ግንቦት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የሙስሊሙ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አመራር አባላት ጀሃዳዊ ሃረካት በሚለው ድራማ በመንግሥት የስም ማጥፋት ዘመቻ ተደርጎብናል ሲሉ ያቀረቡትን የክስ ማመልከቻ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ሬጂስትራር አልቀበልም ማለቱ ተገለጠ። የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች በዚህ የክስ ማመልከቻ 8 ሚሊዮን ብር እንዲከፈላቸው ጠይቀዋል። የሙስሊሙ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አመራር አባላት ጠበቃ ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም ዛሬ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ...
Read More »አንድነት መግለጫ አወጣ
ግንቦት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ጠቅላይ ፍርድ ቤት በእነአንዱዓለም አራጌና በናትናኤል መኮንን የቀረበውን ይግባኝ ውድቅ ማድረጉ በፍትሕ ተቋማት ላይ እምነት መጣል እንደማይቻል ማሳያ ነው ሲል አንድነት ፓርቲ ገለጠ። በፋሲካ በዓል እስረኞቹን ለመጎብኘት የሞከሩት የአንድነት ፓርቲ አመራር አባላትም በልዩ ኃይል ተባረሩ። አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ ገዢው ፓርቲ በማን አለብኝነት የፓርቲው አመራሮችን አስሮ የሚሠራው ሽፍጦች ትግሉን የበለጠ ...
Read More »በአውሮጳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በጄኔቭ የተባበሩት መንግሥታት ዋና መ/ቤት ፊት ለፊት የሕዝብ ትዕይንት አደረጉ
ግንቦት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከአውሮፓ የተለያዩ ከተሞች የተውጣጡ ኢትዮጵያውያን በዛሬው ዕለት በጄኔቭ ስዊትዘርላንድ የተቃውሞ ሰልፍ ያደረጉ ሲሆን በአማሮች ላይ የደረሰውን መፈናቀል የሚያሳይ የጽሑፍ፣ የድምፅና የምስል ማስረጃ ለሦስት ዓለም ዐቀፍ ድርጅቶች ማስረከባቸውንም ባልደረባችን ወንድምአገኝ ጋሹ ከሥፍራው ዘግቧል። ከቤኒንሻንጉል ጉምዝ ክልል በቅርቡ የተፈናቀሉትን አማሮች ሁኔታ በዋናነት በማንሳት ባለፉት 22 ዓመታት በሀገሪቱ የቀጠለውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ በማውሳት የተቃውሞ ድምፃቸውን ያስተባበሩት ...
Read More »ሰማያዊ ፓርቲ በ አፍሪካ ህብረት ጽህፈት ቤት ፊትለፊት የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ጥሪ አቀረበ
ሚያዚያ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአብዛኛው በወጣቶች እና በሴቶች የተገነባው ሰማያዊ ፓርቲ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በመጪው ሜይ 25 በ አፍሪካ ህብረት ጽህፈት ቤት ፊት ለፊት ተቃውሞ ሰልፍ እንዲደረግ ህዝባዊ ጥሪ አስተላለፈ። የተቃውሞ ሰልፉ የሚደረገው የ አፍሪካ ህብረት 50ኛ ኣመት በ ዓሉን በሚያከብርበት ዕለት ነው። ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪል ማህበረሰቡ ተቋማትና ኢትዮጵያውያን ሁሉ በህጋዊውና ሰላማዊው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ...
Read More »የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦይንግ ኩባንያን ካሳ እጠይቃለሁ አለ
ሚያዚያ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አየር መንገዱ ካሳ የሚጠይቀው ከአምስት ወራት በፊት አዲስ ያስገባቸው ቦይንግ 787 አውሮፕላኖች ብዙም አገልግሎት ሳይሰጡ ከበረራ ውጭ ተደርገዉ የቆዩ በመሆኑ ነዉ ፡፡ አውሮፕላኖቹ በረራ አቁመው የነበረው በባትሪያቸዉ ላይ ባጋጠማቸው ችግር ምክንያት በአሜሪካ የፌደራል የበረራ መስሪያ ቤት እገዳ ስለተጣለባቸዉ እንደነበር መዘገቡ ይታወሳል፡፡ የኢትዮዽያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ፥ ከዚህ ...
Read More »ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ቤቱን እንዲለቅ ተገደደ
ሚያዚያ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለጋዜጠኛው ቅርበት ያላቸው ወገኖች ለኢሳት በላኩት መረጃ እንደገለጹት ጋዜጠኛ ተመስገን ተከራይቶ በሚኖርበት ቀበና አካባቢ ያለው ቤቱን እንዲለቅ በአከራዩ የተነገረው አንድ የመስተዳድሩ ባለስልጣንና አንድ ማንነቱ ያልታወቀ ግለሰብ አከራዩ ቤቱን እንዲያስለቀቁት ማስጠንቀቂያ ከሰጡዋቸው በሁዋላ ነው። የቤት አከራዩ ” ሁለቱ ሰዎች መጥተው ለመሆኑ ተመስገን ምን እንደሚሰራ ያውቃሉ ወይ? ተመስገን ማን እንደሆነስ ጠንቅቀው ያውቃሉ ወይ? ለማንኛውም ...
Read More »መንግስት ሸቀጦችን የሚያከፋፍል ድርጅት ለማቋቋም እንቅስቃሴውን መቀጠሉ ታወቀ
ሚያዚያ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ ውስጥ በየጊዜው የሚታየውን የሸቀጦች ዋጋ መናር ለማስቀረት ይረዳል የተባለ የንግድ ድርጅት ለማቋቋም በከፍተኛ እንቅስቃሴ ውስጥ የሚገኘው መንግስት ፣ ድርጅቱ ከተቋቋመ በሁዋላ የማስተዳደር ስራውን ለአሜሪካው የሸቀጦች አከፋፋይ ድርጅት ለማስረከብ በመነጋገር ላይ መሆኑን ፎርቹን ጋዜጣ ዘግቧል። 1 ቢሊዮን ብር የመመስረቻ ካፒታል እንደሚመሰረት የተነገረለት የኢትዮጵያ የሸቀጦች ማከፋፈያ ኢንተርፕራይዝ በሚቀጥለው አመት ስራውን ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል። ...
Read More »ሆላንዳዊውን ባለሀብት የደበደቡ 20 ኢትዮጵያውያን በእስር ላይ ናቸው
ሚያዚያ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ሸዋ ዞን በአና ቦራ ወረዳ በማሊማ በሪ ቀበሌ የሚገኘው የሼር ብሌን ኢትዮጵያ የአበባ እርሻ ባለቤት የሆኑት የሚ/ር ባርኖር ልጅ ሚ/ር ጆን የተባሉት ሆላንዳዊው ባለሀብት በሰራተኞች የተደበደቡት ሚያዚያ 7 ሲሆን፣ ድበደባውን ተከትሎ 27 ሰራተኞች ታስረዋል። ከእነዚህ መካከል 7 ሰዎች ከሶስት ሳምንት በላይ ታስረው በዋስ ሲፈቱ 20ዎቹ አሁንም በእስር ላይ ...
Read More »በሊቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወደ ማይታወቁ ስፍራዎች እየተወሰዱ ነው
ሚያዚያ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በተለያዩ እስር ቤቶች የሚገኙ ኢትዮጵያውያኖች እንደገለጹት ከተለያዩ እስር ቤቶች የተውጣጡ በርካታ ኢትዮጵያውያን ወደ አልታወቁ ስፍራዎች ተሰደዋል። የኢትዮጵያ ዜጎች ከሁሉም ዜጎች ባነሰ ሁኔታ እንደሚስተናገዱ የሚገልጹት እስረኞች ሴቶች ይደፈራሉ፣ ወንዶች ገንዘብ ካላመጡ ይደበደባሉ። ኩሚስ በሚባል እስር ቤት ውስጥ ላለፉት 9 ወራት ታስሮ በስቃይ ላይ የሚገኘው ሽሬ እንደ ስላሴ ተወልዶ ያደገው መምህር ሙሴ ዘ ሚካኤል ...
Read More »የህሊና እስረኞችን ለመጠየቅ ወደ ቃሊቲ የሄዱ ጠያቂዎች በፖሊስ ተባረሩ
ሚያዚያ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የትንሳኤ በአልን ምክንያት በማድረግ በእስር ላይ የሚገኙትን የህሊና እስረኞች ለመጠየቅ ወደ ቃሊቲ ያመሩት የአንድነት ፓርቲ አመራሮች እስካፍንጫቸው በታጠቁ ልዩ ሀይሎች በግድ ከአካባቢው እንዲርቁ መደረጉን ፍኖተ ነጻነት ዘገበ ወጣቱን ፖለቲከኛና ከፍተኛ አመራር አንዱአለም አራጌና ናትናኤል መኮንን ሽብርተኞች እንደሆኑና በሰላማዊ ትግል ሽፋን ሽብርተኝነትን እንደሚያራምዱ ተደርጎ የቀረበው ሀተታና ውሳኔ እጅግ ያሳዘናቸው በርካታ አመራሮችና አባላቱ ...
Read More »