ሚያዚያ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ የዜጐችን መፈናቀል ለማስቆምና በዜጐች መፈናቀልና እንግልት ላይ ተሣታፊ የሆኑ የመንግስት ሀላፊዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ የሚያግዝ ፒቲሽን ለማስፈረም እየተዘጋጀ መሆኑን አስታወቀ፡፡ ፓርቲው፤ኢትዮጵያዊ ምሁራን የሚሣተፉበትና መፈናቀሉ እያስከተለ ባለው ጉዳት ዙሪያ በመወያየት የመፍትሄ ሀሣብ የሚመነጭበት አገር አቀፍ የፓናል ውይይት እንደሚካሄድም ገልጿል፡፡ አዲስ አድማስ የፓርቲው ን የህዝብ ግንኙነት ሀላፊና የኤዲቶሪያል ቦርድ አባል ...
Read More »በሱዳን በተካሄደው የተኩስ ልውውጥ አንድ ኢትዮጵያዊ ወታደር ተገደለ
ሚያዚያ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ደቡብ ሱዳንና ሰሜን ሱዳንን እያወዛገበ ባለው በነዳጅ ዘይት በበለጸገችው የአቤይ ግዛት በማጆክና በሚሴሪያ ጎሳዎች መካከል በተደረገ ጦርነት 20 ሰዎች ሲሞቱ፣ በአካባቢው በሰላም አስከባሪነት የተሰማራ አንድ ኢትዮጵያዊ ወታደር ተገድሎ ሌሎች ሁለት ደግሞ ቆስለዋል። ማጆክ የተባለው ጎሳ ደቡብ ሱዳንን የሚደግፍ ሲሆን ሚሴሪያ ደግሞ ሰሜን ሱዳንን ይደግፋል። በግጭቱ የተገደለው ኢትዮጵያዊ ወታደር ስም አልተገለጸም፣ የኢትዮጵያ ...
Read More »የሸቀጦች ዋጋ የተረጋጋ ቢመስልም አሁንም ከህብረተሰቡ አቅም በላይ ሆነዋል
ሚያዚያ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የትንሳዔ በዓል ገበያ በአዲስ አበባ የተረጋጋ ቢመስልም አሁንም የሸቀጦች ዋጋ በተለይ ከዝቅተኛው ኀብረተሰብ አቅም በላይ መሆኑን በሾላ እና በሳሪስ ገበያ ትላንትና ያሰባሰብናቸው መረጃዎች አመልክተዋል፡፡ በዚሁ መሰረት የጤፍ ዋጋ ማኛ ከ1850-2000ብር በኩንታል፣ነጭ ጤፍ ከ1750-1800፣ሰርገኛ ከ1600-1700 ዋጋ ይጠየቅበታል፡፡ ቅቤ እንደረጃው ከ180-195 ብር በኪሎ በተለይም ለጋ ቅቤ የሸኖ በኪሎ እስከ 200 ብር ፣ ዶሮ የአበሻ ...
Read More »አንድነት ፓርቲ የፖለቲካና የህሊና እስረኞች በአፋጣኝ እንዲፈቱ ጠየቀ
ሚያዚያ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፓርቲው ባወጣው መግለጫ ሚያዚያ 24 ቀን 2005 ዓ.ም ይግባኝ ሰሚ ችሎት በእነአንዷለም አራጌ ፍርድ ላይ የሰጠው ውሳኔ ፍ/ቤቶች የገዥው ፓርቲ ጉዳይ አስፈፃሚዎች እንጅ ገለልተኛ ተቋማት አለመሆናቸውን ያሳየ ነው ብሎአል። ፓርቲው “ሽብርተኝነት በናይጀሪያ፣ በአፍጋኒስታን እና በፓኪስታን በእየለቱ የምንሰማው እንጅ የኢትዮጵያ ችግር አይደለም በማለት ገልጾ የከፍተኛው ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ወጣቱን ፖለቲከኛና ከፍተኛ አመራር ...
Read More »ጋዜጠኛ መስፍን ነጋሽ የሪፖርተርስ ዊዝአውት ቦርደርስ የ2013 ሽልማት አሸናፊ ሆነ
ሚያዚያ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በስዊድን በስደት ላይ የሚገኘው የቀድሞው የአዲስ ነገር ጋዜጣ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ መስፍን ነጋሽ ሽልማቱን ያገኘው በኢትዮጵያ በሽብረተኝነትና በህገወጥ መንገድ ወደ አገር በመግባት ተከሰው ከአንድ አመት በላይ ታስረው ከተፈቱት የስዊድን ጋዜጠኞች ከሆኑት ማርቲን ሽብየ እና ጆሀን ፒርሰን ጋር በጋራ በመሆን ነው። ጋዜጠኛ መስፍን በውጭ አገር ሆኖ ለፕሬስ ነጻነት በመታገሉ ለሽልማት እንደበቃ ድርጅቱ አስታውቋል። ...
Read More »አለማቀፍ መንግስታት እና ድርጅቶች በእነ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና አንዱአለም አራጌ ላይ የተላለፈውን ውሳኔ አወገዙ
ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለእየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በአል በሰላም አደረሳችሁ ሚያዚያ ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በወጣቱ ፖለቲከኛ አንዱአለም አራጌ፣ በእውቁ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ በናትኤል መኮንን፣ ክንፈሚካኤል ደበበ ፣ ምትኩ ዳምጤ ፣ ዮሃንስ ተረፈ ፣ ሻምበል የሺዋስ ይሁን አለም እንዲሁም አንዱአለም አያሌው ላይ የስር ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ውሳኔ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሚያዚያ 24፣ 2005 ዓም ማጽደቁ አለማቀፍ ...
Read More »የታዋቂው ጸሀፊ አስገደገ ገብረስላሴ ሁለተኛ ልጅ ታሰረ
ሚያዚያ ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የህወሀትን የበረሀ ትግል ታሪክ የሚዘክረውን ገሀዲ ቊጥር አንድ፣ ሁለት እና ሶስት የሚሉ መጽሀፎችን ከመጻፍ በተጨማሪ በትግራይ ውስጥ የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን በማጋለጥ የሚታወቁት አቶ አስገደ ገብረስላሴ ሁለተኛ ልጅ ታስሯል። የ28 አመቱ የማነ አስገደ ገብረስላሴ የሶፍት ዌር ኢንጂነረግ ምሩቅ ሲሆን፣ በውቅሮ በመምህርነት ሙያ ተቀጥሮ ነበር። አዲሱን ስራውን ሲጀምር አቶ አስገደ ልጅ መሆኑ በመታወቁ ...
Read More »የፌደራሉ ጠቅላይ ፍድር ቤት በአቶ አንዱዓለም አራጌ መዝገብ በተከሰሱት የህሊና እስረኞች ላይ የስር ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ውሳኔ አጸና
ሚያዚያ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሀሙስ ሚያዚያ 24 ቀን 2005 የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በወጣቱ ፖለቲከኛ አንዱአለም አራጌ፣ የ2012 የፔን ኢንተርናሽናል ሽልማት አሸናፊ በሆነው እውቁ ጋዜጠኛ እስክንድ ነጋ እና በሌሎችም የፖለቲካ እስረኞች የቀረበውን የይግባኝ አቤቱታ ውድቅ አድርጎ የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን የ18 ዓመት እስር ውሳኔ አጽንቷል። መሀል ዳኛው አቶ ዳኜ መላኩ ለረጅም ጊዜ ቀጠሮ ሲሰጡ ከቆዩ በሁዋላ ...
Read More »የታላቁ ሰማእት የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ተነሳ
ሚያዚያ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከአዲስአበባ የቀላል ባቡር ዝርጋታ ጋር በተያያዘ ይነሳል በመባሉ ከፍተኛ ተቃውሞ አስነስቶ የነበረው የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ዛሬ ለዓመታት ከቆመበት የክብር ቦታ ተነሳ፡፡ መንግስት ሐውልቱ በድንገት ለማንሳት በሞከረበት ሰዓት የአዲስአበባ ሕዝብ ያለምንም ጥሪ በመሰባሰብ ሒደቱን የተከታተለ ሲሆን ሐውልቱ ከተነሳ በኋላ በእንጨት ሳጥን ውስጥ ታሽጎ በሎቤይድ ተሸከርካሪ ተጭኖ ወደ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ቅጥር ግቢ ...
Read More »የመከላከያ ባለስልጣናት በደን ጭፍጨፋው ዋነኛ ተሳታፊዎች ሆነዋል ተባለ
ሚያዚያ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በክብረ መንግስት ከተማ ዙሪያ የሚገኙ ነዋሪዎች ” የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊት ባለስልጣናት ከአካባቢው ደላሎች ጋር በመመሳጠር በእየለቱ በትላለቅ መኪኖች ጣውላዎችን እየጫኑ እንደሚያጓጉዙ” ገልጸዋል። ዛፎችን መቁረጥ እና ከክልል ክልል ማስተላለፍ ህገወጥ ቢሆንም የመከላከያ ባለስልጣናት ግን በዚሁ ንግድ ግንባር ቀደም ተዋናዮች ሆነዋል ብለዋል ነዋሪዎቹ። የመከላከያ መኪኖች በመንገድ ላይ የማይፈተሹ በመሆኑ ፣ ባለስልጣናቱ ጣውላዎችን እየጫኑ ወደ ...
Read More »