አቶ በረከት የኢቲቪና የፕሬስ ድርጅት ሥራ አስኪያጆችን አንስተው ታዛዦቻቸውን ሊሾሙ ነው ተባለ

መስከረም ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኮሙኒኬሽን ሚኒስትሩ አቶ በረከት ስምዖን  የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እና የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ሥራ አስኪያጆችን በማንሳት ለእርሳቸው ታዛዥ የሆኑ ሰዎችን ለማስቀመጥ  እንቅስቃሴ መጀመራቸው ተጠቆመ። በዚህም መሰረት ከደቡብ ክልል ያስመጡትና በኢትዮጵያ ራዲዮ ውስጥ በምክትል ሥራ አስኪያጅነት ሢሰራ የቆየው ሰለሞን ተስፋዬ የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣የ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ምክትል ዋና ...

Read More »

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ የነበሩት ኮበለሉ

መስከረም ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአሁኑ ወቅት በኃላፊነት ላይ ባለው የኩማ አስተዳደር የአዲስአበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የማስታወቂያ ቢሮ ኃላፊ በመሆን ያገለገሉትና ከአንድ ዓመት በፊት በአቅም ማነስ ተተችተው ከኃላፊነታቸው የተነሱት አቶ ከፍያለው አዘዘ ወደ ዩናይትድስቴትስ አሜሪካ ቤተሰባቸውን ይዘው መኮብለላቸው ተሰማ፡፡ አቶ ከፍያለው ከ1997 ዓ.ም ምርጫ አለመግባባት ጋር በተያያዘ በገዥው ፓርቲ ተሹሞ የነበረውን የባለአደራውን የአቶ ብርሃነ ደሬሳ አስተዳደር በግንቦት ...

Read More »

የአሜሪካ መንግስት የአቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ሹመት ታሪካዊ ነው አለ

መስከረም ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፕሬዚዳንት ኦባማ አስተዳደር በኢትዮጵያ የታየው የስልጣን ሽግግር ታሪካዊ፣ ሰላማዊና ህገመንግስታ ነው በማለት አወድሶታል። አሜሪካ ከአቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ጋር ጥሩ የሆነ ግንኙነት መመሰርቷን የገለጠው መግለጫ ፣ በሚቀጥሉት አመታት የኢኮኖሚ ግንኙነቱን ለማጠንከር፣ ሰብአዊ መብቶችንና ዲሞክራሲን ለማጎልበት እንዲሁም የአካባቢውን ጸጥታ ለማስጠበቅ ከእርሳቸው ጋር በጋራ እንደሚሰራ አስተዳደሩ ገልጧል። የአሜሪካ መንግስት አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ...

Read More »

ሲሉ አቶ ስብሀት ነጋ ተናገሩ

መስከረም ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የህወሀት መስራች የሆኑት አቶ ስብሀት ነጋ ይህን ያሉት ሰሞኑን ለንባብ ከበቃው አዲስ ጉዳይ መጽሔት ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ነው። ቀደም ሲል  የህዝባዊ ወያነ ሀርነት ትግራይ-ህወሀት ሊቀ-መንበር ሆነው የተመረጡት አቶ አባይ ወልዱ ብሔራዊ እርቅ  የሚለው ጥያቄ  ፈጽሞ ተቀባይነት እንደማይኖረውና  ጥያቄውን የሚያነሱ ሀይሎችን  እንደሚታገሏቸው  መናገራቸው ያታወሳል። የአቶ አባይ ወልዱ  አባባልም ሆነ፤ አቶ ስብሀት ለ አዲስ ...

Read More »

በኮሪያ የኢትዮጵያ ኢምባሲ የባጀት ጥረት ገጠመው

መስከረም ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በደቡብ ኮሪያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ በበጀት ዕጥረት ምክንያት እኤአ 2001  በሩን ዘግቶ ከተመለሰ በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ በ2012  ቢከፈትም ገና ስራውን ከጀመረ 3 ወራትን ሳያስቆጥር ዳግመኛ የበጀት እጥረት እንደገጠመውና ለሰራተኞቹ የሚከፍለው ደመወዝ እንዳጣ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የውስጥ ሰራተኛ አስታወቁ።   ሰራተኛው ለኢሳት በላኩት መልእክት ኢምባሲው በከፍተኛ የገንዘብ ቀውስ ውስጥ ይገኛል።   ለሰራተኞቹ ሊጠበቁ ...

Read More »

በተባበሩት ዓረብ ኢምሬት በሻርጃህ ከተማ 36 ኢትዮጵያውያን ሴቶች ታሰሩ

መስከረም ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢምሬት ኒውስ እንደዘገበው ኢትዮጵያውያኑ በሻርጃህ ፖሊስ የታሠሩት ከስፖንሰሮቻቸው ጠፍተው በመገኘታቸው ነው። ኢትዮጵያውያኑ  በኢምሬት -አረብ ቪላ ውስጥ እንደሚገኙ መረጃ ከደረሰው በሁዋላ በቁጥጥር ሥር  እንዳዋላቸው የገለጸው የሻርጃህ ፖሊስ፤ በህገ-ወጥ መንገድ በሥራ ተሰማርተው እንደነበር አመልክቷል። ጉዳያቸው ወደ አቃቤ ህግ ተልኮ በሁሉም ላይ ክስ እንደሚመሰረትባቸውም ፖሊስ አስታውቋል። በተመሣሳይ መንገድ የተሰማሩ ስደተኞች ካሉ ህዝቡ መረጃ እንዲሰጥ የሻርጃህ ...

Read More »

የኬንያ የአፍሪካ ህብረት ጦር የሶማሊያ ሲቪሎችን ገደለ

መስከረም ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሶማሊያ ከአልሸባብ ተዋጊ ሀይል ጋር በመፋለም ላይ የሚገኘው የኬንያ ሰራዊት ፣ የአልሸባብ ዋና መናገሻ ወደ ሆነችው ኪስማዮ ከተማ ሲያመራ ፣ ሰባት ንጹሀን ዜጎችን መግደሉን ቢቢሲ ዘግቧል። የሶማሊያ መንግስት ጦር ቃል አቀባይ የሆኑት አዳን ሙሀመድ ሂርሲ ግድያው ሆን ተብሎ የተፈጸመ መሆኑን አጋልጠዋል። እንዲህ አይነቱ ድርጊት ስሜትን የሚጎዳ ነው በማለት በአንድ ሱቁ ፊት ለፊት ...

Read More »

የአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ሹመት ህግና ስርአትን የተከተለ አይደለም ተባለ

መስከረም ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሟቹ የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ምትክ የኢትዮጵያ ፓርላማ ከገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ የቀረበለትን ዕጩ ጠ/ሚኒስትር ሹመት ተቀብሎ በማጽደቁ አዲሱ ጠ/ሚኒስትር በትናንትናው ዕለት ቃለመሃላ ፈጽመዋል፡፡ ፓርላማው ትናንት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ሆነው እንዲያገለግሉ የቀረበለትን የሹመት ጥያቄ ተቀብሎ ያጸደቀበት ሒደት ግን ሕግና ሥርዓትን ያልተከተለ ነው በሚል አንዳንድ የሕግ ባለሙያዎች እየተቹት ...

Read More »

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የአቶ ሀይለማርያምን ሹመት እንደምትቀበለው አስታወቀች

መስከረም ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የክቡር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝን በጠቅላይ ሚኒስትርነት መመረጥና የክቡር አቶ ደመቀ መኮንን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን መመረጣቸውን በማስመልከት ለኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ፕ/ት ቤት ያስተላለፈችው መልክት” በሚል ርእስ ትናንት ባወጣችው መግለጫ ለአቶ መለስ ዜናዊ አመራር የነበራትን አድናቆትም ገልጣለች። ቤተክርስቲያኑዋ ” ይህ ያለፈው ዘመን ለአገራችንና ለአፍሪካ ብሎም ለአለም ህዝብ ትልቅ ...

Read More »

በቂ የውጪ ምንዛሬ ያለው በወጋገን ባንክ ብቻ ነው ተባለ

መስከረም ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአገሪቱ ባንኮች በውጪ ምንዛሬ እጥረት በተጠቁበት በአሁኑ ጊዜ የወጋገን ባንክ ደንበኞች ብቻ ያለምንም እጥረት ንግዳቸውን እያቀላጠፉ መሆናቸው ተጠቆመ። የአይ.ኤም.ኤፍ የ ኢትዮጵያ ተወካይ  አገሪቱ ለሁለት ወራት የሚበቃ የውጪ ምንዛሬ እንዳላት በቅርቡ ቢገልጹም ዋናውን ንግድ ባንክ ጨምሮ በ አገሪቱ የሚገኙ ባንኮች በሙሉ በከፍተኛ እጥረት በመጠቃታቸው ደንበኞቻቸውን ማገልገል እንደተሳናቸው  የአዲስ አበባ የ ኢሳት ወኪሎች ከተለያዩ ...

Read More »