የኬንያ የአፍሪካ ህብረት ጦር የሶማሊያ ሲቪሎችን ገደለ

መስከረም ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በሶማሊያ ከአልሸባብ ተዋጊ ሀይል ጋር በመፋለም ላይ የሚገኘው የኬንያ ሰራዊት ፣ የአልሸባብ ዋና መናገሻ ወደ ሆነችው ኪስማዮ ከተማ ሲያመራ ፣ ሰባት ንጹሀን ዜጎችን መግደሉን ቢቢሲ ዘግቧል።

የሶማሊያ መንግስት ጦር ቃል አቀባይ የሆኑት አዳን ሙሀመድ ሂርሲ ግድያው ሆን ተብሎ የተፈጸመ መሆኑን አጋልጠዋል። እንዲህ አይነቱ ድርጊት ስሜትን የሚጎዳ ነው በማለት በአንድ ሱቁ ፊት ለፊት በኬንያ ወታደሮች ለተገደሉት ወጣቶች የሶማሊያ አዲሱ መንግስት እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል።

ባለፈው ቅዳሜ የአልሸባብ ታጣቂዎች አንድ የሶማሊያ የፓርላማ አባል ሞቃዲሾ ውስጥ መግደላቸው ይታወሳል። የተገደሉት የፓርላማ አባል የተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ሸክ ሸሪፍ አህመድ ባለቤት አባት ናቸው።

ባሳለፍነው ሀሙስ አልሸባብ በፈጸመው ጥቃት ደግሞ 18 ሰዎችን መግደሉ ይታወሳል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide