ከሁለት ልጆቿ ጋር የቤት እመቤቷን ገድለዋል የተባሉ የቅርብ ዘመዶች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ህዳር ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭  ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በሻሸመኔ ከተማ ሀይማኖት ደሳለኝ የተባለች የቤት እመቤት ባለፈው ሀሙስ ማንነቱ ባልታወቀ ግለሰብ በተኛችበት ከሁለት ልጆቿ ጋር በመጥረቢያ ተቆራርጣ የእናትየውና የልጆቹ ምላሶች ተቆርጠውና አይናቸውም ወጥቶ መገደላቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

ከፖሊስ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው በግድያው ከተያዙት መካከል የቤት እመቤቷ እናት አንዷ ናቸው። እናትየው በልጃቸው ላይ ሲዝቱ እንደነበር መታወቁ፣ በለቅሶው ጊዜም አርፍደው መምጣታቸውንና ከሌሊቱ ስድስት ሰአት ላይ ውጭ መታየታቸው ነው ለጥርጣሬ በር ከፍቶ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ የተደረገው። ቤቱን ዘግታ የጠፋችው የቤት ሰራተኛም በቁጥጥር ስር ውላለች። የሟችን ሞባይልና አንገት ሀብሎች ይዛ መገኘቱዋንም ከፖሊስ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።   ከሟች እናት ጋር ግንኙነት አለው የተባለ ሌላ ሰውም በቁጥጥር ስር ውሎአል።

የሟች እህት ታስራ መለቀቁዋን ለማወቅ ተችሎአል።