ዶክተር ተቀዳ ዓለሙ ከስልጣናቸው በይፋ ተነሱ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 29/2010)ለረዥም ዓመታት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት  የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት ዶክተር ተቀዳ ዓለሙ  ክስልጣናቸው ተነሱ። በግብጽም አዲስ አምባሳደር ተሹሟል።

ከደርግ መንግስት ግዜ ጀምሮ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ ሚኒስትር ዴኤታን ጨምሮ በተለያዩ የሃላፊነት ቦታዎች ያገለገሉት ዶክተር ተቀዳ ዓለሙን የተኳቸው አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ መሆናቸውን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በግብጽ  የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት አምባሳደር ታዬ አጽቀ ስላሴ  ዶክተር ተቀዳ ዓለሙን ሲተኩ ፣በርሳቸው ምትክ በግብጽ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው የተሾሙት አምባሳደር አዛነው ታደስ ናቸው።አምባሳደር አዛነው ታደሰ ካይሮ መግባታቸውም ታውቋል።