የደመራ በአል በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ ተከበረ

መስከረም ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከምታከብራቸው ታላላቅ ሀይማኖታዊ በአላት መካከል አንዱ የሆነው የደመራ በአል በዛሬው እለት በመላ አገሪቱ ተከብሮአል።

የደመራ በአል  ንግስት ኢሌኒ እየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበትን መስቀል ለመፈለግ የተጠቀመችበትን ደመራ እና የእጣን ጭስ ለመዘከር የሚደረግ ሀይማኖታዊ በአል ነው። የቤተክርስቲያኑዋ መጽሀፍት እንደሚያመለክቱት ግማደ መስቀሉ በአጼ ዳዊትና በልጃቸው ባአጼ ዘርአያቆብ በአስራ አምስተኛም ምእተ አመት መግቢያ ላይ ወደ ኢትዮጵያ ገብቷል።

በአዲስ አበባ ዛሬ በተከበረው የደመራ በአል ላይ በርካታ ጎብኝዎች ስርአቱን ተከታትለውታል።

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንም በቀጥታ ስርጭቱ አንድ ጊዜ የአቶ መለስ ዜናዊን ፎቶ ግራፍ ሌላ ጊዜ የበአሉን ስነስርአት እያፈራረቀ ለህዝብ አቅርቧል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide