“የ11 ከመቶ የኢኮኖሚ እድገት ስሌትን ልንረዳው አልቻልንም” ሲሉ የአለም ባንክ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ተናገሩ

ጥቅምት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-መንግስት የሚናገረው 11 ከመቶ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት በምን ስሌት እንደመጣ ልንረዳ አልቻልንም፤ ምናልባት ችግሩ የማእከላዊ ስታቲስቲክስ ባለስልጣን አቅም ማነስ ሊሆን ይችላል ሲሉ፤ የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ጉዋንግ ዚ ቼን ተናገሩ። ዳይሬክተሩ ከአዲስ ፎርቹን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ የአይ ኤም ኤፍ እና የዓለም ባንክ የሚያወጣቸው ቁጥሮች ተመሳሳይ ቢሆኑም፤ የኢትዮጵያ መንግስት የሚሰጠው የ11 ከመቶ የኢኮኖሚ ...

Read More »

የኢትዮጵያ የገቢና ወጪ ልዩነት 7.5 ቢሊ ን ዶላር ደረሰ

ጥቅምት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የቡናና የቅባት እህሎች ሽያጭ በመቀነሱ ምክንያት የአገሪቱ የውጭ ንግድ ሽያጭ በ7 ከመቶ መቀነሱን ብሉምበርግ የተሰኘው የዜና ምንጭ ዘገበ። የንግድ ሚኒስቴር ዘገባን የጠቀሰው ብሉምበርግ እንደዘገበው አምና በዚህ ሰዓት የሶስት ወር የቡና ሽያጭ ከ200 ሚሊዮን ዶላር በላይ የነበረ ሲሆን፤ በዚህ አመት ግን ከ200 ሚሊዮን ዶላር ወርዷል ብሏል። መቀመጫው አዲስ አበባ የሆነው አክሰስ ካፒታል የተሰኘ ...

Read More »

የአዲስ አበባው ሲኖዶስ ስብሰባ ቀጥሏል፤ አዲስ አበባ በአራት አገረ-ስብከቶች ትከፈላለች

ጥቅምት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ የአገር ቤቱ ሲኖዶስ ስብሰባ እንደቀጠለ ሲሆን፤ ሲኖዶሱ በከፍተኛ ሙስና፤ በመልካም አስተዳደር እጦትና በጎሰኝነት የሚታመሰው የአዲስ አበባ አገረስብከት በአራት አገረ ስብከቶች እንዲከፈል መወሰኑ ታውቋል። በአመት ሁለት ግዜ የሚደረገው የሲኖዱ ስብሰባ፤ ባለፈው ሰኞ የተጀመረው የጥቅምቱ ስብሰባ፤ በእስካሁኑ ውሎው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የመከረ ሲሆን፤ የእርቀ ሰላሙ ጉዳይ፤ የአዲስ አበባ አገረ ስብከት ...

Read More »

በመላው አገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ጠንካራ ተቃውሞ አደረጉ

ጥቅምት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-1433ኛውን የኢድ አል አደሃ በአልን ምክንያት በማድረግ በመላው አገሪቱ የሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች ኢህአዴግ መራሹ መንግስት እየተከተለ ያለውን ፖሊሲ በመቃወም ድምጻቸውን አሰምተዋል። በአዲስ አበባ ስታዲየም ፣ በሀረር፣ በደሴ፣ አዳማ እና ሌሎችም አካባቢዎች የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጽህፈት ወይም መጅሊስ ተወካዮች ንግግር ለማድረግ ሳይችሉ ቀርተወዋል። በተለያዩ ከተሞች በርካታ ሙስሊም ወጣቶች እየታፈሱ መታሰራቸውም ታውቋል። በአዲስ ...

Read More »

የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመጓዝ ላይ የሚገኙ እስረኞች ለማምለጥ ባደረጉት ሙከራ በፖሊስ ጥይት ተገደሉ

ጥቅምት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአ/አ በተለምዶ ጦር ኃይሎች ቶታል እየተባለ በሚጠራ አካባቢ ወደሚገኝ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመጓዝ ላይ የሚገኙ እስረኞች ለማምለጥ ባደረጉት ሙከራ በፖሊስ ጥይት ተገደሉ፡፡ ሁለት እስረኞች በጥይት ተመተው ሞተዋል፡፡ ፖሊስ ዛሬ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ገደማ እስረኞቹን ፍ/ቤት ለማቅረብ በጉዞ ላይ እንደነበረና ፍ/ቤቱ አካባቢ ሲደርሱ ግን በርበሬ መሰል ነገር ፖሊሶቹ ዓይን ላይ በመበተን ለማምለጥ ...

Read More »

የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሠራተኞችን የመለስን ራዕይ ማሳካት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እያወያየ ነው

ጥቅምት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከፍተኛ ካድሬዎች በመሩት በነዚህ መድረኮች የመለስን ራዕይ ማሳካት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ሰራተኛው ግልጽ አቋም እንዲኖረው በይፋ ተነግሮታል፡፡ አቶ መለስ ካረፉ በኃላ ከከፍተኛ  ካድሬው ወደ መካከለኛና ወደ ዝቅተኛ አመራር ሲንከባለል የነበረው ይህው ውይይት የመንግስት ሰራተኞችንም ማካተቱ፣ ለሲቪል ሰርቪሱና ፖለቲካው መደበላለቅ ትልቅ መገለጫ መሆኑን ያነጋገርናቸው ሰራተኞች አስረድተዋል፡፡ አንድ የማዘጋጃ ቤቱ ሰራተኛ እንደተናሩት የተቀጠሩት የመንግስትን ...

Read More »

ኢሳት በሀረር የውሀ እጥረት መከሰቱን ከዘገባ በሁዋላ የክልሉ መስተዳደር በግምገማ እየታመሰ ነው

ጥቅምት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንዳመለከተው ኢሳት በሀረር ስላለው የውሀ ችግር ዘገባ ማቅረቡን ተከትሎ የክልሉ መስተዳደር ግምገማ ተቀምጧል። ግምገማውን ተከትሎም የክልሉ የውሀ ልማት ሀላፊ ከስልጣን በመነሳት   እስር ቤት መግባታቸውን ለማወቅ ተችሎአል። ግምገማው አሁንም ድረስ መቀጠሉን ለማወቅ ተችሎአል። ኢሳት በሀረር ያለው የውሀ ችግር ማህበራዊ ተቃውሞ ሊያስነሳ እንደሚችል መዘገቡ ይታወሳል።

Read More »

በመላ አገሪቱ የሚገኙ ተማሪዎች በባንዲራ ቀን በአል ላይ የአቶ መለስን ፎቶ ግራፍ ይዘው እንዲወጡ ታዘዙ

ጥቅምት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የትምህርት ሚኒስቴር ባስተላለፈው ትእዛዝ መሰረት በመላ አገሪቱ የሚገኙ ተማሪዎች የፈታችን ሰኞ በሚደረገው የባንዲራ ቀን በአል ላይ ጥቁር ሪባን በማሰርና የታላቁን መሪ የአቶ መለስ ዜናዊን ፎቶ ግራፍ ከፍ አድርጎ በመያዝ በአሉን እንዲያከብሩ ትእዛዝ አስተላልፎአል። በመጪው ጥቅምት 19 የሚከበረው የሰንደቅ ዓላማ ቀን የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ራዕይ ለማሳካት ቃል ኪዳናችንን በማደስ የምናከብረው ነው ሲሉ ...

Read More »

ወጣቱ ትውልድ በአንድነት ለሀገር እድገት እንዲቆም ጥሪ ቀረበ

ጥቅምት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አዲሡ ትውልድ ተቻችሎና ተከባብሮ ለሃገሩ በአንድነት እንዲቆምና እንዲሠራ አንጋፋው ኢትዮጲያዊ ዶክተር አክሊሉ ሐብቴ ጠሪ አቀረቡ። በሐገር ቤትና በውጭ ሐገር የሚገኙ የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶችን ለመሸምገል የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠሉንም ዶር አክሊሉ ሐብቴ አብራርተዋል።በአፄ ኃይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት የቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ የዛሬው አዲስ አበባ ፕሬዝዳንት የነበሩት በኋላም በሚንስትርነት እንዲሁም በአለም ባንክና በዩኒሴፍ ...

Read More »

የሙስሊም አመራሮች ፍርድ ቤት ቀረቡ

ጥቅምት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በእስር ላይ የሚገኙት የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አመራር አባላት ዛሬ ልደታ ፍርድ ቤት ቀርበው ያለ አንዳች ውሳኔ ለሰኞ ቀጠሮው መዛወሩ ተገለጠ።ምንጮቻችን ከአዲስ አበባ እንደዘገቡት የአመራሮቹ የፍርድ ሂደት ቀድሞ የሚታየው በአራዳ ፍርድ ቤት የነበረ ቢሆንም ዛሬ የቀረቡት ግን በልደታ ፍ/ቤት ነው ። የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አመራር አባላት በተከሰሱበት የሽብርተኝነት ወንጀል ለብይን ቀጠሮ የተሰጣቸው ...

Read More »