መስከረም ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ የሳዑዲ ኤምባሲ ምንጮች አንዳንድ ሁኔታዎችን ለማጣራት ለተወሰኑ ቀናት ቪዛ መስጠት ከማቆም ውጪ እገዳ አልነበረም ሲሉ መንግስታቸው ጥሎአል የተባለውን እገዳ አስተባብለዋል፡፡ ለኢትዮጵያ እስልምና ም/ቤት ቅርበት ያላቸው ምንጮች ግን እገዳው ለተወሰኑ ቀናት ተጥሎ ከቆየ በኃላ በጉዳዩ የኢትዮጵያ መንግስት ጣልቃ ገብቶ በተደረገ ውይይት ቪዛ የመስጠቱ ሥራ መቀጠሉን ተናግረዋል፡፡ ጉዞው የታገደበት ምክንያት በግልጽ የተነገረ ባይሆንም ...
Read More »ኢህአዴግ የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ እና የጋዜጣው ከፍተኛ አዘጋጆችን ለማሰር መሰናዶ እያደረገ መሆኑን ምንጮቻችን ገለጹ
መስከረም ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የደህንነት ሰዎችም በድጋሚ የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ውሎና አዳር መከታተል መጀመራቸውን ለጋዜጠኛው ቅርበት ያላቸው የዓይን እማኞች ገልጸውልናል፡፡ ጋዜጠኛ ተመስገን እንደገለጠው በዛሬው እለት የደህንነት ሰዎች በአካባቢው ባይታዩም እስካለፈው ቅዳሜ ድረስ ማንነታቸው የማይታወቁ ሰዎች ሲከታተሉት እንደነበር ገልጧል። የኢሳት ዘጋቢ ከጋዜጠኛ ተመስገን ጋር ቃለምልልስ በሚያደርግበት ወቅት ስልኩ በተደጋጋሚ እየተቋረጠ ሲቸገር መዋሉን ገልጧል።። አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን የአቶ ...
Read More »የታላቁ ሩጫ ሀብት ሊወረስ ነው
መስከረም ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ላለፉት 12 ዓመታት በአዲስ አበባና በተለያዩ ክልልሎች የጎዳና ላይ ሩጫ ለተለያዩ ዓላማዎች በማካሄድ ያገኘው ሀብት ሕገወጥና ከተመሠረተበት ዓላማ ውጪ ነው ተብሎ ሊወረስ መሆኑን ለገዢው ፓርቲ ቅርበት ያለው ሪፖርተር ጋዜጣ ዘገበ ከ12 አመታት በላይ በየዓመቱ በአዲስ አበባ ላይ የ10 ሺሕ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በማካሄድ እውቅና ያገኘው የአትሌት ሀይሌ ገ/ስላሴ ...
Read More »የኬንያ እና የሶማሊያ መንግስት ጥምር ጦር ኪስማዩ ገባ
መስከረም ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኬንያና የሶማሊያ መንግስት ጥምር ጦር በአልሸባብ ላይ የጀመረውን ከፍተኛ ወታደራዊ ጥቃት በማጠንከር፣ ሚሊሺያው የስትራቴጂክና የኢኮኖሚ ጠቀሜታ የነበራትን ኪስማዩን ለቆ እንዲወጣ ማድረጉ ይታወሳል። ምንም እንኳ አልሸባብ ኪስማዩን ለቆ መውጣቱን ከሶስት ቀናት በፊት ቢያስታውቅም፣ በኬንያ የሚመራው የአፍሪካ ህብረትና የሶማሊያ መንግስት ጦር ግን ከተማዋን እስካሁን ሳይቆጣጠራት ቆይታል። አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን እንደዘገቡት ጦሩ በዛሬው እለት አንዳንድ ...
Read More »የሳውዲ አረብያ መንግስት ኢትዮጵያን ከሀጂና ኡምራ ጉዞ አገደ
መስከረም ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የሳዑዲዓረቢያ መንግስት ኢትዮጵያን ከሐጂና ዑምራ ጉዞ በድንገት ማገዱ ሙስሊሙን ኀብረተሰብ ማስደንገጡን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች አረጋገጡ፡፡ በየዓመቱ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ለሐጂ ጸሎት ወደ ሳዑዲዓረቢያ የሚያደርጉት ሃይማኖታዊ ጉዞ የአረፋ በዓል ሊደርስ አንድ ወር ሲቀረው ጀምሮ የሚከናወን መሆኑን አስታውሰው ዘንድሮም በሙስሊሙ ኀብረተሰብ አመኔታ ያጣው የኢትዮጵያ እስልምና ም/ቤት(መጅሊስ) ጉዞውን እንደሚያስተባብር ማስታወቂያ በይፋ አስነግሮ የነበረ ቢሆንም ...
Read More »በእስር ላይ የሚገኘው የአንድነት ፓርቲ አመራር አቶ አንዱአለም አራጌ ለነጻነት የሚደረገው ትግል እንዲቀጥል አሳሰበ
መስከረም ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በግፍ እስር ላይ የሚገኘው የአንድነት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት ሀላፊው ወጣቱ ፖለቲከኛ አንዱአለም አራጌ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች መስከረም 17 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም በሽብርተኝነት ስም ታስሮ የሚገኘውንና እና የፓርቲው ከፍተኛ አመራር የሆነውን አቶ አንዱዓለም አራጌን በቃሊቲ በመገኘት ጎብኝተዋቸዋል። አመራሩ የአንድነት ፓርቲ የብሔራዊ ም/ቤት አባል የሆነውንና ቂሊንጦ ታስሮ የሚገኘውን አቶ ናትናኤል መኮንንም ጎብኝተዋል። ...
Read More »ተቃውሞዎችን ወደ ጎን በመግፋት መንግስት ለውጭ ባለሀብቶች መሬት መስጠቱን አንደሚቀጥል አስታወቀ
መስከረም ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያን ሰፊ መሬት በአለም ደረጃ ታይቶ በማይታወቅ አነስተኛ ዋጋ እየቸበቸ ነው የሚል ክስ የሚቀርብብት መንግስት፣ ከኢትዮጵያና ከአለማቀፍ ድርጅቶች ሳይቀር የሚቀርብበትን ትችት ወደ ጎን በመተው በዚህ አመት ተጨማሪ አንድ መቶ ሺ ሄክታር መሬት ለመስጠት አቅዷል። አፍሪካን ሚኒራልስ እንደዘገበው ሰፋፊ የሆኑ መሬቶችን በጋምቤላ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች ለውጭ ባለሀብቶች ለመስጠት ታቅዷል። የኢትዮጵያ ...
Read More »በኢትዮጵያ የሚታየው የኑሮ ውድነት አሁንም የህዝቡ ቁጥር አንድ ችግር ነው ተባለ
መስከረም ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ዘጋቢዎች በተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር ባሰባሰቡት መረጃ የኢትዮጵያ ህዝብ አሁንም ቁጥር አንድ ችግር ብሎ የሚያነሳው የኑሮው ውድነቱን ነው። የኑሮ ውድነቱ ከዛሬ ነገ ይቀንሳል በማለት ህዝቡ ተስፋ ቢያደርግም፣ ውድነቱ ግን ከመጨመር ውጭ ሊቀንስ አልቻለም። ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ መምህር ፣ ሶስት ልጆቻቸውን ለማስተማር ቀርቶ አብልተው ለማኖር እንደተቸገሩ ገልጠዋል። በኑሮ ውድነቱ የተነሳ አመታዊ በአላትን ...
Read More »የአልሸባብ ተዋጊዮች ኪስማዮን ለቀው ወጡ
መስከረም ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የሶማሊያ መንግስትና በአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ስም የዘመተው የኬንያ ጦር በጋር በመሆን በአልሸባብ ላይ የከፈቱት ዘመቻ ወደ ፍጻሜው እየተቃረበ መምጣቱን መረጃዎች ያመለክታሉ። አልሸባብ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ገቢ የሚያስገኝለትን የወደብ ከተማ የሆነችውን ኪስማዩን ለመልቀቅ መገደዱ፣ የድርጅቱን ፍጻሜ ሊያቃርበው እንደሚችል ነው ዘገባዎች የሚያመለክቱት። የሶማሊያ ጦር አዛዥ እንደተናገሩት አልሸባብ ኪስማዩን ለቆ ቢወጣም ፣ የአፍሪካ ህብረት ጦር ...
Read More »በመተማ ከአቶ መለስ ሞት ጋር በተያያዘ ከ120 በላይ ሰዎች ታሰሩ
መስከረም ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢሳት እንዳረጋገጠው በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር ዞን በመተማ ከተማ በአቶ መለስ ዜናዊ ሞት ደስታችሁን ገልጣችሁዋል የተባሉ ከ120 በላይ ሰዎች ታስረው ስቃይ እየደረሰባቸው ነው። የመተማ አካባቢ ነዋሪዎች እንደገለጡት አቶ መለስ ዜናዊ ሞታቸው እንደተሰማ ” መለስ እንኳንም ሞተ፣ ተገላገልን” በማለት በመጠጥ ቤቶች ውስጥም ሆነ በተለያዩ ቦታዎች ደስታቸውን ገልጠዋል የተባሉ ከ120 በላይ ሰዎች ታስረዋል። ግለሰቦቹ ...
Read More »