የኬንያ እና የሶማሊያ መንግስት ጥምር ጦር ኪስማዩ ገባ

መስከረም ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የኬንያና የሶማሊያ መንግስት ጥምር ጦር በአልሸባብ ላይ የጀመረውን ከፍተኛ ወታደራዊ ጥቃት በማጠንከር፣ ሚሊሺያው የስትራቴጂክና የኢኮኖሚ ጠቀሜታ የነበራትን ኪስማዩን ለቆ እንዲወጣ ማድረጉ ይታወሳል።

ምንም እንኳ አልሸባብ ኪስማዩን ለቆ መውጣቱን ከሶስት ቀናት በፊት ቢያስታውቅም፣ በኬንያ የሚመራው የአፍሪካ ህብረትና የሶማሊያ መንግስት ጦር ግን ከተማዋን  እስካሁን ሳይቆጣጠራት ቆይታል።

አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን እንደዘገቡት ጦሩ በዛሬው እለት አንዳንድ የኪስማዩ ከተማ ቦታዎችን መቆጣጠር ጀምሯል።

ምንም እንኳ የኪስማዩ መያዝ የአልሸባብን ፍጻሜ ያመጣል ተብሎ ባይታስብም፣ ሚሊሺያው ከእንግዲህ ወዲያ እስከ ዛሬ የነበረውን ሐይል ይዞ ይቀጥላል ተብሎ አይታመንም።

አልሸባብ  ከአልቃይዳ ጋር በጋራ መስራት መጀመሩን ይፋ ማድረጉ ለውድቀቱ ዋና ምክንያት እንደሆነ የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide