ተቃውሞዎችን ወደ ጎን በመግፋት መንግስት ለውጭ ባለሀብቶች መሬት መስጠቱን አንደሚቀጥል አስታወቀ

መስከረም ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያን ሰፊ መሬት በአለም ደረጃ ታይቶ በማይታወቅ አነስተኛ ዋጋ እየቸበቸ ነው የሚል ክስ የሚቀርብብት መንግስት፣ ከኢትዮጵያና ከአለማቀፍ ድርጅቶች ሳይቀር የሚቀርብበትን ትችት ወደ ጎን በመተው በዚህ አመት ተጨማሪ አንድ መቶ ሺ ሄክታር መሬት ለመስጠት አቅዷል።

አፍሪካን ሚኒራልስ እንደዘገበው ሰፋፊ የሆኑ መሬቶችን በጋምቤላ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች ለውጭ ባለሀብቶች ለመስጠት ታቅዷል።

የኢትዮጵያ መንግስት አርሶአደሮችን ከመሬታቸው በሀይል እያፈናቀለ በርካሽ ዋጋ መቸብቸቡን ሂውማን ራይትስ ወች የተባለው አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ጥናት አድርጎ ማጋለጡ ይታወሳል።

የተለያዩ ኢትዮጵያውያን ምሁራንም የመሬት ችብቸባው ኢትዮጵያውን በዘመናዊ ቅኝ ግዛት ውስጥ የሚያስገባት ነው በማለት እየተቃወሙት መሆኑ ይታወቃል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide