በሰሜን ሸዋ የሚገኙ መምህራን በፖለቲካ አቋማቸው ምክንያት እየታደኑ ነው

መስከረም ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የሰሜን ሸዋ መምህራን ለኢሳት እንደገለጡት፣ የኢህአዴግ መንግስት አንድ ለአምስት በሚለው አደረጃጀቱ የግንባሩ አባላት ለመሆን ፈቃደኛ አልሆኑም ያላቸውን መምህራን እያዋከበ ነው። የኢህአዴግ አባል ለመሆን ፈቃደኛ አልሆኑም የተባሉ መምህራን የአመለካከት ችግር አለባቸው፣ ከሌሎች የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት አባላት ጋር  ትሰራላችሁ፣ የራሳችሁን የፖለቲካ አመለካከት ታራምዳላችሁ እየተባሉ ወከባና ማስፋራሪያ ሲደርስባቸው መቆየቱን መምህራን ይናገራሉ። በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ...

Read More »

ወ/ሮ አዜብ መስፍን እስካሁን ቤተመንግስቱን ለአቶ ኃለማርያም አላስረከቡም

መስከረም ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ዘጋቢ እንደገለጠው ወ/ሮ አዜብ መስፍን ቤተ መንግስቱን ለቀው ባለመውጣታቸው አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም  ደሳለኝ  ቦሌ ከሚገኘው ቤታቸው ጠዋት እና ማታ ሲገቡና ሲወጡ መንገድ እየተዘጋ ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ እየተፈጠረ ከመሆኑም በላይ ከአሁኑ የአካባቢውን ነዋሪዎች እያስመረሩ ነው፡፡ በርግጥ ሥራቸውን ጠ/ሚኒስትር ቢሮ እየገቡ በመስራት ላይ መሆናቸውን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ ወ/ሮ አዜብ በአሁኑ ወቅት በትግራይ ክልል ...

Read More »

የመንግስት ሰራተኞችን በአመለካከታቸው የሚገመግም አዲስ መመሪያ ተዘጋጀ

መስከረም ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አዲሱ የአቶ ሀይለማርያም ና የአቶ በረከት ስምኦን ጥምር መንግስት የክልልና የወረዳ ባለስልጣናትን በባህርዳር  ከመስከረም 21 እስከ 26 በመሰብሰብ ነው ይህን መገምገሚያ ይፋ ያደረገው። የስብሰባው አላማ የትራንስፎርሜሽን እቅዱን  ጠንካራና ደካማ ጎኖችን መገምገም የሚል ሲሆን፣ የስብሰባው መፈክር ደግሞ “ዘመቻ መለስ” የሚል እንደነበር ታውቋል። በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው በተመራው ስብሰባ ላይ እንደተገለጸው የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች ከእንግዲህ ...

Read More »

”ኢህአዴግ ሕዝቦች በአንድ ድምፅ ሲናገሩና ሲሰበሰቡ አይወድም” ሲል የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር ሊቀ-መንበር ወጣት ሀብታሙ አያሌው ገለጸ

መስከረም ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለራዕይ የወጣቶች ማህበር ባለፈው ዓመት ጥር ወር ነው በኢትዮጵያ በበጎ አድራጎት ማኅበራት ምዝገባ ኤጀንሲ የተመዘገበው ። ማህበሩ፤የቀድሞው የወጣቶች ፌዴሬሽን አመራር የነበረውና ከኢህአዴግ ጋር ለረጅም ጊዜ የሠራው አቶ ሀብታሙ ከኢህአዴግ በመውጣትና ሌሎች ወጣቶችን በማስተባበር ያቋቋመው  ነፃ የብዙኃን ማኅበር ነው። የማኅበሩ ለቀመንበር ወጣት ሀብታሙ እንደሚለው ፤ ባለራዕይ የወጣቶች ማህበር  በህግ ጥላ ስር የሚንቀሳቀስ ቢሆንም፤በአዲስ ...

Read More »

“መንግስት ከንግዱ ዘርፍ እጁን ጨርሶ ይሰብስብልን” ሲሉ ሼህ መሀመድ ሁሴን አል-አሙዲ ጠየቁ

መስከረም ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሼህ መሀመድ ሁሴን አል-አሙዲ ይህን ጥያቄ ያቀረቡት፤ በኮምቦልቻ ከተማ  የሚያሠሩትን የጦሳ ብረታብረት ፋብሪካ  ለመገንባት ኮንትራቱን ካሸነፈው የጣሊያን ኩባንያ ጋር  ሲፈራረሙ  ባደረጉት ንግግር ነው።  ‹‹መንግሥትን የምለምነው የንግዱን ነገር ለእኛ እንዲተውልን ነው፤ መንግሥት በመሠረተ ልማት ግንባታ፣ ሰላምና ፀጥታ በማስከረበር ላይ ቢበረታ መልካም ነው >>በማለት ነው ልመናቸውን ያቀረቡት። አል-አሙዲ መንግስት ጨርሶ ከንግዱ እንዲወጣ  ጥያቄ ያቀረቡት፤ ...

Read More »

ዲናው መንግስቱ የማካርተር ጂኒየስ አዋርድ አሸናፊ ሆነ

መስከረም ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዲናው ጂኒየስ ገራንት የተባለውን ሽልማት ያሸነፈው ” How to Read the Air” በሚለው እኤአ በ2012 ባሳተመው የልቦለድ መጽሀፍ ነው።  ከዲናው በተጨማሪ ደራሲ ጁኖት ዲያዝ ” This is how you lose her” በሚለው ድርሰቱ አሸንፎአል። ተሸላሚዎቹ እያንዳንዳቸው 500 ሺ ዶላር እንደሚያገኙ ለማወቅ ተችሎአል። ዲናው ” The Beautiful Things that Heaven Bears” በሚል ርእስ ...

Read More »

ከአንድ ሺ ያላነሱ ቤተሰቦች ጎዳና ላይ ተበተኑ

መስከረም ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአዲስ አበባ መስተዳዳር በንፋስ ስልከ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዜሮ አንድ ሱቂ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ከመስከረም 19  ጀምሮ እያካሄደ ባለው ህገወጥ ያላቸውን ቤቶች በማፍረስ እርምጃ ከ1000 ያላነሱ ነዋሪዎችን የያዙ  ከ130 በላይ ቤቶች እየፈረሱ ነው። በመንግስት ድርጊት በርካታ ህጻናት ሲያልቅሱ፣ ቋሚዎች ሙታንን ለመቅበር ሲቸገሩ፣ አሮጊቶችና ሽማግሊዎች መጠጊያ አጥተው ለብርድና ለዝናብ መዳረጋቸውን ቤታቸው የፈረሰባቸው ...

Read More »

የአንድነት ፓርቲ አመራሮች የፍኖተ ነጻነት እግድ እንዲነሳ በድጋሚ ጠየቁ

መስከረም ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በመንግስት ቀጥተኛ ትእዛዝ የታገደው የፓርቲው ልሳን የሆነው  ፍኖተ ነጻነት እንደገና ስራውን እንዲጀምር ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ጠይቀዋል። ጋዜጣዊ መግለጫውን የሰጡት የፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ ዋና ጸሀፊው አቶ አስራት ጣሴ፣  የብሄራዊ ምክር ቤት ዋና ጸሀፊ አቶ ትእግስቱ አወሉ፣ የፓርቲው ከፍተኛ የአመራር አባል አቶ ስዩም መንገሻ፣ እና የህዝብ ግንኙነት ...

Read More »

የደቡብ ጎንደር እስቴ መካነ ኢየሱስ ከተማ ነዋሪዎች አቤቱታ ለማቅረብ አዲስ አበባ ገቡ

መስከረም ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ በታጣቂዎች ከፍተኛ ድብደባና ግድያ ጭምር የተፈጸመባቸው  የደቡብ ጎንደር እስቴ መካነ ኢየሱስ ከተማ  ነዋሪዎች አቤቱታ ለማቅረብ አዲስ አበባ ገቡ። ኢሳት  በቅርቡ እንደዘገበው፤በእስቴ መካነ ኢየሱስ ነዋሪዎችና በፖሊሶች መካከል ችግር የተፈጠረው፤በከተማዋ የሚያልፈው የመንገድ ፕሮጀክት በሌላ በኩል በማለፉ ምክንያት ህዝቡ በሰላማዊ ሰልፍ ተቃወሞውን ለማሰማት በመውጣቱ ነው። ለህዝቡ የታውሞ ሰልፍ የመንግስት ተወካዮች ምላሽ ...

Read More »

መምህራን ለአዲሱ መንግስት የታዛዥነት ቃል ኪዳናቸውን እንዲያድሱ የሚያደርግ ጉባኤ ተዘጋጀ

መስከረም ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-መንግስት ተሀድሶ በማለት በሚጠራው በዚህ የቃል ኪዳን ማደሻ ጉባኤ ላይ መምህራን የአቶ መለስ ዜናዊን ራእይ ለማስቀጠል ቃል  እንዲገቡ ይጠየቃሉ ። በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በቁጥር ን/ስ/ላ/ወ1/0342/2005 በቀን 10/01/2005ዓም ድጋፍ እንዲደረግ ስለመጠየቅ በሚል ርእስ የተጻፈው ደብዳቤ እንደሚያሳየው ትምህርት ቤቶች ለዚሁ ለተሀድሶ ስራ ማስፈጸሚያ እስከ 600 መቶ ሺ ብር የሚጠጋ ገንዘብ እንዲያዋጡ ተጠይቀዋል ...

Read More »