አቶ በረከት ስምኦን አዲስ መጽሃፍ ጻፉ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 19/2010) አቶ በረከት ስምኦን አዲስ መጽሃፍ መጻፋቸው ተሰማ።

ከፖለቲካው መድረክ በለውጥ ሃይሉ ተገፍተው ከወጡት የኢሕአዴግ የቀድሞ አመራሮች አንዱ በሆኑት አቶ በረከት ስምኦን የተጻፈው መጽሃፍ ትንሳኤ ኢትዮጵያ የሚል ርዕስም እንደተሰጠው ታውቋል።

የአቶ በረከት መጽሃፍ መታሰቢያነቱ ለሟቹ ለቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ነው ተብሏል።

“ትንሳኤ ኢትዮጵያ” በሚል አብይ ርዕስ “ኢትዮጵያ መስቀለኛ መንገድ ላይ ነች”በሚል ንኡስ የቀረበው የአቶ በረከት መጽሃፍ “ከተመጽዋችነት ወደ አፍሪካ ግንባር ቀደምትነት” የሚል ሶስተኛ ንጹስ ርዕስም በመደረብ ፊት ለፊቱ በጽሁፍ የተሞላ እንደሆነም ተመልክቷል።

በኢኮኖሚ ባለሙያዎች ጥያቄ የተነሳበትንና በራሱ በአንዳንድ የመንግስት ሃላፊዎች ጭምር እየተተቸ ያለውን የማዕከላዊ ስታስቲክስ መስሪያ ቤት መረጃ በዋቢነት እየጠቀሰና እያሰፈረ ያቀረበው የአቶ በረከት ስምኦን መጽሃፍ በቅርቡ ለንባብ ይበቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ለአቶ መለስ ዜናዊ መታሰቢያነቱን የሰጠውን መጽሃፍ በማሳተም ላይ ያሉት አቶ በረከት ስምኦን በሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ ከሚቀርብባቸው የኢሕአዴግ መሪዎች አንዱ መሆናቸው ይታወቃል።

በቅርቡ እንኳን እሳቸውን ያሳፈረ ነው የተባለ ተሽከርካሪ በሕዝብ ቁጣ ሲቃጠል አረፉበት የተባለው ሆቴልም ጉዳት እንደደረሰበት ይታወሳል።