የኦህዴድ ካድሬዎች የአቶ ሀይለማርያምን ሹመት በመቃወማቸው በኦነግነት እየተከሰሱ ነው

መስከረም ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ለኢሳት የደረሱት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የኦሮሞ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ካድሬዎች፣ ኦህዴድ ተገቢውን የስልጣን ቦታ አለገኘም በማለት ተቃውሞ ማሰማታቸውን መቀጠላቸውን ተከትሎ በርካታ ካድሬዎች በኦነግነት እየተወነጀሉ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል።

በከፍተኛ ስልጣን ላይ የሚገኙት የኦህዴድ መሪዎች ሹመቱን ከመቀበል ውጭ ሌላ አማራጭ የለም በማለት አቋማቸውን ግልጽ በማድረግ ካድሬዎቻቸውን ለማሳመን ጥረት ቢያደርጉም፣ በመካከለኛ ደረጃ የሚገኙ እና ተራ አባላቱ ግን አንቀበለም በማለት እያንገራገሩ ነው።

ይህንን ተከትሎ በርካታ አባሎች የኦነግ አስተሳሰብ ያላችሁ ናቸው በማለት እየተገመገሙና ማስፈራሪያም እየደረሳቸው ነው። ካድሬዎቹ የሚያነሱት ጥያቄ ” ኦሮሚያ ሰው የለውም ወይ?’ የሚል ሲሆን አመራሮችም በቂ መልስ ለመስጠት አለመቻላው ታውቋል።

ካድሬዎቹ  ጥንካሬያቸው እስከምን ደረጃ እንደሆነ ለማወቅ ባይቻልም፣ የተቃውሞው ይዘት እየጨመረ በመምጣቱ ድርጅቱ ለመስከረም 19 ማእከላዊ ኮሚቴውን ስብሰባ ጠርቷል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide