ጠ/ሚ አብይ አህመድና ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለአጭር ጊዜ ተገናኝተው ተነጋገሩ

ጠ/ሚ አብይ አህመድና ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለአጭር ጊዜ ተገናኝተው ተነጋገሩ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 20 ቀን 2010 ዓ/ም ) አሜሪካ የሚገኙት ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ከአርበኞች ግንቦት7 መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር ተገናኝተው ተነጋግረዋል። ለአንድ ሰዓት ያክል የነበራቸው ግንኙነት የትውውቅ እንደነበረና ተጨማሪ ውይይቶችን እንደሚያካሂዱ ታውቋል። አርበኞች ግንቦት7 መሰረታዊ የሆኑ የዲሞክራሲ ተቋማት እንዲገነቡ ላለፉት 10 አመታት ትግል ሲያካሂድ ቆይቷል። ዶ/ር አብይ ጠ/ሚኒስትር ...

Read More »

ኢትዮጵያውያን በኢንጂነር ስመኛው በቀለ ሞት የተሰማቸውን ሃዘን እየገለጹ ነው

ኢትዮጵያውያን በኢንጂነር ስመኛው በቀለ ሞት የተሰማቸውን ሃዘን እየገለጹ ነው ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 20 ቀን 2010 ዓ/ም ) በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ዜጎች በአባይ ግድብ ዋና መሃንዲስ በኢንጂነር ስመኛው ሞት የተሰማቸውን ሃዘን በመግለጽ፣ የኢንጂኒሩ አሟሟት ሁኔታ በፍጥነት ተጣርቶ ለህዝብ እንዲገለጽ እየጠየቁ ነው። በጎንደር ከተማ ወጣቶች ወደ አደባባይ ወጥተው ተቃውሞአቸውን የገለጹ ቢሆንም፣ የከተማው የአገር ሽማግሌዎች ወጣቶችን በመምከር አረጋግተዋቸዋል። በባህርዳርና በደሴ እንዲሁ ...

Read More »

በአወዳይ አንድ ታጣቂ የነበረ ግለሰብ 3 ሰዎችን ገደሎ 5 ሰዎችን ደግሞ አቆሰለ::

በአወዳይ አንድ ታጣቂ የነበረ ግለሰብ 3 ሰዎችን ገደሎ 5 ሰዎችን ደግሞ አቆሰለ:: ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 20 ቀን 2010 ዓ/ም )ሃሙስ እለት ከአስተዳደር ጥበቃ ስራ የተባረረው ከድር ኢብራሂም የተባለው ታጣቂ በህዝቡ ላይ ጥይት በመተኮስ 3 ሰዎችን ወዲያውኑ ሲገድል 5 ሰዎች ደግሞ ቆስለው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል። ህዝቡ በወሰደው እርምጃም ሰውዬው በአሰቃቂ ሁኔታ መገደሉ ታውቋል። ግለሰቡ ከስራ ከተሰናበተ በሁዋላ ታጥቆት የነበረውን የጦር ...

Read More »

የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ከነገ ጀምሮ ኤርትራን ይጎበኛሉ።

የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ከነገ ጀምሮ ኤርትራን ይጎበኛሉ። ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 20 ቀን 2010 ዓ/ም ) በአፍሪቃ ቀንድ በቅርቡ እየተስተዋሉ ያሉ የፖለቲካ አሰላለፍና የዲፕሎማሲ ለውጦችን ተከትሎ የሶማሊያው ፕሬዚዳንት መሀመድ አብዱላሂ ፎርማጆ ከነገ ጀምሮ በኤርትራ የሦስት ቀናት የሥራ ጉብኝት ያደርጋሉ። የኤርታራው ማስታወቂያ ሚኒስትር በትዊተር ገጻቸው እንደገለጹት የሶማሊያ ሪፐብሊክ መሪ የሆኑት ፕሬዚዳንት ፎርማጆ ኤርትራን የሚጎበኙት፣ በፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ግብዣ መሰረት ነው። በዚህም መሰረት ...

Read More »

ኢሳያስ አፈወርቄ የሶማሊያውን ፕሬዝዳንት ጋበዙ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 20/2010) የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቄ የሶማሊያውን ፕሬዝዳንት አስመራ ጋበዙ። የሶማሊያው ፕሬዝዳንት መሐመድ አብዱላሂ በፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ግብዣ መሰረት ነገ አስመራ ይገባሉ። የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል በቲውተር ገጻቸው እንደገለጹት የሶማሊያ ፕሬዝዳንት መሐመድ አብዱላሂ በቅጽል ስማቸው ፎርማጆ የሶስት ቀናት ጉብኝት ለማድረግ ነገ ማለዳ አስመራ ይገባሉ። የኤርትራ መንግስት አልሻባብን ይረዳል በሚል በቀረበበትና በኋላም ምንም ማረጋገጫ እንዳልተገኘበት በይፋ በተገለጸው ወንጀል ...

Read More »

የኢንጂነር ስመኘው በቀለ ግድያ በአስቸኳይ እንዲጣራ ተጠየቀ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 20/2010) የኢንጅነር ስመኘው በቀለ ግድያ በአስቸኳይ ተጣርቶ ፍትህ እንዲሰጥ በጎንደር ፣ ማክሰኝትና በባህርዳር ከተሞች የሚገኙ ወጣቶች ጠየቁ። በጎንደር በነበረው ህዝባዊ ቁጣ ከጸጥታ አስከባሪዎች ጋር ግጭት ተፈጥሮ አንድ ወጣትና አንድ ታዳጊ በጥይት ተመተው ጉዳት ደርሶባቸዋል። የኢንጅነር ስመኘው በቀለ የቀብር ስነስርዓት የፊታችን እሁድ በአዲስ አበባ ቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን እንደሚፈጸም ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ትላንት ጠዋት አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ተገድለው የተገኙት ...

Read More »

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጋር መከሩ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 20/2010) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ከፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጋር ተወያዩ። የአርበኞች ግንቦት 7 ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌም ትላንት ምሽት አሜሪካ ገብተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ከፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ጋር እንደሚወያዩም ከወጣው መርሃ ግብር መረዳት ተችሏል። ትላንት ሐሙስ ማለዳ ዋሽንግተን ዲሲ የደረሱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ረፋድ ላይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች የዕርቅ ሒደት ...

Read More »

ፓትሪያርክ አቡነ መርቆሪዎስ በነሐሴ መጨረሻ ወደ ሃገራቸው ሊመለሱ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 20/2010) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ አቡነ መርቆሪዎስ በነሐሴ መጨረሻ ወደ ሃገራቸው እንደሚመለሱ ምንጮች ገለጹ። በሁለቱ ሲኖዶሶች መካከል ከሩብ ክፍለ ዘመን በላይ የቀጠለው ውዝግብ ፍጻሜ ማግኘቱም ይፋ ሆኗል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በተገኙበት በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ዋተር ጌት ሆቴል ውስጥ በተካሄደው ስነስርአትም  አቡነ መርቆሪዎስ ከነሙሉ ክብራቸውና ማዕረጋቸው ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው በመንበራቸው እንዲቀመጡ ተወስኗል። በብጹዕ አቡነ አብርሃም በተነበበውና በሁለቱም ...

Read More »

አቶ በረከት ስምኦን አዲስ መጽሃፍ ጻፉ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 19/2010) አቶ በረከት ስምኦን አዲስ መጽሃፍ መጻፋቸው ተሰማ። ከፖለቲካው መድረክ በለውጥ ሃይሉ ተገፍተው ከወጡት የኢሕአዴግ የቀድሞ አመራሮች አንዱ በሆኑት አቶ በረከት ስምኦን የተጻፈው መጽሃፍ ትንሳኤ ኢትዮጵያ የሚል ርዕስም እንደተሰጠው ታውቋል። የአቶ በረከት መጽሃፍ መታሰቢያነቱ ለሟቹ ለቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ነው ተብሏል። “ትንሳኤ ኢትዮጵያ” በሚል አብይ ርዕስ “ኢትዮጵያ መስቀለኛ መንገድ ላይ ነች”በሚል ንኡስ የቀረበው የአቶ በረከት መጽሃፍ “ከተመጽዋችነት ...

Read More »

የአባይ ግድብ ዋና መሃንዲስ መኪናቸው ውስጥ ሞተው ተገኙ

የአባይ ግድብ ዋና መሃንዲስ መኪናቸው ውስጥ ሞተው ተገኙ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 19 ቀን 2010 ዓ/ም ) ግድቡን በዋና ሃላፊነት ሲመሩ የነበሩት ኢንጂነር ስመኛው በቀለ መስቀል አደባባይ ከዋናው መንገድ ገባ ብሎ በቪ 8 መኪናቸው ውስጥ ህይወታቸው አልፎ መገኘቱን የፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘይኑ ጀማል ገልጸዋል። ኮሚሽነሩ ዘይኑ፣ ኢንጂነር ስመኛው ህይወታቸው ያለፈው በጥይት ተመተው እንደነበረ፣ በቀኝ እጃቸው በኩል ኮልት ሽጉጥ መገኘቱን ገልጸዋል። ...

Read More »