በአወዳይ አንድ ታጣቂ የነበረ ግለሰብ 3 ሰዎችን ገደሎ 5 ሰዎችን ደግሞ አቆሰለ::

በአወዳይ አንድ ታጣቂ የነበረ ግለሰብ 3 ሰዎችን ገደሎ 5 ሰዎችን ደግሞ አቆሰለ::
( ኢሳት ዜና ሃምሌ 20 ቀን 2010 ዓ/ም )ሃሙስ እለት ከአስተዳደር ጥበቃ ስራ የተባረረው ከድር ኢብራሂም የተባለው ታጣቂ በህዝቡ ላይ ጥይት በመተኮስ 3 ሰዎችን ወዲያውኑ ሲገድል 5 ሰዎች ደግሞ ቆስለው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል።
ህዝቡ በወሰደው እርምጃም ሰውዬው በአሰቃቂ ሁኔታ መገደሉ ታውቋል። ግለሰቡ ከስራ ከተሰናበተ በሁዋላ ታጥቆት የነበረውን የጦር መሳሪያ አለማስረከቡን ወኪላችን ገልጿል።