አንዲት እናት ከሁለት ልጆቿ ጋር በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደለች

ህዳር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭  ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በሻሸመኔ ከተማ ሀይማኖት ደሳለኝ የተባለች የቤት እመቤት ከትናንት በስቲያ ማንነቱ ባልታወቀ ግለሰብ በተኛችበት ከሁለት ልጆቿ ጋር በመጥረቢያ ተቆራርጠው መገደላቸው ተዘገበ።

የእናትየውና የልጆቹ ምላሶች መቆረጣቸውን፣ አይናቸውም መውጣቱን የአይን እማኞች ለኢሳት ገልፀዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች በነቂስ በመውጣት በዛሬው እለት ሟቾቹን የቀበሩ ሲሆን፣ ከቀብር በሁዋላም የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። .

የቤት ሰራተኛዋ ወንጀሉን በመፈጸም በኩል የመጀመሪያዋ ተጠርጣሪ ሆናለች።