ወ/ሮ አዜብ ቤተ-መንግስቱን ለቀቁ

ጥቅምት ፲፬ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢትዮጵያ በ አቶ መለስ ምትክ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ከመረጠች ወራት ቢቆጠሩም ፤ ተሿሚው አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ለረዥም ቤተ-መንግስት መግባት ሳይችሉ መቆየታቸው ይታወሳል። ከ አቶ መለስ ሞት ከረዥም ጊዜ በሁዋላ ዘግይቶ የተሾሙት አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር  ወደ ቤተ-መንግስቱ መግባት ያልቻሉት ወይዘሮ አዜብ መስፍን ለመልቀቅ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው እንደነበርም ይታወቃል። በዚህም ምክንያት አቶ  ሀይለማርያም ከመኖሪያ ቤታቸው ...

Read More »

የቦዲ ብሄረሰብ አባላት 4 የፌደራል ፖሊስ አባላትን ገደሉ

ጥቅምት ፲፬ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአካባቢው ምንጮች እንደተናገሩት የከባድ መኪና ሾፌሮች 6 የቦዲ አባላትን በመግጨታቸው እና ቦዲዮች በወሰዱት እርምጃ 7 ሲቪሎችንና 4 የፌደራል ፖሊስ አባላትን ገድለዋል። በአካባቢው ከሚካሄደው የስኳር ልማት ጋር በተያያዘ በበቦዲና በመንግስት መካከል አለመግባባት እንዳለ በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወሳል። በአሁኑ ጊዜ ውጥረቱ በመጨመሩ በሁለት የፌደራል ፖሊስ ኦራል መኪና የተጫኑ ልዩ ሀይል ወደ አካባቢው አቅንቷል። የክልሉ ፖሊስ ...

Read More »

የፌዴራሉ አቃቤ ህግ በእነ ደሳለኝ እምቢአለ መዝገብ ስር ክስ በመሰረተባቸው አራት ተከሳሾች ላይ ምስክሮችን አሰምቶ ጨረሰ

ጥቅምት ፲፬ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ መንግስት” የሽብርተኛ ቡድን ነው” ካለው ግንቦት ሰባት ድርጅት ጋር ግንኙነት ነበራቸው፤ አባል መልምለው አሰልጥነዋል፤ የሽብር ጥቃትም ለመሰንዘር ሲያሴሩ ነበር>> ሲል የፌዴራሉ አቃቤ ህግ በእነ ደሳለኝ እምቢአለ መዝገብ ስር ክስ በመሰረተባቸው አራት ተከሳሾች ላይ ከትላንት በስቲያ ስምንት ምስክሮችን አሰምቶ ጨረሰ። የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት የአቃቤ ህግ ምስክሮችን የሰማው በሰኞ ...

Read More »

በኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሐመድ ኦመር ከሥልጣናቸው ተነሱ

ጥቅምት ፲፬ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ምክትል ፕሬዚዳንቱ አቶ አብዲፈታህ መሐመድ ሐሰን በተጠባባቂነት እየሠሩ ይገኛሉ፡፡ አቶ አብዲ መሐመድ ከሥልጣናቸው የተነሱት በክልሉ ያለውን የፀጥታ ሁኔታ በሚመለከት ኃላፊነታቸውን በብቃት ካለመወጣታቸው ጋር ተያይዞ እንደሆነ  ሪፖርተር ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል። የአቶ መለስ ዜናዊ አስከሬን ከብራሰልስ አዲስ አበባ  እንደገባ በመንግስት ሚዲያ በተገለጸበት ወቅት  ስቅስቅ ብለው ሲያለቅሱ የሚታዩት  አቶ አብዲ ከአቶ በረከት ስምዖን፣ ከአቶ ጁነዲን ...

Read More »

ከሚሴ በልዩ ሁኔታ በፌደራል ፖሊሶች ተወራለች

ጥቅምት ፲፫ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በደቡብ ወሎ ከሚሴ አካባቢ በፌደራል ፖሊሶች ከወትሮው በተለየ ሁኔታ መከበቦን ነዋሪዎች ገለጡ:: ከከሚሴ ኢሳት ሬዲዮ ያናገረው አንድ ሙስሊም እንደገለጠው የአካባቢው ሰዎች በግዴታ ስብሰባ እንዲያደርጉ ተጠርተው ሽብር ፈጥራችኋል፤ ከዚህ ተግባራችሁ ታቀቡ ያለበለዚያ ግድያው ይቀጥላል ብለው እንዳስፈራሯቸው ገልጠዋል:: ከትላንት በስቲያ በገርባ ፖሊሶች በሰላማዊ መንገድ ሰላማዊ ጥያቄ ባነሳው የሙስሊሙ ህዝብ ላይ ተኩስ ከፍተው ሁለት ሰው ...

Read More »

ፍኖተ-ነጻነት ጋዜጣ እንደገና መታተም ጀመረች

ጥቅምት ፲፫ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ በዛሬው እለት ዳግም ለአንባቢያን መቅረቧን የጋዜጣው አዘጋጅ ለኢሳት ሬድዮ አስታወቀ። ዳግም ለሕትመት በቅታ ዛሬ ለአንባቢያን የተሰራጨችው ፍኖተ-ነጻነት ጋዜጣ፤ በግል ማተሚያ ቤት መታተሟንም የጋዜጣው አዘጋጅ ብስራት ወልደሚካኤል ለኢሳት ገልጿል። የግል ማተሚያ ቤቱ ፍኖተ ነጻነትን በመደበኛ የጋዜጣዋ የቀድሞ መጠንና ቅርጽ ለማውጣት የወረቀት ችግር አለበት ያለው ጋዜጠኛ ብስራት፤ በዚህ ምክንያትም በኤ ፎር ...

Read More »

በቶሮንቶ የኢሳት የድጋፍ ጽ/ቤት ተከፈተ

ጥቅምት ፲፫ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የቶሮንቶና አካባቢው የኢሳት ድጋፍ ኮሚቴ ሥራውን በሚገባ ለማከናወንና ከህብረተሰቡ ጋር ሊያገናኘው የሚያስችል አዲስ የጽህፈት ቢሮ ትናንት ኦክቶበር 20, 2012 ከፈተ። በ2017 –B2 Danforth Ave. የተከፈተው ይህ ጽህፈት ቤት የተለያዩ ባለሙያዎችን በማሰባሰብ ኢሳትን በዜናና በልዩ ልዩ ፕሮግራሞች ከማገዝ በተጨማሪ; በገንዘብና በሃሳብ የሚደግፉ የህብረተሰቡ ክፍሎችን ለማስተባበር እንደሚጠቀምበት የኮሚቴው አባላት በምረቃው ስነስርዓት ላይ አስረድተዋል። ከሁለት ...

Read More »

በሊቢያ የሚገኙ ስደተኞች ጥቃት እየደረሰባቸው ነው

ጥቅምት ፲፫ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሊቢያ ቤንጋዚ በስደት የሚገኙ ኢትዮጲያውያንና ኤርትራዊያን በስደተኞች ላይ በደል እየደረሰባቸው መሆኑ ተገለጸ። ኢትዮጲያውያንና ኤርትራዊያን ስደተኞች በካምፕ ውስጥ እና በእስር ቤቶች ክፍተኛ በደል እየደረሰባቸው መሆኑ ተገለጿል። በቀይ ጨረቃ ካምፕ እና እስር ቤቶች በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በሊቢያ ወታደሮች ድብደባና አስገድዶ መድፈር እየደረሰባቸውም ነው ተብሏል። ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁና ከኢሳት ሬዲዮ ጋር ቃል የተመላለሱ ...

Read More »

በገርባ የተነሳውን ግጭት ተከትሎ በርካታ ወጣቶች እየታሰሩ ነው

ጥቅምት ፲፫ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌደራል ፖሊስ አባላት 4 ንጸሁን ዜጎችን ፣ ሁለቱን አስረው በመውስድና በመረሸን ሁለቱን ደግሞ በተቃውሞው ቦታ ላይ ከገደሉ በሁዋላ ፣ ሌሊቱን የቤት ለቤት አሰሳ በማድረግ በርካታ የገርባ ቀበሌ ወጣቶችን ማሰራቸው ታውቋል። ትናንት ምሽት በርካታ ወጣቶች ከተደበቁበት ቦታ በመሆን ስልኮችን ወደ ኢሳት ቢሮ እየደወሉ የፌደራል ፖሊስ አባላት ቤቶችን እያስከፈቱ ሲሰፈትሹ እንደነበር ድምጻቸውን ዝቅ በማድረግ ...

Read More »

የቡና ገበያ መቀዝቀዝ ነጋዴዎችንና አምራቹን ስጋት ላይ ከቷል

ጥቅምት ፲፫ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በጌዲዮና በሲዳማ ዞን በቡና ንግድ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች ለዘጋቢያችን እንደገለጡት የቡና ገበያ መቀዝቀዙ ለኪሳራ እየዳረጋቸው ነው። በ2004 ዓም በእረጥብ ቡና ግዢና በደረቅ ቡና መፈልፈያ የሳይት የቡና ማሽን የተከሉ ባለሀብቶች በደረሰባቸው ከፍተኛ ኪሳራ በ2005 ነሀሴ ውር መጀመር የነበረበት የቡና ማሽኖች እድሳትና የቡና ማድረቂያ አልጋ ስራ እስካሁን አለመጀመሩ በአጠቃላይ በንግድ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ጫና ...

Read More »