በኢትዮጵያ የሚታየው የኑሮ ውድነት አሁንም የህዝቡ ቁጥር አንድ ችግር ነው ተባለ

መስከረም ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የኢሳት ዘጋቢዎች በተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር ባሰባሰቡት መረጃ የኢትዮጵያ ህዝብ አሁንም ቁጥር አንድ ችግር ብሎ የሚያነሳው የኑሮው ውድነቱን ነው።

የኑሮ ውድነቱ ከዛሬ ነገ ይቀንሳል በማለት ህዝቡ ተስፋ ቢያደርግም፣ ውድነቱ ግን ከመጨመር ውጭ ሊቀንስ አልቻለም።

ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ መምህር  ፣ ሶስት ልጆቻቸውን ለማስተማር ቀርቶ አብልተው  ለማኖር እንደተቸገሩ ገልጠዋል። በኑሮ ውድነቱ የተነሳ አመታዊ በአላትን በወጉ ለማክበር አለመቻላቸውን ገልጠዋል።

የኑሮ ውድነቱ ከክልል ክልል ተመሳሳይ መሆኑን የገለጡት ዘጋቢዎቻችን አብዛኛው ህዝብ ግራ ተጋብቶ የሚያደርገው እንደጠፋው አክለዋል።

የመንግስት ሰራተኞች ለአባይ ግድብ ማሰሪያ የወር ደሞዛቸውን እንዲለግሱ ከፍተኛ ጫና እየደረሰባቸው መሆኑም ኑሮዋቸውን እንዳከበደባቸው የመንግስት ሰራተኞች ይገልጣሉ።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide