በአንድ አመት ከስድስት ወር ይጠናቀቃሉ ተብሎ ከ2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ የወጣባቸው የስኳር ፕሮጀክቶች ከ6 አመታት በሁዋላም አልተጠናቀቁም

በአንድ አመት ከስድስት ወር ይጠናቀቃሉ ተብሎ ከ2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ የወጣባቸው የስኳር ፕሮጀክቶች ከ6 አመታት በሁዋላም አልተጠናቀቁም ( ኢሳት ዜና ጳግሜን 02 ቀን 2010 ዓ/ም ) በቀድሞው የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ አባይ ጸሃዬ እና በሜቴክ የቀድሞው ዋና ዳይሬክተር ጀኔራል ክንፈ ዳኘው መካከል የተፈረመው የውል ሰነድ እንደሚያሳየው ከፍተኛ ሃብት የፈሰሰባቸው 10 የስኳር ፕሮጀክቶች በ2005 እና በ2006 ምርት ማምረት ነበረባቸው። ...

Read More »

በሃረር ከተማ የሚኖሩ የጉራጌ ተወላጆች በፖለቲካና በኢኮኖሚ ፍትሃዊ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ጠየቁ

በሃረር ከተማ የሚኖሩ የጉራጌ ተወላጆች በፖለቲካና በኢኮኖሚ ፍትሃዊ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ጠየቁ ( ኢሳት ዜና ጳግሜን 02 ቀን 2010 ዓ/ም ) በከተማዋ የሚኖሩ የጉራጌ ተወላጆች ነሃሴ 25 ቀን 2010ዓም በኢሚር አብዱላሂ አዳራሽ ባካሄዱት ስብሰባ፣ የሐረር ከተማ የጉራጌ ብሔረሰብ ተወላጆች የአቋም መግለጫ ፣ “በህገ መንግስቱ የተረጋገጠልን በየትኛውም የሐገሪቱ ክፍሎች ተዘዋውሮ የመስራትና ሀብት የማፍራት መብታችን ሳይሸራረፍ እንዲከበር እንታገላለን፡፡” ሲሉ ጠይቀዋል። ተወላጆቹ ፣ ለውጡን ...

Read More »

በሰላም አስከባሪነት የተሰማሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላቶች ምዝበራ እንደተፈጸመባቸው አስታወቁ። ጉዳዩንም ለጠቅላይ ሚንስትሩ እና ለሚመለከታቸው አካላት አሳውቀዋል።

በሰላም አስከባሪነት የተሰማሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላቶች ምዝበራ እንደተፈጸመባቸው አስታወቁ። ጉዳዩንም ለጠቅላይ ሚንስትሩ እና ለሚመለከታቸው አካላት አሳውቀዋል። ( ኢሳት ዜና ጳግሜን 02 ቀን 2010 ዓ/ም ) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፈቃጅነት አፍሪካን በመወከል በጎረቤት አገራት ሰላም ለማስከበር የተሰማሩ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ የተለያዩ ምዝበራዎች ሲፈጸምባቸው መቆየቱን የሰራዊቱ አባላት ለመንግስት እና ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት በጻፉት ደብዳቤ አመልክተዋል። በመንግስት የተሰጣቸውን ግዴታዎች ከመወጣት በተጨማሪ ...

Read More »

አቶ ኦባንግ ሜቶ አዲስ አበባ ገቡ

(ኢሳት ዲሲ–ጳጉሜ 1/2010)የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ መስራችና ፕሬዝዳንት አቶ ኦባንግ ሜቶ ዛሬ አዲስ አበባ ገቡ። ለረዥም ዓመታት በስደት የቆዩት የመብት ተሟጋቹ አቶ ኦባንግ ሜቶ ዛሬ ሐሙስ ማለዳ አዲስ አበባ ሲደርሱ የመንግስት ባለስልጣናት አቀባበል አድርገውላቸዋል። በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሱ የመብት ጥሰቶችን ግድያና አፈና በአሜሪካ ኮንግረስና በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች ጭምር ሲያጋልጡ የቆዩት አቶ ኦባንግ ሜቶ በኢትዮጵያ ውስጥ ነዋሪዎችን በማፈናቀል የሚፈጸሙ የመሬት ወረራዎችን ...

Read More »

የዲያስፖራ ኤጀንሲ ሊቋቋም ነው

(ኢሳት ዲሲ–ጳጉሜ 1/2010) በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ የዲያስፖራ ኤጀንሲ ሊቋቋም መሆኑ ተገለጸ። በዳይሬክተር የሚመራውና ምክትል ዳይሬክተር የሚኖረው የዲያስፖራ ኤጀንሲ በራሱ በጀት ኖሮት፣ለፓርላማው በራሱ ሪፖርት የሚያቀርብ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዛሬ ለጋዜጠኞች ገልጸዋል። በውጭ ሃገር የሚኖረውን ኢትዮጵያዊ መብት ለማስጠበቅ እንደሚቋቋም የተገለጸው የዲያስፖራ ኤጀንሲ፣በሚኒስትሮች ምክር ቤት ከጸደቀ በኋላ አንዳንድ የሕግ ጉዳዮች ሲያልቁ ስራ እንደሚጀርም ተመልክቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በሐምሌ ...

Read More »

በማንነት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ተቀባይነት የለውም ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጳጉሜ 1/2010) የትግራይን ሕዝብ አንድነት ለማዳከም ሆነ ተብሎ የሚካሄድ በማንነት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ተቀባይነት የለውም ሲል የክልሉ መንግስት ገለጸ። የማንነት ጥያቄ ህገ መንግስታዊ መልስ ባገኘበት ሁኔታ አንድ ጊዜ ወልቃይት ሌላ ግዜ ራያ እያሉ የትግራይን ህዝብ አንድነት ለማዳከም አልሞ መስራት በማንኛውም መመዘኛ ተቀባይነት የለውም ብሏል። የራያ ተወላጆች ማንነታችን ይከበር በሚል በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄዳቸው ይታወሳል። የትግራይ ክልላዊ መንግስት መግለጫ ...

Read More »

ኢትዮጵያ፣ኤርትራና ሶማሊያ የሶስትዮሽ ስምምነት ተፈራረሙ

(ኢሳት ዲሲ–ጳጉሜ 1/2010) የኢትዮጵያ፣ኤርትራና ሶማሊያ መሪዎች የሶስትዮሽ ስምምነት ተፈራረሙ። ትብብሩን ለማስፋት በተያዘው እቅድ መሰረትም የኢትዮጵያ፣የኤርትራና የሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ዛሬ ጅቡቲ ገብተዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለም ከ1990 ጀምሮ ለ20 አመታት ተዘግቶ የነበረው በአስመራ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዛሬ በሁለቱ ሃገራት መሪዎች በይፋ ተከፍቷል። የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፍወርቂ፣ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት መሐመድ አብድላሂ (ፎርማጆ) አስመራ ላይ ያደረጉትን ውይይት ...

Read More »

የሜቴክ ዘረፋ የተደራጀ ሌብነት ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጳጉሜ 1/2010) በመሰረታዊ ብረታብረት ኮርፖሬሽን ሜቴክ ውስጥ የሚካሄደው ዘረፋ ብሔርን መሰረት ያደረገና እጅግ የተደራጀ ሌብነት መሆኑ ተገለጸ። ሜቴክን ከምስረታው ጀምሮ የሚያውቁት ብርጋዴር ጄኔራል መላኩ ሽፈራው ለኢሳት እንደገለጹት በዘረፋው ሒደት በደላላነት በሚሊየን ዶላሮች የሃገሪቱን ሃብት የሚቀራመቱ ግለሰቦችን በዝርዝር አስቀምጠዋል። ዘረፋውን በመቃወማቸውም ከተቋሙ የተባረሩና የተሰናበቱ የአማራ፣የኦሮሞና የሌላ ብሔረሰብ ተወላጆችን ስም ዘርዝረዋል። በሃገር መከላከያ ሚኒስቴር የመረጃ መረብ ከፍተኛ ሃላፊ የነበሩት ብርጋዴር ጄኔራል ...

Read More »

በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ የዘረፉና ያባከኑ ሰዎች ሜቴክን እየለቀቁና ማእረጋቸውን እየለወጡ በሲቪል አስተዳደርነት እየተቀጠሩ ነው

በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ የዘረፉና ያባከኑ ሰዎች ሜቴክን እየለቀቁና ማእረጋቸውን እየለወጡ በሲቪል አስተዳደርነት እየተቀጠሩ ነው ( ኢሳት ዜና ጳግሜን 01 ቀን 2010 ዓ/ም )የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ሜቴክ በአገሪቱ ውስጥ ላወደመውና ላዘረፈው በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ዋና ተጠያቂ የሆኑ የቀድሞ ወታደራዊ መሪዎች ማእረጋቸውን እየተዉ በሲቪል ተቋማት ውስጥ እየተቀጠሩ ነው። የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ የሆኑት ዶ/ር ሶሎሞነ ኪዳኔ ወደ ከንቲባነት ከመምጣታቸው በፊት የሜቴክ ዋና ...

Read More »

በሰኔ 16ቱ የቦንብ ጥቃት ተጠርጣሪ በሆኑት አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ላይ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ተሰጠባቸው

በሰኔ 16ቱ የቦንብ ጥቃት ተጠርጣሪ በሆኑት አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ላይ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ተሰጠባቸው ( ኢሳት ዜና ጳግሜን 01 ቀን 2010 ዓ/ም ) በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል ዓደባባይ ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም በተጠራው የምስጋና እና የመደመር የድጋፍ ሰልፍ ወቅት በተፈጸመው የቦንብ ጥቃት እጃቸው አለበት ተብለው ከተጠረጠሩት አንዱ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ላይ መርማሪ ፖሊስ ያቀረበውን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፍርድ ...

Read More »