ለዩኒቨርስቲ መምህራን ሊሰጥ የነበረው አገር አቀፍ ስልጠና ተሰረዘ

መስከረም ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የትምህርት ሚኒስቴር በቁጥር 7/ጠ-259/2311/04 በ 10/12/2004  ዓም በጻፈው ደብዳቤ ለዩኒቨርስቲ መምህራን ከመስከረም 10 እስከ 20 ቀን 2005 ዓም የሚቆይ አገራቀፍ ስልጣን ለመስጠት አቅዶ የነበረ ቢሆንም ይህን እቅዱን በመሰረዝ ስልጠናው ከመስከረም 3 እስከ 20 እንዲሆን አዲስ መመሪያ መበተኑን ኢሳት መዘገቡ ይታወሳል።

ዩኒቨርስቲው የቪዲዮ ኮንፈረንሱን  ለማዘጋጀት በስድስት ኪሎ  እና በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ አዳራሾችን ቢያዘጋጅም፣ በዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት በዶ/ር አድማሱ ጸጋየ ፊርማ መስከረም 3 ቀን 2005 ዓም  በተጻፈው ደብዳቤ ስብሰባው ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ተዳርጓል።

ለስብሰባው መራዘም የተሰጠው ምክንያት ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት የሚል ይሁን እንጅ የዩኒቨርስቲ መምህራን ለኢሳት እንደገለጡት ግን  በመንግስት በኩል ያለው አለመረጋጋት  ስልጠናውን ለማራዘም ግድ ሳይል እንዳልቀረ ያመለክታል።

ትናንት ከትምህርት ጥራት ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው የሃይማኖት አክራሪነት የስልጠናው አጀንዳ ሆኖ ለአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን የቀረበ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ ኢህአዴግና መንግሥት በመተካካት ሂደት የደረሱበት ዕመርታ የውይይት መነሻ እንደሚሆን መግለጻችን ይታወቃል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide