በኮሪያ የኢትዮጵያ ኢምባሲ የባጀት ጥረት ገጠመው

መስከረም ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በደቡብ ኮሪያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ በበጀት ዕጥረት ምክንያት እኤአ 2001  በሩን ዘግቶ ከተመለሰ በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ በ2012  ቢከፈትም ገና ስራውን ከጀመረ 3 ወራትን ሳያስቆጥር ዳግመኛ የበጀት እጥረት እንደገጠመውና ለሰራተኞቹ የሚከፍለው ደመወዝ እንዳጣ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የውስጥ ሰራተኛ አስታወቁ።

 

ሰራተኛው ለኢሳት በላኩት መልእክት ኢምባሲው በከፍተኛ የገንዘብ ቀውስ ውስጥ ይገኛል።

 

ለሰራተኞቹ ሊጠበቁ የሚገባቸው ጥቅማጥቅሞች ፈፅሞ ሊታሰቡ የማይገባቸው ጉዳዮች ሆነዋል በማለት ግለሰቡ ገልፀዋል።

 

በተለይም  ሰራተኞች የጤና ኢንሹራንስ የለንም፣ የጡረታ አበል አይከፈልልንም፣ የአደጋ ጊዜ ኢንሹራንስ የለንም፣ የአገልግሎት አበል አልተከበረልንም፣ የትርፍ ጊዜ ክፍያ አይከፈለንምና የተደራረበ የስራ ጫና አለብን በማለት ቢያሳውቁም መልስ አላገኙም።

 

በአንድ በኩል በበጀት እጥረት ምክንያት ለሰራተኛ የሚከፈል ደመወዝ እንዲስተጓጎል እና አስፈላጊ የሰው ሃይል ቅጥር እንዳይደረግ ቢደርግም በሌላ በኩል ደግሞ እጅግ የተጋነነና  ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ለኮርያ ንጉሳዊ ቤተሰቦች ተደጋጋሚ ግብዣ እንደሚደረግ የውስጥ ሰራተኛው ቅሬታቸውን ለኢሳት ገልጠዋል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide