በደቡብ ክልል የተለያዩ ከተሞች ነዋሪዎች ሲሉ ተናገሩ

መስከረም ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ከደቡብ ክልል ከወላይታ ብሄረሰብ የተገኙ መሆናቸው በክልሉ ነዋሪዎች ዘንድ ምን ስሜት ፈጠረ የሚለውን ለማወቅ ኢሳት ከተለያዩ የክልሉ ነዋሪዎች ጋር  ቃለምልልስ አድርጓል።

አንዳንድ ነዋሪዎች የእርሳቸው መመረጥ ደስታ የፈጠረላቸው መሆኑን ቢናገሩም፤ አብዛኞቹ ግን ሹመቱ የይስሙላ በመሆኑ ምንም ስሜት እንዳልሰጣቸው ይናገራሉ።

አቶ ኦታራ ኦሼ የጋሞጎፋ ዞን ተወላጅ ናቸው። የአቶ ሀይለማርያም ሹመት ” ‘ ጉልቻ ቢቀያየር ወጥ አያጣፍጥም’ አይነት ነው፤ ኢህአዴግ የ20 አመት ሳይሆን የ40 አመት ራእይ እናስፈጽማለን እያለ በሚናገርበት ጊዜ፤ ምን ይጠበቃል” በማለት ለውጥ እንደማይመጣ ገልጠዋል

ወጣት ዲንጋም የተባለው የዲላ ነዋሪ በበኩሉ የአቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ሹመት ለውጥ ያመጣል የሚል እምነት እንደሌለው ገልጧል ።  ወጣት ዲንጋማ እንደሚለው ግለሰቡ የተቅላይ ሚኒስተርነቱን ድርሻ  ከምር የያዙ ባለመሆኑ ፤ ለውጥ የመጣል ተብሎ በክልሉ ህዝብ እንደማይታሰብ ተናግሯል

በአዋሳ ከተማ ነዋሪ የሆኑት የተቃዋሚ ፓርቲ አባሉ አቶ ሲዳ ሀይሌ  ደግሞ፤ድርጅቱ ኢህአዴግ እስካለ ድረስ   የአቶ መለስ መሄድና የአቶ ሀይለማርያም መምጣት_ ለውጥ እንደማያመጣ ገልጠዋል። <ኢህአዴግ ሄደ፤ ኢህአዴግ ተተካ ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚጠቅመው የለም> ሲሉ አቶ ሲዳ አክለዋል

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide