ሱልጣን ሃንፍሬ አሊሚራህ ሰመራ ገቡ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 30 ቀን 2010 ዓ/ም ) ሱልጣኔ በአፋር ዋና ከተማ ሰመራ ሲደርሱ ህዝቡ ወጥቶ ደማቅ አቀባባል አድርጎላቸዋል። በሽግግር መንግስቱ ወቅት የአፋር ክልል መሪ የነበሩት ሱልጣን ሃንፍሬ፣ ከህወሃት ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ከስልጣናቸው እንዲወርዱ በመደረጉ ለስደት ተዳርገዋል። በኢትዮጵያ የሚታየውን የለውጥ እንቅስቃሴ ተከትሎ ወደ አገራቸው የተመለሱት ሱልጣኑ፣ በክልሉ በሚካሄደው የፖለቲካ እንቅስቃሴ ዋና ተዋናይ ይሆናሉ ተብሎ ...
Read More »ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ የአሰብ እና ምጽዋ ወደቦችን ጎበኙ።
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ የአሰብ እና ምጽዋ ወደቦችን ጎበኙ። ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 30 ቀን 2010 ዓ/ም ) ከሃያ ዓመታት በላይ ግንኙነታቸውን አቋርጠው የነበሩት ኢትዮጵያ እና ኤርትራ እርቀ ሰላም በማድረግ ከመሪዎች እና ሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነነት በተጨማሪ የወደብና የንግድ ሥራዎች በይፋ ጀምረዋል። ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በአሰብ ወደብ አየር ማረፊያ በማቅናት ወደቡንና ሁለቱን አገራት የሚያገናኘውን የጥርጊያ መንገድ ጎብኝተዋል። በአሁኑ ወቅት ያለው ...
Read More »በሸካ ዞን የቴፒ ከተማ ነዋሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ
(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 29/2010) በሸካ ዞን የቴፒ ከተማ ነዋሪዎች በአካባቢው አመራሮች የሚፈጸምባቸውን የአስተዳደር በደል በመቃወም የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ። በ10ሺዎች የሚቆጠሩ የከተማዋ ነዋሪዎችና የልዩ ልዩ ብሔረሰቦች ተወላጆች በሸካ ዞን አስተዳደር የሚደርስባቸውን በደል በሰላማዊ ሰልፍ ተቃውመዋል። በአካባቢው የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ በቅርቡ 6 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል። በሸካ ዞን የተለያዩ ብሔረሰቦች በፍቅርና በመተሳሰብ ለዘመናት አብረው ኖረዋል። ባለፉት 27 አመታት በነበረው ብሔርን መሰረት ባደረገው ፖለቲካ ግን ...
Read More »ዶክተር ተቀዳ ዓለሙ ከስልጣናቸው በይፋ ተነሱ
(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 29/2010)ለረዥም ዓመታት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት ዶክተር ተቀዳ ዓለሙ ክስልጣናቸው ተነሱ። በግብጽም አዲስ አምባሳደር ተሹሟል። ከደርግ መንግስት ግዜ ጀምሮ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ ሚኒስትር ዴኤታን ጨምሮ በተለያዩ የሃላፊነት ቦታዎች ያገለገሉት ዶክተር ተቀዳ ዓለሙን የተኳቸው አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ መሆናቸውን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። በግብጽ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት አምባሳደር ታዬ አጽቀ ስላሴ ዶክተር ተቀዳ ዓለሙን ሲተኩ ፣በርሳቸው ምትክ ...
Read More »ሜቴክ ለሁለት እንዲከፈል ተወሰነ
(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 29/2010) የመሰረታዊ ብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኩባንያ/ሜቴክ/ ለሁለት እንዲከፈል ተወሰነ። ሜቴክ በወታደራዊና በንግድ ዘርፉ ለሁለት ተከፍሎ ስራውን እንዲያከናውን በተወሰነው መሰረት በመከላከያ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለስልጣናት የተዋቀረ ቡድን ስራውን በማከናወን ላይ መሆኑ ተመልክቷል። ከፍተኛ ዘረፋ ሲፈጸምበት እንደነበር የሚገለጸው ሜቴክ ዳይሬክተሩ የነበሩትን የህወሃት ጀኔራሉን ክንፈ ዳኘውን ከአራት ወራት በፊት ማሰናበቱ ይታወሳል። አዲስ ፎርቹን ከአዲስ አበባ እንደዘገበው በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ትዕዛዝ መሰረት ...
Read More »13 ጄኔራል መኮንኖች ከሰራዊቱ ተሰናበቱ
(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 29/2010) የሀገር መከላከያ 13 ጄኔራል መኮንኖች ከሰራዊቱ በጡረታ ተሰናበቱ። ጄኔራል መኮንኖቹ በጡረታ የተሰናበቱት የሐገር መከላከያ ሰራዊትን በተሻለ አደረጃጀት ለማዋቀር የተጀመረውን መርሃ ግብር ተከትሎ መሆኑ ታውቋል። ከሃገር መከላከያ ሰራዊት በጡረታ ከተገለሉት መካከል ሜጄር ጄኔራል በርሃነ ነጋሽ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ሃላፊ የነበሩ፣ሌተናል ጂኔራል ሃለፎም እጅጉ የመከላከያ ኮሌጅ አዛዥ፣ሜጄር ጄኔራል ሙሉ ግርማይ ከመከላከያ ሎጅስቲክ ተጠቃሽ መሆናቸውን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። በጠቅላይ ኢታማጆር ሹም ...
Read More »የትግራይ ክልል አስተዳደር ያፈናቀላቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ቆቦ ሰፍረዋል
የትግራይ ክልል አስተዳደር ያፈናቀላቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ቆቦ ሰፍረዋል ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 29 ቀን 2010 ዓ/ም ) የራያ ተወላጆች ህወሃት በሚያዛቸው ወታደሮች አካባቢያቸውን ለቀው እንዲወጡ መደረጋቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገረዋል። በርካታ ወጣቶች የራያን የማንነት ጥያቄ በማንሳታቸው በርካታ ወታደሮችን ያስገቡት የህወሃት መሪዎች፣ በወጣቶች ላይ ጥቃት እየፈጸሙ ነው። ከ400 በላይ ተፈናቃይ ወጣቶች ከአላማጣ ተፈናቅለው ወደ አማራ ክልል በመሄድ ቆቦ ከተማ ላይ የሰፈሩ ...
Read More »የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች መንግስት በወሰደው እርምጃ ግራ መጋባታቸውን ገለጹ
የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች መንግስት በወሰደው እርምጃ ግራ መጋባታቸውን ገለጹ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 29 ቀን 2010 ዓ/ም ) የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት ከመልካም አስተዳደር፣ ከደሞዝ፣ ከማበረታቻና ከፈቃድ ጋር በተያያዘ ላቀረቡት ጥያቄ የደህንነት ሰራተኞች እና ፖሊስ ድጋፋቸውን ሰጥተው የነበረ ቢሆንም፣ በሌሎች ባለስልጣናት ታዘው የአድማ መሪዎች የተባሉ ሰዎች እንዲታሰሩ መደረጉ አስገርሟቸዋል። 120 የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች የአለማቀፍ ሲቪል አቬሽን እና አለማቀፍ የሰራተኞች ...
Read More »በሃረሪ ክልል የህግ የበላይነት እንዲከበር ተጠየቀ
በሃረሪ ክልል የህግ የበላይነት እንዲከበር ተጠየቀ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 29 ቀን 2010 ዓ/ም ) የክልሉ ም/ል ፕሬዚዳንት አቶ ጋዲሳ ተስፋዬ፣ የደቡብ ምስራቅ እዝ ምክትል አዛዥ፣ ጄ/ል ዱባለ አብዲ፣ የክልሉ ፍትህና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ በመሩት ስብሰባ የክልሉ የጸጥታ ችግር እየተባባሰ መምጣቱን ተናግረዋል። ምክንያቱ ደግሞ ከአጎራባች ክልሎች ተደራጅተው የሚመጡ እና በተለያዩ ሰዎች በግልጽም በስወርም ድጋፍ የሚደረግላቸው ሃይሎች ናቸው ብለዋል። የእነዚህ ሰዎች ...
Read More »በደቡብ ሱዳን በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በእስር ቤት ስቃይ እንደደረሰባቸው አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ
በደቡብ ሱዳን በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በእስር ቤት ስቃይ እንደደረሰባቸው አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 29 ቀን 2010 ዓ/ም ) በእስር ቤት ውስጥ ስቃይ የደረሰባቸው ሰዎች አብዛኛዎቹ የፖለቲካ እስረኞች ናቸው። በርካታ ሴቶችም በእስር ቤት ውስጥ ተደፍረዋል። የደቡብ ሱዳን መንግስት የሚቀርብበትን ትችት እንደማይቀበል አምነስቲ ኢንተርናሽናል ገልጿል። የፕሬዚዳንት ሳለቫኪር ቃል አቀባይ አቴንግ ዋግ አቴንግ የአምነስቲን ሪፖርት አስተባብለው በቅርቡ 20 የፖለቲካ እስረኞች ...
Read More »