ሰበር ዜና በአማራ ክልል ቃሉ ወረዳ በደጋንና ገርባ ቀበሌዎች በፌደራል ፖሊስና በህዝቡ መካከል ግጭት ተነስቷል።

ሰበር ዜና

በአማራ ክልል ቃሉ ወረዳ በደጋንና ገርባ ቀበሌዎች በፌደራል ፖሊስና በህዝቡ መካከል ግጭት ተነስቷል።

ችግሩ የተፈጠረው የፌደራል ፖሊስ ሁለት የእስልምና ተከታይ ወጣቶችን ይዞ በማሰሩ ነው፡፡ የአካባቢው ህዝብም የወጣቶችን እስር በመቃወምና ወደ ፖሊስ ጣቢያ በማምራት በሀይል ወጣቶችን አስፈትቷል።  በአካባቢው የነበሩ የፌደራል  የወረዳ ፖሊሶች የህዝቡን ቁጣ በማየት ሸሽተው የነበር ሲሆን፣ የፌደራል ፖሊሶች ከእየአካባቢው በመሰባሰብ ወደ አካባቢው ተጉዘዋል

የፌደራል ፖሊስ አባላት አስለቃሽ ጭስ መስጊድ ውስጥ በመተኮስ ፣ 5 ሰዎችን ወስደው አስረዋል ። ከተያዙት መካከል ሼክ ሙሀመድ ሙሳ፣ አቶ ወሀብ፣ አቶ ሚኒሊክና አቶ ጃፋር ይገኙበታል። ህዝቡ ባደረገው ተቃውሞ የፌደራል ፖሊስ አባላት ከመስጊድ የወጡ ሲሆን  በአሁኑ ጊዜም በመስጊድ ውስጥ ያለውን ህዝብ ከበዋል። ህዝቡ ፖሊሶችን ወደ መስጊድ አናስገባም በማለት ተቃውሞውን እንደቀጠለ ነው።

በፌደራል ፖሊስ ተይዘው በህዝቡ ተቃውሞ ከተፈቱት መካከል አንደኛውን  አነገጋርነዋል

ውድ ተመልካቾቻችንና አድማጮቻችን አዳዲስ መረጃዎች እንደደረሱን እናቀርባለን።