ቴዲ አፍሮ በግዮን ሆቴል የተሳካ ኮንዘርት አካሄደ

ጥቅምት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዕውቁ ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን ቅዳሜ ምሽት በግዮን ሆቴል ያዘጋጀው <ኮንሰርት> እጅግ የተሳካ እንደነበር በስፍራው የተገኙት የኢሳት ሪፖርተሮች ዘግበዋል። ኮንሰርቱ በነበረው ድምቀት እስከዛሬ ከተደረጉት የሙዚቃ ኮንሰርቶች  ሁሉ  በቀዳሚነት ስፍራ የሚመደብ ነው ያሉት ዘጋቢዎቻችን፤ ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁንም አቡጊዳ ከሚለው የመጀመሪያው አልበሙ ጀምሮ እስከ አዲሱ <ጥቁር ሰው> አልበም ድረስ ከተካተቱት ሙዚቃዎቹ ጥቂት የማይባሉትን በጥሩ ትንፋሽና ...

Read More »

ሰበር ዜና በአማራ ክልል ቃሉ ወረዳ በደጋንና ገርባ ቀበሌዎች በፌደራል ፖሊስና በህዝቡ መካከል ግጭት ተነስቷል።

ሰበር ዜና በአማራ ክልል ቃሉ ወረዳ በደጋንና ገርባ ቀበሌዎች በፌደራል ፖሊስና በህዝቡ መካከል ግጭት ተነስቷል። ችግሩ የተፈጠረው የፌደራል ፖሊስ ሁለት የእስልምና ተከታይ ወጣቶችን ይዞ በማሰሩ ነው፡፡ የአካባቢው ህዝብም የወጣቶችን እስር በመቃወምና ወደ ፖሊስ ጣቢያ በማምራት በሀይል ወጣቶችን አስፈትቷል።  በአካባቢው የነበሩ የፌደራል  የወረዳ ፖሊሶች የህዝቡን ቁጣ በማየት ሸሽተው የነበር ሲሆን፣ የፌደራል ፖሊሶች ከእየአካባቢው በመሰባሰብ ወደ አካባቢው ተጉዘዋል የፌደራል ፖሊስ አባላት አስለቃሽ ...

Read More »

ለወ/ሮ አዜብ መስፍን ተለዋጭ መኖሪያቤት ሊሰራላቸው ነው

ጥቅምት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከቤተመንግስት ላለመልቀቅ እያንገራገሩ ያሉት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ተለዋጭ ቤተመንግስት እንዲሰራላቸው የጀመሩትን ጥያቄ በመግፋት ቦታ እያማረጡ ከቆዩ በሁዋላ ስድስት ኪሎ የሚገኘው አዲስ አበባ ስብሰባ ማዕከል እና የቀድሞ የአቅም ግንባታ ሚኒሰቴር ጊቢ ውስጥ ወደ 60ሺካሬ ሜትር በአንድነት እንዲሆን በመወሰን የግንባታ ጥናት ለማካሄድ የቤተመንግስት አስተዳደር በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኝ ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡ ይሁን እንጅ ቦታው በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ...

Read More »

በጉባ ላፍቶ ወረዳ በቅርቡ በተካሄደው የእስልምና ምክር ቤቶች ምርጫ ያሸነፉ ተመራጮች ዋህቢያ ናችሁ በሚል ታገዱ፣ በምትካቸውም አዲስ ምርጫ ሊካሄድ ነው

ጥቅምት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ዞን በጉባ ላፍቶ ወረዳ በተካሄደው የእስልምና ምክር ቤቶች ምርጫ ፣ በሳንቃ ቀበሌ ከፍተኛ የህዝብ ድምጽ አግኝተው የተመረጡት የቀበሌው የእስልምና ምክር ቤት ሰብሳቢ፣ ዋና ጸሀፊውና ሌሎች ተመራጮች የአህባሽን አስተምህሮ ይቃወማሉ፣ አህባሽን አይቀበሉም እንዲሁም በአዲስ አበባ የሚካሄደውን ተቃውሞ ለመቃወም በተጠራው ሰልፍ ላይ ለመገኘት ፈቃደኛ አልሆኑም በሚል ነው አሸናፊነታቸው ተሰርዞ በምትኩ ሌላ ...

Read More »

በርካታ ነባር የህወሀት አባላት በጋምቤላ የተደረገውን የሊዝ ዋጋ ጭማሪ ተቃወሙ

ጥቅምት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በጋምቤላ ክልል የመንግስት ባለስልጣናት ከክልሉ ባለሀብቶች ጋር ከጥቅምት 9 እስከ 10 ባካሄዱት ስብሰባ ላይ ነው ነባር የህወሀት ታጋዮች አዲሱን የመሬት ሊዝ ዋጋ አምርረው የተቃወሙት። ” የግብር ኢንቨስትመንት የስራ እንቅስቃሴና የ2005 እቅድ የጋራ ውይይት”  በሚል አጀንዳ የተካሄደውን ስብሰባ የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ኦሞድ ኦቦንግ፣ ከፌደራል መንግስቱ ተወክለው የመጡት የኢንቨስትመንት ሃላፊው አቶ ኢሳያስ እንዲሁም የክልሉ የግብርና ...

Read More »

በኢትዮጵያ በታችኛው ኦሞ ሸለቆ በውጭ አገር ባለሃብቶች የሚካሄደው የመሬት ዘረፋና ሽሚያ ተወላጆቹን ለመፈናቀልና ለሞት እያጋለጠ ነው ተባለ።

  ጥቅምት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሰርቫይቫል ኢንተርናሽናል  እንደገለጸው በ አ ካባቢው እየተፈፀመ ያለው ድርጊት ነዋሪዎች መሬታቸውን እንዳያርሱ እንቅፋት በመፍጠር በርካታዎችን በችጋር እያመሰና ‹‹ሞታቸውን እንዲጠብቁ›› እያደረገ ነው ።   ድርጅቱ ይህን ያለው፤በመላው ዓለም ላይ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር  ኦክቶበር 16 ቀን የሚከበረውን  የ “ዓለም የምግብ ቀን”ን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ነው። በታችኛው ኦሞ ሸለቆ በኢትዮጵያ  ኢሰብአዊ ገዥዎች አማካይነት በሚካሄድ የመሬት ...

Read More »

አቶ ሀይለማርያም ካቢኔያቸውን መሰየም አልቻሉም

ጥቅምት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአዲሶቹን ጠቅላይ ሚኒስትሮች ሹመት ተከትሎ በኢህአዴግ ውስጥ የተፈጠረው የስልጣን ሽኩቻና አለመግባባት ሊፈታ ባለመቻሉ፤ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ካቢኔያቸውን ለመሾም አለመቻላቸውን በግንባሩ ውስጥ የሚገኙ የኢሳት ምንጮች ጠቆሙ። አቶ ሀይለማርም ደሳለኝና አቶ ደመቀ መኮንን ጠቅላይ ሚኒስትርና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተደርገው በተመረጡበት ዕለት ምሽት በሂልተን ሆቴል በጋራ መግለጫ የሰጡት አቶ በረከት ስምዖንና አቶ ሬድዋን ሁሴን ፤ አዲሱ ...

Read More »

ኦህዴድ ለሌላ አስቸኳይ ስብሰባ አዳማ ከተተ

ጥቅምት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) አመራር አሁንም እንዳልተረጋጋ እየተነገረ ሲሆን፤ የድርጅቱ አመራር አባላት በመስከረም አጋማሽ ተጀምሮ ያልተቋጨውን ስበስባ ለመቀጠል አዳማ መክተታቸው ታውቋል። ከኢትዮጵያ የደረሱን መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከሆነ፤ ከወረዳ ጀምሮ የሚገኙት የድርጅቱ ከፍተኛ አመራር አባላትም በዚህ ስበሰባ እንደተካከቱ ለማወቅ ተችሏል። ቀደም ሲል በአቶ አባዱላ ገመዳ፤ ኩማ ደመቅሳና ጁነዲን ሳዶ ይመሩ የነበሩት ሶስት አንጃዎች ወደአራት ...

Read More »

የሰመጉና የሴቶች የህግ ባለሙያዎች ማህበር ገንዘብ እንዲወረስ የተወሰነው ውሳኔ ጸና

ጥቅምት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት፤ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ሰመጉ) እና የኢትዮጵያ ሴቶች የህግ ባለሙያዎች ማህበር ገንዘብ እንዲታገድና እንዲወረስ በበታች ፍ/ቤቶች የተወሰነውን ውሳኔ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ አጸና። የአገሪቱ ከፍተኛው የፍትህ አካል የሆነው ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚው ችሎት፤ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ባለስልጣን 20 ሚሊዮን ብር የሚደርሰውን የሁለቱን ድርጅቶች ገንዘብ እንዲታገድና እንዲወረስ የወሰነውና ቦርዱና ...

Read More »

ወደሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የሚገቡ ልጃገረዶች መጠን 30 ከመቶ ብቻ ነው

ጥቅምት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ ውስጥ ወደሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የሚገቡ ሴት ተማሪዎች ቁጥር ከአፍሪካ አማካይ እንኩዋን ያነሰ መሆኑ አሳሳቢ እንደሆነ፤ ፕላን ኢንተርናሽናል የተሰኘው አለማቀፍ ድርጅት ገለጸ። ድርጅቱ በዚህ ወር ባወጣው የዓለም የልጃገረዶች ሁኔታ የተመለከተ ዘገባ፤ በአንደኛ ደረጃ የተመዘገቡ ሴቶች ቁጥር ከ30 በመቶ ወደ75 በመቶ ቢያድግም፤ ከአንደኛ ደረጃ ወደሁለተኛ ደረጃ የሚሸጋገሩ ልጃገረዶች ቁጥር ግን 20 ከመቶ ብቻ ነው ...

Read More »