በቦና ወረዳ ከ40 በላይ ሰዎች ታፍሰው ተወሰዱ

ግንቦት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሰሜን ጎንደር ዞን በቦና ከተማ ሚያዚያ 29 ቀን ፣ 2005 የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ከ40 በላይ ሰዎች በመከላከያ ሰራዊት አባላት ታፍሰው የተወሰዱ ሲሆን ከ8 ያላነሱ ሰዎች ደግሞ በደረሰባቸው ከፍተኛ ደብደባ በጽኑ ቆስለዋል። ግጭቱ የተፈጠረው በቅጽል ስማቸው አቶ በደሌ የተባሉ ባለሀብት ማህበረሰቡ የሚጠቀምበትን የምንጭ ውሀ በማጠር ለራሳቸው የከብት ማድለብ ስራ ሊጠቀሙበት ማሰባቸውን ህብረተሰቡ በመቃወሙ ነው። ህዝቡ ...

Read More »

የገቢዎችና የጉምሩክ ባለስልጣን ዋና እና ምክትል ዳይሬክተሮችን ጨምሮ 16 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን መንግስታዊ መገናኛ ብዙሀን ዘገቡ

ግንቦት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ቀደም ሰል የገቢዎች ሚኒስትር ዴኤታ የነበሩትና ሚኒስቴሩ በበለስልጣን መስሪያ ቤት ሆኖ ሲዋቀር ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙት አቶ መላኩ ፋንታ፣ ምክትል ዳይሬክተሩ አቶ ወልደዋህድ ገብረጊዮርጊስ እና ሌሎች ከ 10 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር የዋሉት በሙስና ተጠርጥረው እንደሆነ መንግስት ገልጿል። የ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዜና አቅራቢ አጠቃላይ የታሰሩት ሰዎች 12 መሆናቸውን ሲገልጽ፤ዝርዝር ዜናውን ያነበበው ሪፖርተር ታሳሪዎቹ 16 መሆናቸውን ...

Read More »

በአውሮፓ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በአውሮፓ ህብረት ጽህፈት ቤት ፊትለፊት የተቃውሞ ሰልፍ ሊያደርጉ ነው

ግንቦት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያውያን ማህበር በኔዘርላንድስ ከቤልጂየም የኢትዮጵያውያን ማህበር ጋር በመተባበር የፊታችን ረቡእ ፣ እኤአ ሜይ 15፣ 2013 በብራሰልስ በሚገኘው በአውሮፓ ህብረት ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚያደርግ ለኢሳት በላከው ደብዳቤ አስታውቋል።   ሰልፉ በአማራ ተወላጆች ላይ በተደጋገሚ እየተፈጸመ ያለውን የማፈናቀል ዘመቻ ፣ በልማት ስም የአፋር፣ የጋምቤላ እና የሌውንም ህዝብ ህልውና ለማጥፋት የሚደረገውን እንቅስቃሴ ለማውገዝ፣ በየእስር ቤቱ ውስጥ ...

Read More »

የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ ሙሀመድ ኡመር አድገናል በማለት የምናቀርበው ሪፖርት ሁሉ ውሸት ነው አሉ

ግንቦት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፕሬዚዳንቱ የካቢኔ አመራሮችን እና የሶህዴፓ ፓርቲ አባሎችን በመሰብሰብ እንደተናገሩት ክልሉ እንደ ለማ እንደ አደገ ተደርጎ ለመንግስት የሚቀርበው ሪፖርት ሁሉ ግምገማ ለማለፍ ተብሎ የሚቀርብ በውሸት የተሞላ ነው ብለዋል። ፕሬዚዳንቱ በስሜት ውስጥ ሆነው ባደረጉት ንግግር ”  እኛ እንዳደግን ፣ ጥሩ ደረጃ ላይ እንደደረስን ተደርጎ በየጊዜው የሚቀርበው ሪፖርት ፍጹም ትክክል ያልሆነ ውሸት ነው። አሁን በእጄ የያዝኩት ...

Read More »

የኦነግ ወታደሮች አንድ የጸጥታ ሹም ገድለው 7 ፖሊሶችን አቆሰሉ

ግንቦት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቦረና ዞን ፣ የሚኦ ወረዳ  የጸጥታ ዘርፍ ሀላፊ የሆኑት  አቶ ጁኬ የአካባቢውን ፖሊሶች በማሰልፍ የኦነግን ታጣቂዎች ለማደን  ሚያዚያ 29፣ 2005 ዓም ቢንቀሳቀሱም የኦነግ ወታደሮች   ጨሶ እና ሜጢ በሚባል ቦታ ላይ አድፍጠው በመጠበቅ በወሰዱት እርምጃ ፣ የጸጥታ ሹሙን አቶ ጁኬን ገድለው፣ 7 ፖሊሶች ደግሞ አቁስለዋል። 6ቱ ፖሊሶች   በያቤሎ ሆስፒታል ተኝተው በመታከም ላይ ሲሆኑ አንዱ ...

Read More »

በ ደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ደማቅ የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

ግንቦት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢትዮጵያውያኑ ሰልፉን ያደረጉት ገዥው የኢህአዴግ መንግስት ኢትዮጵያ ውስጥ እየፈጸማቸው ያሉትን ኢፍትሀዊ እና ህገ ወጥ ድርጊቶች በመቃወም ነው። በርካታ  ኢትዮጵያውያን በተሳተፉበት በዚህ ሰልፍ፤ ገዥው ፓርቲ ዜጎችን በዘር እየመረጠ ከመኖሪያ ይዞታቸው ከማፈናቀል ተግባሩ እንዲገታ፣ አላግባብ የታሰሩት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ፣ ጋዜጠኞች፣የሙስሊም መሪዎችና ሌሎች የህሊና እስረኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ! መንግስት በሀይማኖት ተቋማት ጣልቃ መግባቱን እንዲያቆም፣በዋልድባ ...

Read More »

አፍሪካ ሚስጢራዊ በሆነ ስምምነት ሀብቷን እየተዘረፈች ነው ተባለ

ግንቦት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የቀድሞውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ  ኮፊ አናን ፣ የቀድሞውን የናይጀሪያ መሪ ኦለሱጎን ኦባሳንጆ እንዲሁም የኔልሰን ማንዴላን ባለቤት ግራሻ ሚሸልን ያቀፍ የጥናት ቡድን ይፋ ባደረገው ጥናት አፍሪካ ግልጽነት በጎደለው ሚስጢራዊ ድርድሮች የተፈጥሮ ሀብቷን እየተዘረፈች ነው። ከታክስ ማጭበርበር ፣ በድብቅ በሚካሄድ የማእድን ማውጣት እና በህገወጥ መንገድ ገንዘብ ወደ ውጭ ከመላክ ጋር በተያያዘ አፍሪካ በየአመቱ ...

Read More »

ታዋቂ የኢትዮጵያ ሶማሊ ተወላጆች የክልሉ ፕሬዚዳንት በድብቅ ያደረጉት ንግግር እየነቀፉ ነው

ግንቦት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢህአዴግ የሽግግር መንግስት ወቅት ለሶስት አመታት በዲፕሎማትነት፣ በመምህርነት እና በጋዜጠኝነት የሰሩትና በርካታ የታሪክ መጽሀፎችን የጻፉት አቶ መሀመድ ሀሰን ለኢሳት እንደተናገሩት ፣ የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ ሙሀመድ ኡመር  የተናገረው ከወያኔ በስሎ የቀረበለትን ነው በማለት ተናግረዋል። “ግለሰቡ ያልተማረ ነፍሰ ገዳይ ነው” የሚሉት አቶ ሙሀመድ ፣ የመለስ ዜናዊ ቀኝ እጅ እንደነበረም ገልጸዋል። ክልሉ ለወያኔ ጄኔራሎች ...

Read More »

ጸረ ሙስና ከ8 ሚሊዮን ብር በላይ የተዘረፈ ገንዘብ እና ሌሎች ንብረቶችን ወረሰ

ግንቦት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌደራልየሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በ2005 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ውስጥ በሙሰኞች የተመዘበረ ከ8ሚሊዮን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ፣ መሬት፣ ህንፃዎችና ሌሎች የተለያዩ ንብረቶችን ለመንግሥት ማስመለሱን አስታወቀ፡፡ ኮሚሽኑ ከሐምሌ 1 ቀን 2004 ዓ.ም እስከ መጋቢት 30 ቀን 2005 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት ብቻ በሙሰኞች የተመዘበሩ 8, ሚሊዮን 11 ሺ 710 ብር በጥሬ ገንዘብ ፣ 1 ሺ ...

Read More »

የፍትሕ ሚኒስትሩ በማረሚያ ቤቶች የሰብዓዊ መብት ጥሰት የለም አሉ

ግንቦት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከብአዴን እና ከኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚነት በቅርቡ በተካሄዱት ጉባዔዎች የተነሱት የፍትህ ሚኒስትሩ አቶ ብርሃን ኃይሉ በማረሚያ ቤቶች የሰብዓዊ መብት ጥሰት መኖሩን አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ የመብት ጥሰት የለም ሲሉ ተናገሩ። በዛሬው ዕለት የመ/ቤታቸውን የ9 ወራት ሪፖርት ለፓርላማ ያቀረቡት ሚኒስትሩ አቶ ብርሃን ኃይሉ ከብቸኛው የአንድነት ፓርቲ የፓርላማ ተወካይ አቶ ግርማ ሰይፉ ጥያቄ ቀርቦላቸዋል፡፡ አቶ ግርማ ባቀረቡት ...

Read More »