ህዳር ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢትዮጵያ በመገንባት ላይ የምትገኘው የህዳሴ ግድብ የአባይ ተፋሰስ ሀገሮችን የአባይ ውሀ ድርሻ በጽኑ የሚጎዳ በመሆኑ የጋራ ስምምነት ላይ ሊደርስ ይገባል ሲሉ አንድ የፖለቲካ ምሁር ገለጹ። ግድቡ ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያ የአባይን ወንዝ ውሀ 86 በመቶ በመቆጣጠር በአባይ ላይ የበላይነቱን ትይዛለችና፤ በተለይ ግብጽና ሱዳን ከወዲሁ መፍትሄ ሊያበጁ ይገባል ብለዋል። ኢትዮጵያ በበኩሏ ከህዳሴው ግድብ ግብጽና ሱዳን ይጠቀማሉ ...
Read More »በሀገረማርያም በተደረገ ስብሰባ ህዝቡ የመንግስትን የአፈና አገዛዝ ነቀፈ
ህዳር ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቦረና ዞን በሀገረማሪያም ከተማ ህዳር 14 ቀን 2005 ዓም “ከተማዋን ለማልማት” በሚል አጀንዳ በተጠራ ስብሰባ ላይ ነው ህዝቡ የ21 አመታት የአፈና አገዛዝ በቃን በማለት የተናገረው። የኢሳት ወኪል እንደዘገበው የዞን እና የወረዳ ባለስልጣናት ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ከ500 በላይ ሰዎችን ሰብስበው የ2004 ዓም አፈጻጸም ግምገማንና የ2005 ዓም እቅድን ይፋ አድርገዋል። ባለስልጣናቱ ለ2005 ዓም ለከተማዋ ...
Read More »የቆዳ እንዱስትሪው በጨው እጥረት አደጋ ላይ ነው ተባለ
ህዳር ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዚህ ዓመት ከኤክስፖርት 200 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስገባ እቅድ የተያዘለት የቆዳ ኢንደስትሪ በጨው አቅርቦት እና በተለያዩ ግብዓቶች እጥረት አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱን የዘገበው ሪፖርተር ነው የ ቆዳ ኢንዱስትሪዎች ማህበር በ አምስት ወር 150 ሺህ ኩንታል ቸው ሊደርሰን ሲገባ፤ያገኘነው ግን አምስት ሺህ ኩንታል ብቻ ነው አለ። የአፋር ክልል በበኩሉ፦-<< ምንም ዓይነት የ አቅርቦት ችግር አልተፈጠረም> ...
Read More »ስዊድን ኢትዮጵውያውያን ጥገኝነት ጠያቂ ጋዜጠኞችን ወደ አገራቸው እንዳትልክ የስዊድን ጋዜጠኛ ጠየቀ
ህዳር ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከአመት በላይ በቃሊቲ እስር ቤት ታስሮ የተፈታው ዮሃን ፐርሹን ይህን ያስገነዘበው ትናንት ባለፈው ሳምንት በስቶክሆልም ስዊድን ከተማ በሚካሄደው ዓመታዊው ታላቁ የስዊድሽ ጋዜጠኞች ሽልማት ስነስርዓት ላይ ሲሆን በዚሁ ወቅት እሱና ባልደረባው ማርቲን ሺብዬ ከእስር ተፈተው በነጻነት እንደልባቸው ለመንቀሳቀስ ቢችሉም በአሁን ሰዓት በቃሊቲ እና በሌሎች እስር ቤቶች በመማቀቅ ላይ የሚገኙት ኢትዮጵያውያን የህሊና እስረኞች ጉዳይ እጅግ ...
Read More »የግብጹ መሪ የአገሪቱን ዳኞች ሊያነገግሩ ነው
ህዳር ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የግብጽ ፕሬዚዳንት ሙሀመድ ሙርሲ ባለፈው ሳምንት ያወጡትን አዲስ ድንጋጌ የተቃመው ግብጻውያን አደባባይ በመውጣት ተቃውሞአቸውን መግለጻቸውን ተከትሎ ነው ፕሬዘዳንቱ ከከፍተኛ ዳኞች ጋር ለመነጋገርና ችግሩን ለመፍታት ቃል የገቡት። ፕሬዚዳንቱ ያወጡት ህግ ዳኞች እርሳቸው የሚያወጡትን ህግ እንዳይቀለብሱ የሚያስጠነቀቅ ነው። ይህን ድንጋጌ የተቃወሙ ዳኞች ህዝቡን ለተቃውሞ ጠርተዋል። ያልተጠበቀ ተቃውሞ የገጠማቸው አዲሱ ፕሬዚዳንት ውሳኔው በዲሞክራሲአዊ መንገድ የተመረጡትን ...
Read More »ከሁለት ልጆቿ ጋር የቤት እመቤቷን ገድለዋል የተባሉ የቅርብ ዘመዶች በቁጥጥር ስር ዋሉ
ህዳር ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሻሸመኔ ከተማ ሀይማኖት ደሳለኝ የተባለች የቤት እመቤት ባለፈው ሀሙስ ማንነቱ ባልታወቀ ግለሰብ በተኛችበት ከሁለት ልጆቿ ጋር በመጥረቢያ ተቆራርጣ የእናትየውና የልጆቹ ምላሶች ተቆርጠውና አይናቸውም ወጥቶ መገደላቸውን መዘገባችን ይታወሳል። ከፖሊስ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው በግድያው ከተያዙት መካከል የቤት እመቤቷ እናት አንዷ ናቸው። እናትየው በልጃቸው ላይ ሲዝቱ እንደነበር መታወቁ፣ በለቅሶው ጊዜም አርፍደው መምጣታቸውንና ከሌሊቱ ስድስት ሰአት ላይ ...
Read More »የሰማዕቱ የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ለባቡር ሀዲድ ግንባታ ሲባል ይፈርሳል መባሉ ከፍተኛ ህዝባዊ ቁጣ ቀሰቀስ
ህዳር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-መንግስት በበኩሉ ሐውልቱ ለደህንነቱ ሲል ከተነሳ በሁዋላ ወደነበረበት ስፍራ ይመለሳል እያለ ነው። በአዲስ አበባ ውስጥ ሊሠራ በታቀደ የ ከተማ ውስጥ የባቡር ሀዲድ ሥራ ምክንያት የዓፄ ምኒልክና የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ሊፈርሱ የመቻላቸው ወሬ አስቀድሞ የሾለከው ፤ለምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ቅርበት ካላቸው ምንጮች ነው። እነዚህ የዘርፉ ሙያተኞች በ አምስት ዓመቱ የልማትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ መሰረት በ አዲስ አበባ ...
Read More »በሙስሊም ኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰው ሰቆቃ እየጨመረ ነው ተባለ
ህዳር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-መንግስት ሙስሊሙ ላነሳው ጥያቄ ተገቢውንና ሰላማዊ የሆነ መፍትሄ ከመስጠት ይልቅ የሀይል አማራጭ መጠቀሙ፣ በሙስሊሙ ላይ የሚደርሰው በደል እየከፋ እንዲሄድ አድርጎታል። የአካባቢው ነዋሪዋች እንደተናገሩት ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በአማራ ክልል የኦሮሚያ ዞን ዋና ከተማ በሆነችው ከምሴ የፌደራል ፖሊስ አባላት ቤት ለቤት በመግባት ከ60 በላይ ሙስሊም ኢትዮጵያውያንን በመያዝ አስረዋል። በተያዙት ወጣቶች ላይ የሚደርሰው እንግልት እየጨመረ መምጣቱን ...
Read More »በሀረር ከተማ ከ500 በላይ ሱቆች ይፈርሳሉ መባሉን ተከትሎ አለመረጋጋት መፈጠሩ ተሰማ
ህዳር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሀረር ከተማ ሸዋ በር እየተባለ በሚጠራው የገበያ ማእከል የሚገኙ ከ500 ያላነሱ ሱቆች ይፈርሳሉ በመባሉ በዛሬው እለት አለመረጋጋት ተፈጥሮ እንደነበር ዘጋቢዎቻችን ከስፍራው ገልጸዋል። አብዛኞቹ ሱቆች ካለፉት 30 አመታት ጀምሮ በጉራጌ ተወላጆች የተያዙ ሲሆን፣ ክልሉ ነጋዴዎችን በማስወጣት ለአካባቢው ተወላጆች ለመስጠት እንዳቀደ መነገሩን ተከትሎ ነው አለመረጋጋቱ የተፈጠረው። ተገቢው ካሳ እና ምትክ ቦታ ሳይሰጥ ሱቆችን ለቀው እንዲወጡ ትእዛዝ ...
Read More »አንዲት እናት ከሁለት ልጆቿ ጋር በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደለች
ህዳር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሻሸመኔ ከተማ ሀይማኖት ደሳለኝ የተባለች የቤት እመቤት ከትናንት በስቲያ ማንነቱ ባልታወቀ ግለሰብ በተኛችበት ከሁለት ልጆቿ ጋር በመጥረቢያ ተቆራርጠው መገደላቸው ተዘገበ። የእናትየውና የልጆቹ ምላሶች መቆረጣቸውን፣ አይናቸውም መውጣቱን የአይን እማኞች ለኢሳት ገልፀዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች በነቂስ በመውጣት በዛሬው እለት ሟቾቹን የቀበሩ ሲሆን፣ ከቀብር በሁዋላም የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። . የቤት ሰራተኛዋ ወንጀሉን በመፈጸም በኩል የመጀመሪያዋ ተጠርጣሪ ሆናለች።
Read More »