በኤርትራ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሁለቱም አገራት መሪዎች በተገኙበት በይፋ ተከፈተ

በኤርትራ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሁለቱም አገራት መሪዎች በተገኙበት በይፋ ተከፈተ
( ኢሳት ዜና ጳግሜን 01 ቀን 2010 ዓ/ም ) በኤርትራ ላለፉት ሃያ ዓመታት ተዘግቶ የነበረው የኢትዮጵያ ኤንባሲ በዛሬው ዕለት በጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ እና በፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ተመርቆ ተከፈተ። ከወራት በፊት ኤርትራም በተመሳሳይ ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ተዘግቶ የቆየውን ኤንባሲዋን በአዲስ አበባ መክፈቷ ይታወሳል።
ይህም የሁለቱ አገራት የሁለትዮሽ ግንኙነትን ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግራል የተባለለት ግንኙነት በሁሉም መስክ የተሻለ ቅርርብን ይፈጥራል ተብሎ ተገምቷል። አምባሳደር አቶ ሬድዋን ሁሴን በኢትዮጵያ የኤርትራ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው ተሹመዋል።
በኤርትራ መዲና አስመራ የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ እና የሶማሊያ መሪዎች ተገናኝተው በቀጠናው የሰላም፣ የደኅንነትና የልማት ጉዳዮች ላይ በጋራ መክረዋል። በተጨማሪም በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ደረጃ ለመነጋገረ ወደ ጅቡቲ ማቅናታቸውም ታውቋል።