የአዲስቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ ኦባንግ ሜቶን ጨምሮ 15 አባላት ያለው ቡድን ወደ ኢትዮጵያ ገቡ።

የአዲስቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ ኦባንግ ሜቶን ጨምሮ 15 አባላት ያለው ቡድን ወደ ኢትዮጵያ ገቡ። ( ኢሳት ዜና ጳግሜን 01 ቀን 2010 ዓ/ም ) የአዲስቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (Solidarity Movement for New Ethiopia) መስራችና ሊቀመንበር የሆኑት የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አቶ ኦባንግ ሜቶን ጨምሮ 15 አባላትን ያካተተው ቡድን ወደ አገራቸው የገቡ ሲሆን በምንግስት ባለስልጣናት አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ቡድኑ በመንግስት የቀረበለትን የሰላም ...

Read More »

በኤርትራ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሁለቱም አገራት መሪዎች በተገኙበት በይፋ ተከፈተ

በኤርትራ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሁለቱም አገራት መሪዎች በተገኙበት በይፋ ተከፈተ ( ኢሳት ዜና ጳግሜን 01 ቀን 2010 ዓ/ም ) በኤርትራ ላለፉት ሃያ ዓመታት ተዘግቶ የነበረው የኢትዮጵያ ኤንባሲ በዛሬው ዕለት በጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ እና በፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ተመርቆ ተከፈተ። ከወራት በፊት ኤርትራም በተመሳሳይ ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ተዘግቶ የቆየውን ኤንባሲዋን በአዲስ አበባ መክፈቷ ይታወሳል። ይህም የሁለቱ አገራት የሁለትዮሽ ግንኙነትን ወደ ላቀ ...

Read More »

አንዲት የ13 አመት ታዳጊ ከተደፍረች በኋላ በተደፋባት አሲድ ሕይወቷ አለፈ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 30/2010)አንዲት የ13 አመት ታዳጊ ከተደፍረች በኋላ በተደፋባት አሲድ መሰል ንጥረ ነገር ሕይወቷ አለፈ። ጫልቱ አብዲ የተባለችውና ከምስራቅ ሐረርጌ በደኖ ወደ ሐረር መጥታ የቤት ሰራተኛ የነበረችው ይህች ታዳጊ የተደፈረችውና ሕይወቷ ያለፈው በአሰሪዋ እንደሆነም ተመልክቷል። ስሙ ያልተጠቀሰው ይህ ግለሰብ ታዳጊዋን ከደፈራት በኋላ የአሲድ ጥቃት እንደፈጸመባትም ተመልክቷል። ከጥቃቱም በኋላ በስቃይ ውስጥ እያለች በቤት ተደብቃ እንድትቀመጥ ማድረጉም ታውቋል። ታዳጊዋ ከመሞቷ በፊት ለፖሊስ ...

Read More »

የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ለተጨማሪ የምርመራ ጊዜ በእስር ላይ እንዲቆዩ ተደረገ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 30/2010) አድማ በማስተባበር ተጠርጥረው የታሰሩት ዘጠኝ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ለተጨማሪ የምርመራ ጊዜ በእስር ላይ እንዲቆዩ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ አሳለፈ። በሌላም በኩል በአድማ ላይ የቆዩት የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ዛሬ ስራ መጀመራቸውን መንግስታዊ መገናኛ ብዙሃን በዘገባቸው አስፍረዋል። የ10 እጥፍ የደሞዝ ጭማሪ በመጠየቅ ከነሐሴ 21/2010 ጀምሮ አድማ ላይ የቆዩት የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ዛሬ ሙሉ በሙሉ እንዴት እንደተመለሱ በዝርዝር የተገለጸ ነገር ባይኖርም ...

Read More »

ኢትዮጵያ፣ ኤርትራና ሶማሊያ የሶስትዮሽ ውይይት ሊያደርጉ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 30/2010) ኢትዮጵያ፣ ኤርትራና ሶማሊያ በአካባቢው ጉዳዮች ላይ የሶስትዮሽ ውይይት ለማድረግ ዛሬ አስመራ ገቡ። በዚህ ውይይት ላይ ለመሳተፍ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድና የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሙሐመድ አብዱላሒ/ፎርማጆ/ኤርትራ መግበታቸው ተሰምቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በኤርትራ ቆይታቸው ወደ አሰብና ምጽዋ ተጉዘው ሁለቱ ወደቦች አገልግሎት የሚሰጡበትን ሁኔታ መመልከታቸውም ታውቋል። ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ በቻይና የቆዩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ከቤጂንግ ወደ ኤርትራ ያቀኑ ሲሆን ...

Read More »

የራያ ተወላጆች ሰልፍ አካሄዱ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 30/2010) ከወሎ ክፍለ ሃገር ተወስዶ ወደ ትግራይ ክልል ያለፍላጎቱ የተጠቃለለው የራያ ተወላጆች የማንነት ጥያቄ በማንሳት የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ። የራያ ተወላጆች በአዲስ አበባ ከተማ ባካሄዱት ሰልፍ በራያ ሕዝብ ላይ የሚፈጸመው የሰብአዊ መብት ረገጣ እንዲቆምና በሕገ መንግስቱ መሰረት ማንነታቸው እንዲከበር ጠይቀዋል። ሰልፈኞቹ ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቅጥር ግቢ በመነሳት ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት  አምርተው ጥያቄያቸውን ማቅረባቸው ታውቋል። የራያ ተወላጆች ያለፍላጎታችን ወደ ትግራይ ...

Read More »

የሕዳሴው ግድብ ገንዘብ የገባበት አይታወቅም ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 30/2010)ለሕዳሴው ግድብ ግንባታ ተሰብስቦ ከነበረው ገንዘብ ውስጥ ከግማሽ በመቶ በላይ የሚሆነው የገባበት አይታወቅም ተባለ። ገንዘቡ የደረሰበትን ለማወቅም በመጣራት ላይ መሆኑን የሜቴክ የኮሜርሻልና ሲቪል ምርቶች ኦፕሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ገልጸዋል። በ5 አመት ይጠናቀቃል የተባለው የህዳሴው ግድብ ግንባታም ቢሆን ከ25ና ከ30 በመቶ በላይ አለመጠናቀቁም ታውቋል። አቃቤ ህግ በበኩሉ በዚህ ሒደት ውስጥ ያሉ አካላት በሙሉ ተጠያቂ ይሆናሉ ብሏል። በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ...

Read More »

በራያ ሕዝብ ላይ ያነጣጠረው ጥቃት እንዲቆም የሚጠይቅ የተቃውሞ ሰልፍ በአዲስ አበባ ተደረገ።

በራያ ሕዝብ ላይ ያነጣጠረው ጥቃት እንዲቆም የሚጠይቅ የተቃውሞ ሰልፍ በአዲስ አበባ ተደረገ። ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 30 ቀን 2010 ዓ/ም ) የትግራይ ክልል በልዩ ጦሩና በሚሊሺያው አማካኝነት የሚፈጽመውን የመብት ጥሰት እንዲያቆም ሰልፈኞቹ ጠይቀዋል። መነሻቸውን ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጣቢያ ያደረጉት ሰልፈኞቹ ፍትህ ለራያ ሕዝብ፣ ማንነታችን ይከበር፣ የትግራይ ልዩ ኃይል የሚፈጽመውን ጭፍጨፋ ያቁም፤ የሚሉና የተለያዩ መፈክሮችን አሰምተዋል። በሕዝብ ቀረጥ የሚተዳደረው ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ኢቲቪ ...

Read More »

በረጲ የደረቅ ቆሻሻ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከፍተኛ ሙስና መፈጸሙን የውስጥ ምንጮች ገለጹ

በረጲ የደረቅ ቆሻሻ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከፍተኛ ሙስና መፈጸሙን የውስጥ ምንጮች ገለጹ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 30 ቀን 2010 ዓ/ም ) ከ120 ሚሊዮን ዶላር ወይም አሁን ባለው ምንዛሬ ከ3 ቢሊዮን ብር ያላነሰ በጀት ተመድቦለት የተሰራው የአዲስ አበባ ረጲ የደረቅ ቆሻሻ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከውል ስምምነት ጀምሮ ሙስና የተፈጸመበት እንደሆነና ለዚህም ዋናው ተጠያቂ በወቅቱ የኢትዮጵያ መብራት ሃይል ቦርድ ዳይሬክተር ዶ/ር ደብረጺዮን ...

Read More »

አርቲስት ታማኝ በየነ በጎንደር ከተማ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት

አርቲስት ታማኝ በየነ በጎንደር ከተማ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 30 ቀን 2010 ዓ/ም ) ከሃያ ሁለት ዓመታት በኋላ ወደ ትውልድ አገሩ ኢትዮጵያ የተመለሰው የሰብዓዊ መብት ተሟጋችና አርቲስት ታማኝ በየነ በዛሬው እለት በጎንደር ከተማ በመገኘት ከሚወዱት አድናቂዎቹ ጋር ፊት ለፊት ተገናኝቷል። ታማኝን በየነና ባለቤቱን አርቲስት ፋንቲሽ በቀለን ለመቀበል የከተማ ነዋሪዎች፣ የክልሉ ባለስልጣናትን ጨምሮ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ከጎንደር አጼ ...

Read More »