ጠ/ሚ አብይ አህመድና ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለአጭር ጊዜ ተገናኝተው ተነጋገሩ

ጠ/ሚ አብይ አህመድና ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለአጭር ጊዜ ተገናኝተው ተነጋገሩ
( ኢሳት ዜና ሃምሌ 20 ቀን 2010 ዓ/ም ) አሜሪካ የሚገኙት ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ከአርበኞች ግንቦት7 መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር ተገናኝተው ተነጋግረዋል። ለአንድ ሰዓት ያክል የነበራቸው ግንኙነት የትውውቅ እንደነበረና ተጨማሪ ውይይቶችን እንደሚያካሂዱ ታውቋል።
አርበኞች ግንቦት7 መሰረታዊ የሆኑ የዲሞክራሲ ተቋማት እንዲገነቡ ላለፉት 10 አመታት ትግል ሲያካሂድ ቆይቷል። ዶ/ር አብይ ጠ/ሚኒስትር ከሆኑ በሁዋላም እርሳቸው የጀመሩትን የለውጥ እንቅስቃሴ በመደገፍ የሃይል አማራጭ ትግን መግታቱን አስታውቋል።
ሌላው የድርጅቱ አመራር አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከእስር በተፈቱ ማግስት ዶ/ር አብይ በቤተመንግስት ተቀብለው አነጋግረዋቸዋል።
አርበኞች ግንቦት7 ከጠ/ሚኒስትሩ ጋር ከሚያደርገው ውይይት በሁዋላ በአገር ውስጥ ትግል ስለሚጀምርበት ሁኔታ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።