሎ እንደዋለ አንድ የእስልምና እምነት ተከታይ ከስፍራው ለኢሳት ገለጹ። ኢሳት ያነጋገራቸው ሙስሊም እንደተናገሩት ሰሞኑን በፌስቡክና በሌሎችም መገናኛ መንገዶች እነደተነገረው፤ በዛሬው እለት አማኞች በታላቁ አንዋር መስጊድ በግዜ በመገኘት የእለቱን ጸሎት ከጨረሱ በሁዋላ፤ አስቀድሞ በታቀደው መሰረት መጀመሪያ ነጭ መሀረቦችን በማውለብለብ፤ ለጥቆም አላሁዋክበር በማለት፤ ድምጻቸው እንዲሰማ እንዲሁም የታሰሩት የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባለት ...

Read More »

የአማራ ክልል ወጣቶች መሪ ጫካ መግባቱን ገለጸ

የአማራ ክልል ወጣቶች ማኅበር ፕሬዚዳንትና የኢህአዴግ አባል የነበረው ወጣት ዘመነ ካሴ፤ ሥልጣን ላይ ያለውን የኢትዮጵያ መንግሥት ማስወገድ የሚቻለው በኃይል  ነው በማለት ወደ ትግል ቦታ መግባቱን ለኢሳት ገለፀ። በኢህአዴግ አባልነቱና በወጣቶች ማኅበር ፕሬዚዳንትነቱ ቤትና መኪናን ጨምሮ የተለያዩ ጥቅማጥቅሞችን ከሥርዓቱ ሲያገኝ መቆየቱን የገለፀው ወጣት ዘመነ ካሴ፣ በሀገሪቱ በተለይ በወጣቱ ክፍል ላይ እየደረሰ ያለው ችግርና ጉስቁልና እንዲሁም ተስፋ ማጣት፣ ከሥርዓቱ ለመለየትና ሥርዓቱን ለመታገል ...

Read More »

የአቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ጸደቀ

ዛሬ አስቸኳይ ስብሰባ ያደረገው የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ መረጠ። አቶ ደመቀ መኮንንን ደግሞ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የትምህርት ሚኒስትር አድርጎ ሾሟቸዋል። የፓርላማው አንዱ አጀንዳ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ መሾም መሆኑን ተናግረው ፓርላማውን የከፈቱት አፈ ጉባኤ፣ አቶ አባ ዱላ ገመዳ በተናገሩት መሰረት፤ በአቶ ደመቀ መኮንን ጠቋሚነት፤ አቶ ኃይለማርያም ደሣለኝ ጠቅላይ ሚነስትር ተደርገው ...

Read More »

ለዩኒቨርስቲ መምህራን ሊሰጥ የነበረው አገር አቀፍ ስልጠና ተሰረዘ

መስከረም ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የትምህርት ሚኒስቴር በቁጥር 7/ጠ-259/2311/04 በ 10/12/2004  ዓም በጻፈው ደብዳቤ ለዩኒቨርስቲ መምህራን ከመስከረም 10 እስከ 20 ቀን 2005 ዓም የሚቆይ አገራቀፍ ስልጣን ለመስጠት አቅዶ የነበረ ቢሆንም ይህን እቅዱን በመሰረዝ ስልጠናው ከመስከረም 3 እስከ 20 እንዲሆን አዲስ መመሪያ መበተኑን ኢሳት መዘገቡ ይታወሳል። ዩኒቨርስቲው የቪዲዮ ኮንፈረንሱን  ለማዘጋጀት በስድስት ኪሎ  እና በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ አዳራሾችን ቢያዘጋጅም፣ በዩኒቨርስቲው ...

Read More »

በደሴ የፌዴራል ፖሊሶች ሙስሊሞችን በቆመጥ ሲደበድቡ የሚያሳይ ቪዲዮ ይፋ ሆነ

መስከረም ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሙስሊሞቹ በፌዴራል ፖሊሶች ክፉኛ የተደበደቡት፤ <መመራት የምንፈልገው ራሳችን በመረጥነው መጂሊስ ነው!፤ መንግስት በሀይማኖታችን ጣልቃ አይግባብን!>በማለት ህገ-መንግስታዊ ጥያቄ በማንሳታቸው ነው። ቪዲዮውን ለኢሳት ያደረሱ አንድ የደሴ ነዋሪ<በአወሊያ ከተጀመረ ዘጠኝ ወራት ያስቆጠረው የሙስሊሞች መብት የማስከበር እንቅስቃሴ አንድም ጊዜ ከህጋዊና ሰላማዊ ማዕቀፍ አፈንግጦ የታየበት ጊዜ ባይኖርም፤መንግስት ግን ሲፈልግ መሪዎቻችንን ያስራል፤ሲያሻው ይደበድበናል>>ብለዋል። <<ሌላው ቢቀር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ...

Read More »

አቶ መለስ በመጨረሻው የስልጣን እድሜያቸው በፕሮፓጋንዳ ሰራተኞቻቸው ተስፋ ቆርጠው እንደነበር ታወቀ

መስከረም ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት የኢህአዴግ ምንጮች እንደገለጡት ኢህአዴግ በፕሮፖጋንዳው መስክ ለደረሰበት ኪሳራ  አቶ መለስ አቶ በረከትን ተጠያቂ አድርገው ነበር። በአንድ የግንባሩ ስብሰባ ላይ በመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሠራተኞች ብቃት ማነስ የተበሳጩት አቶ መለስ ‹‹እዚህ ተቋም ላይ ከሰበሰብካቸው ሰዎች ይልቅ ያ የግል ጋዜጣ የሚያዘጋጀው ልጅ የበለጠ ኮሚትመንት አለው፣ እሱ የሚሰራውን ያውቃል፣ ያንተ ሰራተኞች የሚሰሩትን አያውቁም›› በማለት አቶ ...

Read More »

የጋዜጠኛ ግሩም ተክለሐይማኖት ደህንነት አደጋ ላይ ነው ተባለ

መስከረም ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአስኳልና ሳተናው ዋና አዘጋጅ የነበረው በየመን አገር በስደት ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ግሩም ተክለሐማኖት  በየመን ፖሊሶች እየተዋከ ነው። ጋዜጠኛው ጳጉሜ 3 ቀን 2004 ዓም ቤቱ በሌሊት በፖሊስ እንደተፈተሸበት ለኢሳት ተናግሯል::    ጋዜጠኛ ግሩም ችግሩን ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን ቢያመለክትም ጽሁፍ መጻፉን እንዲያቆምና ቤት እንዲቀይር ከመጠየቅ ውጭ ችግሩን የሚያቃልል መልስ ሊሰጠው አልቻለም፡። ጋዜጠኛ ግሩም ኢትዮጵያውያን ...

Read More »