መጋቢት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከሁለት ዓመት በፊት ኢሳት በወ/ሮ አዜብ መስፍን የእህት ልጅ በወ/ሮ አቲኮ ስዩም አምባየ የተመሰረተው ኦርቺድ ቢዝነስ ግሩፕ በጣሊያኑ ሳሊኒ ኮንስትራክሽን አማካኝነት በሚገነቡት ግልገል ጊቤ አንድ እና ግልገል ጊቢ ሁለት የሀይድሮ ኤሌክትሪክ ፕሮጀክቶች ስሚንቶ እና የግንባታ እቃዎችን እንዲሁም ከፍተኛ ማሺነሪዎችን በማቅረብ ከፍተኛ የሆነ ትርፍ ማጋበሱን ዘግቦ ነበር። በአባይ ወንዝ ላይ የሚሰራውን የህዳሴውን ግድብ ...
Read More »የኢህአዴግ የመተካካት ዕቅድ በተግባር እየከሸፈ ነው ተባለ
መጋቢት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢህአዴግ ያወጣው የአመራር መተካካት ከመፈክር ባለፈ እየተተገበረ አለመሆኑን ለግንባሩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ የግንባሩ ከፍተኛ አመራሮች ከ17 ዓመታት በላይ በጫካ ትግል ላይ ዕድሜያቸውን ያሳለፉ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በአሁኑ ወቅት በተለይ ከዕድሜና ሕመም ጋር ተያይዞ ብዙዎቹ የያዙትን ከፍተኛ ኃላፊነት መወጣት የማይችሉበት ደረጃ ላይ እየደረሱ በመሆናቸው በሌላ አመራር የመተካታቸው ጉዳይ ታምኖበት የአፈጻጸም ፕሮግራም ወጥቶለት ...
Read More »የአፍሪካ መዲና-አዲስ አበባ የውሀ እና የመብራት ያለህ እያለች ነው
መጋቢት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የውኃና የኤሌክትሪክ መቆራረጥ ችግር ከጊዜ ወደ ጊዜ ይሻሻላል በሚል በትዕግስት ቢጠባበቁም፣ እየባሰበት እንደመጣና መፍትሔ በማጣታቸው ግራ መጋባታቸውን በርካታ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች መግለፃቸውን ሪፖርተር ዘገበ። እንደ ጋዜጣው ዘገባ ውኃና ኤሌክትሪክ ከዓመት እስከ ዓመት ተቋርጦባቸው እንደማያውቅ ሲነገርላቸው የነበሩ በተለይ በቤተ መንግሥት አቅራቢያ ያሉ ነዋሪዎች ሳይቀሩ አሁን ውኃ እያገኑ ያሉት በሳምንት ለሦስትና አራት ቀናት ብቻ ...
Read More »ፕሬዚዳንት ኦባማ እስራኤልን እየጎበኙ ነው
መጋቢት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አሜሪካዊው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ እስራኤል ሲገቡ ፣ አገራቸው ለእስራኤል ጠንካራ ወዳጅ አገር መሆኑዋን ገልጸዋል። እስራኤል እንደ አሜሪካ ጠንካራ ወዳጅ የላትም ብለዋል ፕሬዚዳንቱ። ለቅድስቲቱ አገር ሰላም መምጣት እንዳለበትም ተናግረዋል። ፕሬዚዳንቱ ሀሙስ ወደ ዌስት ባንኩዋ ራማላህ ከተማ ተጉዘው ከፍልስጤም ባለስልጣናት ጋር ይነጋገራሉ። የፕሬዚዳንት ኦባማ ዋና የጉብኝት አላማ በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን የቆየ ወዳጅነት ማደስ ...
Read More »በባህርዳር ጊዮን ሆቴል ጉዳይ የተነሳ የአማራ ክልል ባለስልጣናትና ህወሀት ተፋጠዋል
መጋቢት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የዛሬ 21 አመት ህወሀት/ ኢህአዴግ አሸንፎ አዲስ አበባን ከመቆጣጠሩ በፊት ለህወሀት በመሰለል ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረጋቸው የሚታወቁት በባህርዳር ከተማ ነዋሪ የሆኑት የአድዋው ተወላጅ እና የአቶ መለስ ዜናዊ የቅርብ ዘመድ አቶ ወልዱ፣ ለህወሀት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ፣ አቶ መለስ ዜናዊ የመንግስት ንብረት የሆነውን ጊዮን ሄቴልን በ5 ሺ ብር ኪራይ እንዲሰሩበት በገጸ በረከት ስጥተዋቸው ነበር። አቶ ወልዱ ...
Read More »የህዝቡ የፖለቲካ ተሳትፎ ካልጎለበተ በኢትዮጵያ ጠንካራ ለውጥ አይመጣም ሲሉ የለጋሽ አገራት ቡድን አስታወቀ
መጋቢት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ተቀማጭነቱ አዲስ አበባ የሆነው የለጋሽ አገራት ቡድን ባወጣው ሪፖርት እንዳመለከተው የኢትዮጵያ መንግስት አገሪቱን ወደ መካከለኛ ገቢ አገር ለመቀየር ማቀዱ በአወንታዊነት የሚመዘገብ ቢሆንም፣ ይህን አላማ እውን ለማድረግ መንግስት የህዝቡን ተሳትፎ ለመጨመር፣ የመልካም አስተዳደር ማሻሻያ ለማድረግ፣ የዲሞክራሲ ተቋማት እንዲገነቡና እንዲጠናከሩ ለማድረግ ጠንካራ እርምጃዎችን መውሰድ አለበት ብሎአል። ሪፖርቱ አክሎም መንግስት የመቻቻል ባህል እንዲጎለብትን ልዩነቶችን ለማስተናገድ ካልቻለ ...
Read More »የአለም ባንክ በኢትዮጵያ ጉዳይ የሚያደርገውን ምርመራ አራዘመ
መጋቢት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአለም ባንክ በሂውማን ራይትስ ወች የቀረበለትን ጥያቄ መነሻ በማድረግ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚከተለው ፖሊሲ የተነሳ ሰብአዊ መብቶች መጣሳቸውን ለማረጋገጥ የጠራው ስብሰባ መራዘሙን ሂውማን ራይትስ ወች ዘግቧል። ድርጅቱ በድረገጹ ላይ ባሰፈረው ዘገባ ” የአለም ባንክ ፕሮጀክት ከሰፈራ ፕሮግራም ጋር የተያያዘ ነው። ሂውማን ራይትስ ወች የአለም ባንክ ከሰፈራ ጋር በተያያዘ የሚከተለውን ፖሊሲ እንዲመረምር ጥያቄ ማቅረቡን አስታውሷል። ...
Read More »የግራዚያኒን ሀውልት ግንባታ በመቃወም ታሰረው የተፈቱ ዜጎች ዘራቸው እየተጠቀሰ መሰደባቸው ታወቀ
መጋቢት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፋሽስት ኢጣሊያ መንግስት ወኪል በመሆን በአንድ ቀን ከ30 ሺ በላይ ኢትዮጵያውያንን በስድስት ኪሎ አደባባይ የጨፈጨፈውን የሮዶልፎ ግራዚያኒን ሀውልት ለማቆም እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ለመቃወም ትናንት እሁድ በስድስት ኪሎ የተሰባሰቡ የባለራእይ ወጣቶች ማህበር አባላት፣ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን እንዲታሰሩ ተደርጓል። የጸጥታ ሀይሎች ታዋቂውን የህግ ባለሙያና ፖለቲከኛ ዶ/ር ያእቆብ ሀይለማርያምን ጨምሮ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ...
Read More »በኢትዮጵያ ዋና ዋና ከተሞች ፍተሻው ተጠናክሯል
መጋቢት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢህአዴግ አባል ድርጅቶችን ስብሰባ ተከትሎ በአዋሳ፣ አዳማ እና ባህርዳር ጥብቅ ፍተሻ መካሄዱን የአይን እማኞች ገለጹ በተለይ በአዳማ እና በአዋሳ ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ ፍተሻ ከቅዳሜ ከሰአት ጀምሮ እስከ ዛሬ መካሄዱ ታውቋል። ወደ አዋሳ ከተማ የሚገቡ ሰዎች በጥብቅ የተፈተሹ ሲሆን፣ በከተማዋ ውስጥም በአንዳንድ ቦታዎችም ፍተሻዎች ተደርገዋል። በአዋሳ የተለያዩ ቦታዎች ድንኳኖች ተተክለው የኢህአዴግ ደጋፊዎች ሲበሉና ...
Read More »የአልጀዚራን ድረ-ገጽ በኢትዮጵያ እንዳይታይ ታገደ
መጋቢት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ መንግስት የ አልጀዚራን እንግሊዝኛ እና ዐረብኛ ድረ-ገጾች ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይታዩ ማገዱን አልጀዚራ ዘገበ። ድርጊቱ፤የ ኢትዮጵያ መንግስት እንደ አዲስ እያደረበት ከመጣው ፍርሀት አኳያ ሚዲያዎችን ጸጥ ለማሰኘት እየወሰደ ያለው እርምጃ አካል ነው ብሏል- አልጀዚራ። አልጀዚራ ከጎግል የተቀበላቸው ዳታዎች እንደሚያሳዩት፤ባለፈው ሀምሌ ወር እስከ 50000 ደርሶ የነበረው እንግሊዝኛ ድረ-ገፁን የሚጎበኙ ኢትዮጵያውያን ቁጥር በመስከረም ወር በአስደንጋጭ ሁኔታ ...
Read More »